At-Takwir
التكوير
The Overthrowing • 29 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
إِذَا ٱلشَّمۡسُ كُوِّرَتۡ﴿١﴾
1ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلنُّجُومُ ٱنكَدَرَتۡ﴿٢﴾
2ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡجِبَالُ سُيِّرَتۡ﴿٣﴾
3ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡعِشَارُ عُطِّلَتۡ﴿٤﴾
4የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡوُحُوشُ حُشِرَتۡ﴿٥﴾
5እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡبِحَارُ سُجِّرَتۡ﴿٦﴾
6ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلنُّفُوسُ زُوِّجَتۡ﴿٧﴾
7ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡمَوۡءُۥدَةُ سُئِلَتۡ﴿٨﴾
8በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤
بِأَيِّ ذَنۢبٖ قُتِلَتۡ﴿٩﴾
9በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤
وَإِذَا ٱلصُّحُفُ نُشِرَتۡ﴿١٠﴾
10ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلسَّمَآءُ كُشِطَتۡ﴿١١﴾
11ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡجَحِيمُ سُعِّرَتۡ﴿١٢﴾
12ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡجَنَّةُ أُزۡلِفَتۡ﴿١٣﴾
13ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤
عَلِمَتۡ نَفۡسٞ مَّآ أَحۡضَرَتۡ﴿١٤﴾
14ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤
فَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلۡخُنَّسِ﴿١٥﴾
15ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡
ٱلۡجَوَارِ ٱلۡكُنَّسِ﴿١٦﴾
16ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡
وَٱلَّيۡلِ إِذَا عَسۡعَسَ﴿١٧﴾
17በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤
وَٱلصُّبۡحِ إِذَا تَنَفَّسَ﴿١٨﴾
18በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡
إِنَّهُۥ لَقَوۡلُ رَسُولٖ كَرِيمٖ﴿١٩﴾
19እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡
ذِي قُوَّةٍ عِندَ ذِي ٱلۡعَرۡشِ مَكِينٖ﴿٢٠﴾
20የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡
مُّطَاعٖ ثَمَّ أَمِينٖ﴿٢١﴾
21በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡
وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجۡنُونٖ﴿٢٢﴾
22ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡
وَلَقَدۡ رَءَاهُ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡمُبِينِ﴿٢٣﴾
23በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡
وَمَا هُوَ عَلَى ٱلۡغَيۡبِ بِضَنِينٖ﴿٢٤﴾
24እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡
وَمَا هُوَ بِقَوۡلِ شَيۡطَٰنٖ رَّجِيمٖ﴿٢٥﴾
25እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡
فَأَيۡنَ تَذۡهَبُونَ﴿٢٦﴾
26ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ?
إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ لِّلۡعَٰلَمِينَ﴿٢٧﴾
27እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَسۡتَقِيمَ﴿٢٨﴾
28ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡
وَمَا تَشَآءُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ﴿٢٩﴾
29የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡