Ar-Rahman

الرحمن

The Most Merciful78 ayahsMedinan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ٱلرَّحۡمَٰنُ﴿١

1አል-ረሕማን፤

عَلَّمَ ٱلۡقُرۡءَانَ﴿٢

2ቁርኣንን አስተማረ፡፡

خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ﴿٣

3ሰውን ፈጠረ፡፡

عَلَّمَهُ ٱلۡبَيَانَ﴿٤

4መናገርን አስተማረው፡፡

ٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ بِحُسۡبَانٖ﴿٥

5ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡

وَٱلنَّجۡمُ وَٱلشَّجَرُ يَسۡجُدَانِ﴿٦

6ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡

وَٱلسَّمَآءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ ٱلۡمِيزَانَ﴿٧

7ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡

أَلَّا تَطۡغَوۡاْ فِي ٱلۡمِيزَانِ﴿٨

8በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡

وَأَقِيمُواْ ٱلۡوَزۡنَ بِٱلۡقِسۡطِ وَلَا تُخۡسِرُواْ ٱلۡمِيزَانَ﴿٩

9መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡

وَٱلۡأَرۡضَ وَضَعَهَا لِلۡأَنَامِ﴿١٠

10ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡

فِيهَا فَٰكِهَةٞ وَٱلنَّخۡلُ ذَاتُ ٱلۡأَكۡمَامِ﴿١١

11በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡

وَٱلۡحَبُّ ذُو ٱلۡعَصۡفِ وَٱلرَّيۡحَانُ﴿١٢

12የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿١٣

13(ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِن صَلۡصَٰلٖ كَٱلۡفَخَّارِ﴿١٤

14ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡

وَخَلَقَ ٱلۡجَآنَّ مِن مَّارِجٖ مِّن نَّارٖ﴿١٥

15ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿١٦

16ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

رَبُّ ٱلۡمَشۡرِقَيۡنِ وَرَبُّ ٱلۡمَغۡرِبَيۡنِ﴿١٧

17የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿١٨

18ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

مَرَجَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ يَلۡتَقِيَانِ﴿١٩

19ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡

بَيۡنَهُمَا بَرۡزَخٞ لَّا يَبۡغِيَانِ﴿٢٠

20(እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٢١

21ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›

يَخۡرُجُ مِنۡهُمَا ٱللُّؤۡلُؤُ وَٱلۡمَرۡجَانُ﴿٢٢

22ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٢٣

23ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

وَلَهُ ٱلۡجَوَارِ ٱلۡمُنشَـَٔاتُ فِي ٱلۡبَحۡرِ كَٱلۡأَعۡلَٰمِ﴿٢٤

24እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٢٥

25ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

كُلُّ مَنۡ عَلَيۡهَا فَانٖ﴿٢٦

26በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡

وَيَبۡقَىٰ وَجۡهُ رَبِّكَ ذُو ٱلۡجَلَٰلِ وَٱلۡإِكۡرَامِ﴿٢٧

27የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٢٨

28ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

يَسۡـَٔلُهُۥ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ كُلَّ يَوۡمٍ هُوَ فِي شَأۡنٖ﴿٢٩

29በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٣٠

30ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›

سَنَفۡرُغُ لَكُمۡ أَيُّهَ ٱلثَّقَلَانِ﴿٣١

31እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٣٢

32ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ إِنِ ٱسۡتَطَعۡتُمۡ أَن تَنفُذُواْ مِنۡ أَقۡطَارِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ فَٱنفُذُواْۚ لَا تَنفُذُونَ إِلَّا بِسُلۡطَٰنٖ﴿٣٣

33የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም)

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٣٤

34ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

يُرۡسَلُ عَلَيۡكُمَا شُوَاظٞ مِّن نَّارٖ وَنُحَاسٞ فَلَا تَنتَصِرَانِ﴿٣٥

35በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٣٦

36ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

فَإِذَا ٱنشَقَّتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ وَرۡدَةٗ كَٱلدِّهَانِ﴿٣٧

37ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٣٨

38ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

فَيَوۡمَئِذٖ لَّا يُسۡـَٔلُ عَن ذَنۢبِهِۦٓ إِنسٞ وَلَا جَآنّٞ﴿٣٩

39በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٤٠

40ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

يُعۡرَفُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ بِسِيمَٰهُمۡ فَيُؤۡخَذُ بِٱلنَّوَٰصِي وَٱلۡأَقۡدَامِ﴿٤١

41ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٤٢

42ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡

هَٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِي يُكَذِّبُ بِهَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ﴿٤٣

43ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡

يَطُوفُونَ بَيۡنَهَا وَبَيۡنَ حَمِيمٍ ءَانٖ﴿٤٤

44በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٤٥

45ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

وَلِمَنۡ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ جَنَّتَانِ﴿٤٦

46በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٤٧

47ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

ذَوَاتَآ أَفۡنَانٖ﴿٤٨

48የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٤٩

49ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

فِيهِمَا عَيۡنَانِ تَجۡرِيَانِ﴿٥٠

50በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٥١

51ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

فِيهِمَا مِن كُلِّ فَٰكِهَةٖ زَوۡجَانِ﴿٥٢

52በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٥٣

53ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ فُرُشِۭ بَطَآئِنُهَا مِنۡ إِسۡتَبۡرَقٖۚ وَجَنَى ٱلۡجَنَّتَيۡنِ دَانٖ﴿٥٤

54የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٥٥

55ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

فِيهِنَّ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ لَمۡ يَطۡمِثۡهُنَّ إِنسٞ قَبۡلَهُمۡ وَلَا جَآنّٞ﴿٥٦

56በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٥٧

57ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

كَأَنَّهُنَّ ٱلۡيَاقُوتُ وَٱلۡمَرۡجَانُ﴿٥٨

58ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٥٩

59ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

هَلۡ جَزَآءُ ٱلۡإِحۡسَٰنِ إِلَّا ٱلۡإِحۡسَٰنُ﴿٦٠

60የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٦١

61ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

وَمِن دُونِهِمَا جَنَّتَانِ﴿٦٢

62ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٦٣

63ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?›

مُدۡهَآمَّتَانِ﴿٦٤

64ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٦٥

65ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

فِيهِمَا عَيۡنَانِ نَضَّاخَتَانِ﴿٦٦

66በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٦٧

67ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

فِيهِمَا فَٰكِهَةٞ وَنَخۡلٞ وَرُمَّانٞ﴿٦٨

68በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٦٩

69ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

فِيهِنَّ خَيۡرَٰتٌ حِسَانٞ﴿٧٠

70በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٧١

71ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

حُورٞ مَّقۡصُورَٰتٞ فِي ٱلۡخِيَامِ﴿٧٢

72በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٧٣

73ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

لَمۡ يَطۡمِثۡهُنَّ إِنسٞ قَبۡلَهُمۡ وَلَا جَآنّٞ﴿٧٤

74ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٧٥

75ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ?

مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ رَفۡرَفٍ خُضۡرٖ وَعَبۡقَرِيٍّ حِسَانٖ﴿٧٦

76በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ﴿٧٧

77ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

تَبَٰرَكَ ٱسۡمُ رَبِّكَ ذِي ٱلۡجَلَٰلِ وَٱلۡإِكۡرَامِ﴿٧٨

78የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡

RELATED SURAHS