An-Nazi'at

النازعات

Those Who Drag Forth46 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلنَّٰزِعَٰتِ غَرۡقٗا﴿١

1በኃይል አውጪዎች በኾኑት፤

وَٱلنَّٰشِطَٰتِ نَشۡطٗا﴿٢

2በቀስታ መምዘዝንም መዘዦች በኾኑት፤

وَٱلسَّٰبِحَٰتِ سَبۡحٗا﴿٣

3መዋኘትም ዋኚዎች በኾኑት፤

فَٱلسَّٰبِقَٰتِ سَبۡقٗا﴿٤

4መቅደምንም ቀዳሚዎች በኾኑት፤

فَٱلۡمُدَبِّرَٰتِ أَمۡرٗا﴿٥

5ነገርንም አስተናባሪዎች በኾኑት (መላእክት) እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡

يَوۡمَ تَرۡجُفُ ٱلرَّاجِفَةُ﴿٦

6ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤

تَتۡبَعُهَا ٱلرَّادِفَةُ﴿٧

7ለጣቂይቱ የምትከተላት ስትኾን (ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡

قُلُوبٞ يَوۡمَئِذٖ وَاجِفَةٌ﴿٨

8በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው፡፡

أَبۡصَٰرُهَا خَٰشِعَةٞ﴿٩

9ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው፡፡

يَقُولُونَ أَءِنَّا لَمَرۡدُودُونَ فِي ٱلۡحَافِرَةِ﴿١٠

10«እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ኹነታ ተመላሾች ነን?» ይላሉ፡፡

أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمٗا نَّخِرَةٗ﴿١١

11«የበሰበሱ አጥንቶች በኾን ጊዜ (እንቀሰቀሳለን?)»

قَالُواْ تِلۡكَ إِذٗا كَرَّةٌ خَاسِرَةٞ﴿١٢

12«ይህቺ ያን ጊዜ ባለ ከሳራ መመለስ ናት» ይላሉ፡፡

فَإِنَّمَا هِيَ زَجۡرَةٞ وَٰحِدَةٞ﴿١٣

13እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡

فَإِذَا هُم بِٱلسَّاهِرَةِ﴿١٤

14ወዲያውኑም እነርሱ እንቅልፍ በሌለባት (ምድር) ላይ ይኾናሉ፡፡

هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ مُوسَىٰٓ﴿١٥

15የሙሳ ወሬ መጣልህን?

إِذۡ نَادَىٰهُ رَبُّهُۥ بِٱلۡوَادِ ٱلۡمُقَدَّسِ طُوًى﴿١٦

16ጌታው በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ በጠራው ጊዜ፤

ٱذۡهَبۡ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ إِنَّهُۥ طَغَىٰ﴿١٧

17ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡

فَقُلۡ هَل لَّكَ إِلَىٰٓ أَن تَزَكَّىٰ﴿١٨

18በለውም፡- «ወደ መጥራራትህ ላንተ (መንገድ) አለህን?»

وَأَهۡدِيَكَ إِلَىٰ رَبِّكَ فَتَخۡشَىٰ﴿١٩

19«ወደ ጌታህም ልመራህ ትፈራውም ዘንድ፤ (መንገድ አለህን?)» አለው፡፡

فَأَرَىٰهُ ٱلۡأٓيَةَ ٱلۡكُبۡرَىٰ﴿٢٠

20ታላቂቱንም ተዓምር አሳየው፡፡

فَكَذَّبَ وَعَصَىٰ﴿٢١

21አስተባበለም፤ አመጸም፡፡

ثُمَّ أَدۡبَرَ يَسۡعَىٰ﴿٢٢

22ከዚያም (ለማጥፋት) የሚተጋ ኾኖ ዞረ፡፡

فَحَشَرَ فَنَادَىٰ﴿٢٣

23(ሰራዊቶቹን) ሰበሰበም፤ ተጣራም፡፡

فَقَالَ أَنَا۠ رَبُّكُمُ ٱلۡأَعۡلَىٰ﴿٢٤

24አለም፡- «እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡»

فَأَخَذَهُ ٱللَّهُ نَكَالَ ٱلۡأٓخِرَةِ وَٱلۡأُولَىٰٓ﴿٢٥

25አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ (ቃል) ቅጣት ያዘው፡፡

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبۡرَةٗ لِّمَن يَخۡشَىٰٓ﴿٢٦

26በዚህ ውስጥ ለሚፈራ ሰው በእርግጥ መገምገሚያ አለበት፡፡

ءَأَنتُمۡ أَشَدُّ خَلۡقًا أَمِ ٱلسَّمَآءُۚ بَنَىٰهَا﴿٢٧

27ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት፡፡

رَفَعَ سَمۡكَهَا فَسَوَّىٰهَا﴿٢٨

28ከፍታዋን አጓነ፤ አስተካከላትም፡፡

وَأَغۡطَشَ لَيۡلَهَا وَأَخۡرَجَ ضُحَىٰهَا﴿٢٩

29ሌሊቷንም አጨለመ፡፡ ቀንዋንም ገለጸ፡፡

وَٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ ذَٰلِكَ دَحَىٰهَآ﴿٣٠

30ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡

أَخۡرَجَ مِنۡهَا مَآءَهَا وَمَرۡعَىٰهَا﴿٣١

31ውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡

وَٱلۡجِبَالَ أَرۡسَىٰهَا﴿٣٢

32ጋራዎችንም አደላደላቸው፡፡

مَتَٰعٗا لَّكُمۡ وَلِأَنۡعَٰمِكُمۡ﴿٣٣

33ለእናንተና ለእንስሶቻችሁ መጣቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን አደረገ)፡፡

فَإِذَا جَآءَتِ ٱلطَّآمَّةُ ٱلۡكُبۡرَىٰ﴿٣٤

34ታላቂቱም መዐት በመጣች ጊዜ፣

يَوۡمَ يَتَذَكَّرُ ٱلۡإِنسَٰنُ مَا سَعَىٰ﴿٣٥

35ሰው ሁሉ የሠራውን በሚያስታውስበት ቀን፣

وَبُرِّزَتِ ٱلۡجَحِيمُ لِمَن يَرَىٰ﴿٣٦

36ገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፣

فَأَمَّا مَن طَغَىٰ﴿٣٧

37የካደ ሰውማ፣

وَءَاثَرَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا﴿٣٨

38ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፣

فَإِنَّ ٱلۡجَحِيمَ هِيَ ٱلۡمَأۡوَىٰ﴿٣٩

39ገሀነም እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡

وَأَمَّا مَنۡ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ وَنَهَى ٱلنَّفۡسَ عَنِ ٱلۡهَوَىٰ﴿٤٠

40በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ

فَإِنَّ ٱلۡجَنَّةَ هِيَ ٱلۡمَأۡوَىٰ﴿٤١

41ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡

يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلسَّاعَةِ أَيَّانَ مُرۡسَىٰهَا﴿٤٢

42«ከሰዓቲቱ መቼ ነው መኾኛዋ?» ሲሉ ይጠይቁሃል፡፡

فِيمَ أَنتَ مِن ذِكۡرَىٰهَآ﴿٤٣

43አንተ እርሷን ከማስታወስ በምን ውስጥ ነህ?

إِلَىٰ رَبِّكَ مُنتَهَىٰهَآ﴿٤٤

44(የዕውቀት) መጨረሻዋ ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡

إِنَّمَآ أَنتَ مُنذِرُ مَن يَخۡشَىٰهَا﴿٤٥

45አንተ የሚፈራትን ሰው አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡

كَأَنَّهُمۡ يَوۡمَ يَرَوۡنَهَا لَمۡ يَلۡبَثُوٓاْ إِلَّا عَشِيَّةً أَوۡ ضُحَىٰهَا﴿٤٦

46እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፏዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡

RELATED SURAHS