إِذَا وَقَعَتِ ٱلۡوَاقِعَةُ﴿١﴾
1መከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡
لَيۡسَ لِوَقۡعَتِهَا كَاذِبَةٌ﴿٢﴾
2ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡
خَافِضَةٞ رَّافِعَةٌ﴿٣﴾
3ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡
إِذَا رُجَّتِ ٱلۡأَرۡضُ رَجّٗا﴿٤﴾
4ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡
وَبُسَّتِ ٱلۡجِبَالُ بَسّٗا﴿٥﴾
5ተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡
فَكَانَتۡ هَبَآءٗ مُّنۢبَثّٗا﴿٦﴾
6የተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ
وَكُنتُمۡ أَزۡوَٰجٗا ثَلَٰثَةٗ﴿٧﴾
7ሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡
فَأَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ﴿٨﴾
8የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ﴿٩﴾
9የግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلسَّٰبِقُونَ﴿١٠﴾
10(ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلۡمُقَرَّبُونَ﴿١١﴾
11እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡
فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ﴿١٢﴾
12በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡
ثُلَّةٞ مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿١٣﴾
13ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
وَقَلِيلٞ مِّنَ ٱلۡأٓخِرِينَ﴿١٤﴾
14ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡
عَلَىٰ سُرُرٖ مَّوۡضُونَةٖ﴿١٥﴾
15በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡
مُّتَّكِـِٔينَ عَلَيۡهَا مُتَقَٰبِلِينَ﴿١٦﴾
16በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡
يَطُوفُ عَلَيۡهِمۡ وِلۡدَٰنٞ مُّخَلَّدُونَ﴿١٧﴾
17በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡
بِأَكۡوَابٖ وَأَبَارِيقَ وَكَأۡسٖ مِّن مَّعِينٖ﴿١٨﴾
18ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡
لَّا يُصَدَّعُونَ عَنۡهَا وَلَا يُنزِفُونَ﴿١٩﴾
19ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡
وَفَٰكِهَةٖ مِّمَّا يَتَخَيَّرُونَ﴿٢٠﴾
20ከሚመርጡትም ዓይነት እሸቶች፡፡
وَلَحۡمِ طَيۡرٖ مِّمَّا يَشۡتَهُونَ﴿٢١﴾
21ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡
وَحُورٌ عِينٞ﴿٢٢﴾
22ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡
كَأَمۡثَٰلِ ٱللُّؤۡلُوِٕ ٱلۡمَكۡنُونِ﴿٢٣﴾
23ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡
جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ﴿٢٤﴾
24በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡
لَا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوٗا وَلَا تَأۡثِيمًا﴿٢٥﴾
25በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡
إِلَّا قِيلٗا سَلَٰمٗا سَلَٰمٗا﴿٢٦﴾
26ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡
وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡيَمِينِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡيَمِينِ﴿٢٧﴾
27የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!
فِي سِدۡرٖ مَّخۡضُودٖ﴿٢٨﴾
28በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡
وَطَلۡحٖ مَّنضُودٖ﴿٢٩﴾
29(ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡
وَظِلّٖ مَّمۡدُودٖ﴿٣٠﴾
30በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡
وَمَآءٖ مَّسۡكُوبٖ﴿٣١﴾
31በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡
وَفَٰكِهَةٖ كَثِيرَةٖ﴿٣٢﴾
32ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡
لَّا مَقۡطُوعَةٖ وَلَا مَمۡنُوعَةٖ﴿٣٣﴾
33የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡
وَفُرُشٖ مَّرۡفُوعَةٍ﴿٣٤﴾
34ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡
إِنَّآ أَنشَأۡنَٰهُنَّ إِنشَآءٗ﴿٣٥﴾
35እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡
فَجَعَلۡنَٰهُنَّ أَبۡكَارًا﴿٣٦﴾
36ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡
عُرُبًا أَتۡرَابٗا﴿٣٧﴾
37ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡
لِّأَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ﴿٣٨﴾
38ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡
ثُلَّةٞ مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿٣٩﴾
39ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
وَثُلَّةٞ مِّنَ ٱلۡأٓخِرِينَ﴿٤٠﴾
40ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
وَأَصۡحَٰبُ ٱلشِّمَالِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلشِّمَالِ﴿٤١﴾
41የግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡
فِي سَمُومٖ وَحَمِيمٖ﴿٤٢﴾
42በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡
وَظِلّٖ مِّن يَحۡمُومٖ﴿٤٣﴾
43ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡
لَّا بَارِدٖ وَلَا كَرِيمٍ﴿٤٤﴾
44ቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡
إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَبۡلَ ذَٰلِكَ مُتۡرَفِينَ﴿٤٥﴾
45እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡
وَكَانُواْ يُصِرُّونَ عَلَى ٱلۡحِنثِ ٱلۡعَظِيمِ﴿٤٦﴾
46በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡
وَكَانُواْ يَقُولُونَ أَئِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ﴿٤٧﴾
47ይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን?
أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ﴿٤٨﴾
48«የፊተኞቹ አባቶቻችንም?»
قُلۡ إِنَّ ٱلۡأَوَّلِينَ وَٱلۡأٓخِرِينَ﴿٤٩﴾
49በላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡
لَمَجۡمُوعُونَ إِلَىٰ مِيقَٰتِ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ﴿٥٠﴾
50«በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡
ثُمَّ إِنَّكُمۡ أَيُّهَا ٱلضَّآلُّونَ ٱلۡمُكَذِّبُونَ﴿٥١﴾
51«ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ!
لَأٓكِلُونَ مِن شَجَرٖ مِّن زَقُّومٖ﴿٥٢﴾
52« ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡
فَمَالِـُٔونَ مِنۡهَا ٱلۡبُطُونَ﴿٥٣﴾
53«ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡
فَشَٰرِبُونَ عَلَيۡهِ مِنَ ٱلۡحَمِيمِ﴿٥٤﴾
54«በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡
فَشَٰرِبُونَ شُرۡبَ ٱلۡهِيمِ﴿٥٥﴾
55«የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡»
هَٰذَا نُزُلُهُمۡ يَوۡمَ ٱلدِّينِ﴿٥٦﴾
56ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡
نَحۡنُ خَلَقۡنَٰكُمۡ فَلَوۡلَا تُصَدِّقُونَ﴿٥٧﴾
57እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?
أَفَرَءَيۡتُم مَّا تُمۡنُونَ﴿٥٨﴾
58(በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን?
ءَأَنتُمۡ تَخۡلُقُونَهُۥٓ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡخَٰلِقُونَ﴿٥٩﴾
59እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን?
نَحۡنُ قَدَّرۡنَا بَيۡنَكُمُ ٱلۡمَوۡتَ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ﴿٦٠﴾
60እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ أَمۡثَٰلَكُمۡ وَنُنشِئَكُمۡ فِي مَا لَا تَعۡلَمُونَ﴿٦١﴾
61ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡
وَلَقَدۡ عَلِمۡتُمُ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأُولَىٰ فَلَوۡلَا تَذَكَّرُونَ﴿٦٢﴾
62የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን?
أَفَرَءَيۡتُم مَّا تَحۡرُثُونَ﴿٦٣﴾
63የምትዘሩትንም አያችሁን?
ءَأَنتُمۡ تَزۡرَعُونَهُۥٓ أَمۡ نَحۡنُ ٱلزَّٰرِعُونَ﴿٦٤﴾
64እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?
لَوۡ نَشَآءُ لَجَعَلۡنَٰهُ حُطَٰمٗا فَظَلۡتُمۡ تَفَكَّهُونَ﴿٦٥﴾
65ብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡
إِنَّا لَمُغۡرَمُونَ﴿٦٦﴾
66«እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡
بَلۡ نَحۡنُ مَحۡرُومُونَ﴿٦٧﴾
67«በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡
أَفَرَءَيۡتُمُ ٱلۡمَآءَ ٱلَّذِي تَشۡرَبُونَ﴿٦٨﴾
68ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን?
ءَأَنتُمۡ أَنزَلۡتُمُوهُ مِنَ ٱلۡمُزۡنِ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡمُنزِلُونَ﴿٦٩﴾
69እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?
لَوۡ نَشَآءُ جَعَلۡنَٰهُ أُجَاجٗا فَلَوۡلَا تَشۡكُرُونَ﴿٧٠﴾
70ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን?
أَفَرَءَيۡتُمُ ٱلنَّارَ ٱلَّتِي تُورُونَ﴿٧١﴾
71ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?
ءَأَنتُمۡ أَنشَأۡتُمۡ شَجَرَتَهَآ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡمُنشِـُٔونَ﴿٧٢﴾
72እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን?
نَحۡنُ جَعَلۡنَٰهَا تَذۡكِرَةٗ وَمَتَٰعٗا لِّلۡمُقۡوِينَ﴿٧٣﴾
73እኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡
فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ﴿٧٤﴾
74የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡
۞ فَلَآ أُقۡسِمُ بِمَوَٰقِعِ ٱلنُّجُومِ﴿٧٥﴾
75በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡
وَإِنَّهُۥ لَقَسَمٞ لَّوۡ تَعۡلَمُونَ عَظِيمٌ﴿٧٦﴾
76እርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡
إِنَّهُۥ لَقُرۡءَانٞ كَرِيمٞ﴿٧٧﴾
77እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
فِي كِتَٰبٖ مَّكۡنُونٖ﴿٧٨﴾
78በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
لَّا يَمَسُّهُۥٓ إِلَّا ٱلۡمُطَهَّرُونَ﴿٧٩﴾
79የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡
تَنزِيلٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ﴿٨٠﴾
80ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
أَفَبِهَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ أَنتُم مُّدۡهِنُونَ﴿٨١﴾
81በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?
وَتَجۡعَلُونَ رِزۡقَكُمۡ أَنَّكُمۡ تُكَذِّبُونَ﴿٨٢﴾
82ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን?
فَلَوۡلَآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلۡحُلۡقُومَ﴿٨٣﴾
83(ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡
وَأَنتُمۡ حِينَئِذٖ تَنظُرُونَ﴿٨٤﴾
84እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡
وَنَحۡنُ أَقۡرَبُ إِلَيۡهِ مِنكُمۡ وَلَٰكِن لَّا تُبۡصِرُونَ﴿٨٥﴾
85እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡
فَلَوۡلَآ إِن كُنتُمۡ غَيۡرَ مَدِينِينَ﴿٨٦﴾
86የማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡
تَرۡجِعُونَهَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ﴿٨٧﴾
87እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡
فَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ﴿٨٨﴾
88(ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡
فَرَوۡحٞ وَرَيۡحَانٞ وَجَنَّتُ نَعِيمٖ﴿٨٩﴾
89(ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡
وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ﴿٩٠﴾
90ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡
فَسَلَٰمٞ لَّكَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ﴿٩١﴾
91ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡
وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡمُكَذِّبِينَ ٱلضَّآلِّينَ﴿٩٢﴾
92ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡
فَنُزُلٞ مِّنۡ حَمِيمٖ﴿٩٣﴾
93ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡
وَتَصۡلِيَةُ جَحِيمٍ﴿٩٤﴾
94በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ حَقُّ ٱلۡيَقِينِ﴿٩٥﴾
95ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡
فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ﴿٩٦﴾
96የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡