Al-Infitar
الانفطار
The Cleaving • 19 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنفَطَرَتۡ﴿١﴾
1ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡكَوَاكِبُ ٱنتَثَرَتۡ﴿٢﴾
2ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡبِحَارُ فُجِّرَتۡ﴿٣﴾
3ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡقُبُورُ بُعۡثِرَتۡ﴿٤﴾
4መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤
عَلِمَتۡ نَفۡسٞ مَّا قَدَّمَتۡ وَأَخَّرَتۡ﴿٥﴾
5ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡإِنسَٰنُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ ٱلۡكَرِيمِ﴿٦﴾
6አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?
ٱلَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّىٰكَ فَعَدَلَكَ﴿٧﴾
7በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡
فِيٓ أَيِّ صُورَةٖ مَّا شَآءَ رَكَّبَكَ﴿٨﴾
8በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡
كَلَّا بَلۡ تُكَذِّبُونَ بِٱلدِّينِ﴿٩﴾
9ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡
وَإِنَّ عَلَيۡكُمۡ لَحَٰفِظِينَ﴿١٠﴾
10በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤
كِرَامٗا كَٰتِبِينَ﴿١١﴾
11የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡
يَعۡلَمُونَ مَا تَفۡعَلُونَ﴿١٢﴾
12የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡
إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمٖ﴿١٣﴾
13እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡
وَإِنَّ ٱلۡفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٖ﴿١٤﴾
14ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡
يَصۡلَوۡنَهَا يَوۡمَ ٱلدِّينِ﴿١٥﴾
15በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡
وَمَا هُمۡ عَنۡهَا بِغَآئِبِينَ﴿١٦﴾
16እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ﴿١٧﴾
17የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
ثُمَّ مَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ﴿١٨﴾
18ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
يَوۡمَ لَا تَمۡلِكُ نَفۡسٞ لِّنَفۡسٖ شَيۡـٔٗاۖ وَٱلۡأَمۡرُ يَوۡمَئِذٖ لِّلَّهِ﴿١٩﴾
19(እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡