Al-Mutaffifin

المطففين

The Defrauders36 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَيۡلٞ لِّلۡمُطَفِّفِينَ﴿١

1ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡

ٱلَّذِينَ إِذَا ٱكۡتَالُواْ عَلَى ٱلنَّاسِ يَسۡتَوۡفُونَ﴿٢

2ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡

وَإِذَا كَالُوهُمۡ أَو وَّزَنُوهُمۡ يُخۡسِرُونَ﴿٣

3ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡

أَلَا يَظُنُّ أُوْلَٰٓئِكَ أَنَّهُم مَّبۡعُوثُونَ﴿٤

4እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን?

لِيَوۡمٍ عَظِيمٖ﴿٥

5በታላቁ ቀን፡፡

يَوۡمَ يَقُومُ ٱلنَّاسُ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ﴿٦

6ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٖ﴿٧

7በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سِجِّينٞ﴿٨

8ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?

كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ﴿٩

9የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡

وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿١٠

10ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

ٱلَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ﴿١١

11ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡

وَمَا يُكَذِّبُ بِهِۦٓ إِلَّا كُلُّ مُعۡتَدٍ أَثِيمٍ﴿١٢

12በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡

إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿١٣

13አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡

كَلَّاۖ بَلۡۜ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ﴿١٤

14ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡

كَلَّآ إِنَّهُمۡ عَن رَّبِّهِمۡ يَوۡمَئِذٖ لَّمَحۡجُوبُونَ﴿١٥

15ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡

ثُمَّ إِنَّهُمۡ لَصَالُواْ ٱلۡجَحِيمِ﴿١٦

16ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡

ثُمَّ يُقَالُ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ﴿١٧

17ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡأَبۡرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ﴿١٨

18በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا عِلِّيُّونَ﴿١٩

19ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?

كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ﴿٢٠

20የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡

يَشۡهَدُهُ ٱلۡمُقَرَّبُونَ﴿٢١

21ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡

إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمٍ﴿٢٢

22እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡

عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ﴿٢٣

23በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡

تَعۡرِفُ فِي وُجُوهِهِمۡ نَضۡرَةَ ٱلنَّعِيمِ﴿٢٤

24በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡

يُسۡقَوۡنَ مِن رَّحِيقٖ مَّخۡتُومٍ﴿٢٥

25ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡

خِتَٰمُهُۥ مِسۡكٞۚ وَفِي ذَٰلِكَ فَلۡيَتَنَافَسِ ٱلۡمُتَنَٰفِسُونَ﴿٢٦

26ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡

وَمِزَاجُهُۥ مِن تَسۡنِيمٍ﴿٢٧

27መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡

عَيۡنٗا يَشۡرَبُ بِهَا ٱلۡمُقَرَّبُونَ﴿٢٨

28ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡

إِنَّ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْ كَانُواْ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ يَضۡحَكُونَ﴿٢٩

29እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡

وَإِذَا مَرُّواْ بِهِمۡ يَتَغَامَزُونَ﴿٣٠

30በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡

وَإِذَا ٱنقَلَبُوٓاْ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمُ ٱنقَلَبُواْ فَكِهِينَ﴿٣١

31ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡

وَإِذَا رَأَوۡهُمۡ قَالُوٓاْ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَضَآلُّونَ﴿٣٢

32ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡

وَمَآ أُرۡسِلُواْ عَلَيۡهِمۡ حَٰفِظِينَ﴿٣٣

33በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡

فَٱلۡيَوۡمَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنَ ٱلۡكُفَّارِ يَضۡحَكُونَ﴿٣٤

34ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡

عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ﴿٣٥

35በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡

هَلۡ ثُوِّبَ ٱلۡكُفَّارُ مَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ﴿٣٦

36ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡

RELATED SURAHS