Al-Fatiha

الفاتحة

The Opening7 ayahsMeccan

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ﴿١

1በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡[1]

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ﴿٢

2ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤

ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ﴿٣

3እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ

مَٰلِكِ يَوۡمِ ٱلدِّينِ﴿٤

4የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡

إِيَّاكَ نَعۡبُدُ وَإِيَّاكَ نَسۡتَعِينُ﴿٥

5አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡

ٱهۡدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ﴿٦

6ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡

صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنۡعَمۡتَ عَلَيۡهِمۡ غَيۡرِ ٱلۡمَغۡضُوبِ عَلَيۡهِمۡ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ﴿٧

7የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡ [1]

RELATED SURAHS