Ash-Shams
الشمس
The Sun • 15 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلشَّمۡسِ وَضُحَىٰهَا﴿١﴾
1በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡
وَٱلۡقَمَرِ إِذَا تَلَىٰهَا﴿٢﴾
2በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤
وَٱلنَّهَارِ إِذَا جَلَّىٰهَا﴿٣﴾
3በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤
وَٱلَّيۡلِ إِذَا يَغۡشَىٰهَا﴿٤﴾
4በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤
وَٱلسَّمَآءِ وَمَا بَنَىٰهَا﴿٥﴾
5በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤
وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا طَحَىٰهَا﴿٦﴾
6በምድሪቱም በዘረጋትም፤
وَنَفۡسٖ وَمَا سَوَّىٰهَا﴿٧﴾
7በነፍስም ባስተካከላትም፤
فَأَلۡهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقۡوَىٰهَا﴿٨﴾
8አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡
قَدۡ أَفۡلَحَ مَن زَكَّىٰهَا﴿٩﴾
9(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡
وَقَدۡ خَابَ مَن دَسَّىٰهَا﴿١٠﴾
10(በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡
كَذَّبَتۡ ثَمُودُ بِطَغۡوَىٰهَآ﴿١١﴾
11ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡
إِذِ ٱنۢبَعَثَ أَشۡقَىٰهَا﴿١٢﴾
12ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡
فَقَالَ لَهُمۡ رَسُولُ ٱللَّهِ نَاقَةَ ٱللَّهِ وَسُقۡيَٰهَا﴿١٣﴾
13ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡
فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمۡدَمَ عَلَيۡهِمۡ رَبُّهُم بِذَنۢبِهِمۡ فَسَوَّىٰهَا﴿١٤﴾
14አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡
وَلَا يَخَافُ عُقۡبَٰهَا﴿١٥﴾
15ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አይፈራም፡፡