'Abasa

عبس

He Frowned42 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

عَبَسَ وَتَوَلَّىٰٓ﴿١

1ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡

أَن جَآءَهُ ٱلۡأَعۡمَىٰ﴿٢

2ዕውሩ ስለ መጣው፡፡

وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّهُۥ يَزَّكَّىٰٓ﴿٣

3ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡

أَوۡ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ ٱلذِّكۡرَىٰٓ﴿٤

4ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡

أَمَّا مَنِ ٱسۡتَغۡنَىٰ﴿٥

5የተብቃቃው ሰውማ፤

فَأَنتَ لَهُۥ تَصَدَّىٰ﴿٦

6አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡

وَمَا عَلَيۡكَ أَلَّا يَزَّكَّىٰ﴿٧

7ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡

وَأَمَّا مَن جَآءَكَ يَسۡعَىٰ﴿٨

8እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤

وَهُوَ يَخۡشَىٰ﴿٩

9እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤

فَأَنتَ عَنۡهُ تَلَهَّىٰ﴿١٠

10አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡

كَلَّآ إِنَّهَا تَذۡكِرَةٞ﴿١١

11ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡

فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ﴿١٢

12የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡

فِي صُحُفٖ مُّكَرَّمَةٖ﴿١٣

13በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡

مَّرۡفُوعَةٖ مُّطَهَّرَةِۭ﴿١٤

14ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡

بِأَيۡدِي سَفَرَةٖ﴿١٥

15በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡

كِرَامِۭ بَرَرَةٖ﴿١٦

16የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡

قُتِلَ ٱلۡإِنسَٰنُ مَآ أَكۡفَرَهُۥ﴿١٧

17ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው?

مِنۡ أَيِّ شَيۡءٍ خَلَقَهُۥ﴿١٨

18(ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?)

مِن نُّطۡفَةٍ خَلَقَهُۥ فَقَدَّرَهُۥ﴿١٩

19ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡

ثُمَّ ٱلسَّبِيلَ يَسَّرَهُۥ﴿٢٠

20ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡

ثُمَّ أَمَاتَهُۥ فَأَقۡبَرَهُۥ﴿٢١

21ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡

ثُمَّ إِذَا شَآءَ أَنشَرَهُۥ﴿٢٢

22ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡

كَلَّا لَمَّا يَقۡضِ مَآ أَمَرَهُۥ﴿٢٣

23በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡

فَلۡيَنظُرِ ٱلۡإِنسَٰنُ إِلَىٰ طَعَامِهِۦٓ﴿٢٤

24ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡

أَنَّا صَبَبۡنَا ٱلۡمَآءَ صَبّٗا﴿٢٥

25እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡

ثُمَّ شَقَقۡنَا ٱلۡأَرۡضَ شَقّٗا﴿٢٦

26ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤

فَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا حَبّٗا﴿٢٧

27በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤

وَعِنَبٗا وَقَضۡبٗا﴿٢٨

28ወይንንም፤ እርጥብ (ያበቀልን)፤

وَزَيۡتُونٗا وَنَخۡلٗا﴿٢٩

29የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤

وَحَدَآئِقَ غُلۡبٗا﴿٣٠

30ጭፍቆች አትክልቶችንም፤

وَفَٰكِهَةٗ وَأَبّٗا﴿٣١

31ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡

مَّتَٰعٗا لَّكُمۡ وَلِأَنۡعَٰمِكُمۡ﴿٣٢

32ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡

فَإِذَا جَآءَتِ ٱلصَّآخَّةُ﴿٣٣

33አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤

يَوۡمَ يَفِرُّ ٱلۡمَرۡءُ مِنۡ أَخِيهِ﴿٣٤

34ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤

وَأُمِّهِۦ وَأَبِيهِ﴿٣٥

35ከናቱም ካባቱም፤

وَصَٰحِبَتِهِۦ وَبَنِيهِ﴿٣٦

36ከሚስቱም ከልጁም፤

لِكُلِّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ يَوۡمَئِذٖ شَأۡنٞ يُغۡنِيهِ﴿٣٧

37ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡

وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ مُّسۡفِرَةٞ﴿٣٨

38ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤

ضَاحِكَةٞ مُّسۡتَبۡشِرَةٞ﴿٣٩

39ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡

وَوُجُوهٞ يَوۡمَئِذٍ عَلَيۡهَا غَبَرَةٞ﴿٤٠

40ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤

تَرۡهَقُهَا قَتَرَةٌ﴿٤١

41ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤

أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡكَفَرَةُ ٱلۡفَجَرَةُ﴿٤٢

42እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡

RELATED SURAHS