Al-Inshiqaq

الانشقاق

The Splitting Open25 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنشَقَّتۡ﴿١

1ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤

وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ﴿٢

2ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤

وَإِذَا ٱلۡأَرۡضُ مُدَّتۡ﴿٣

3ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤

وَأَلۡقَتۡ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتۡ﴿٤

4በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤

وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ﴿٥

5ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡإِنسَٰنُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدۡحٗا فَمُلَٰقِيهِ﴿٦

6አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡

فَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ﴿٧

7መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤

فَسَوۡفَ يُحَاسَبُ حِسَابٗا يَسِيرٗا﴿٨

8በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡

وَيَنقَلِبُ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورٗا﴿٩

9ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡

وَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ وَرَآءَ ظَهۡرِهِۦ﴿١٠

10መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤

فَسَوۡفَ يَدۡعُواْ ثُبُورٗا﴿١١

11(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡

وَيَصۡلَىٰ سَعِيرًا﴿١٢

12የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡

إِنَّهُۥ كَانَ فِيٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورًا﴿١٣

13እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡

إِنَّهُۥ ظَنَّ أَن لَّن يَحُورَ﴿١٤

14እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡

بَلَىٰٓۚ إِنَّ رَبَّهُۥ كَانَ بِهِۦ بَصِيرٗا﴿١٥

15አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡

فَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلشَّفَقِ﴿١٦

16(አትካዱ)፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡

وَٱلَّيۡلِ وَمَا وَسَقَ﴿١٧

17በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤

وَٱلۡقَمَرِ إِذَا ٱتَّسَقَ﴿١٨

18በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡

لَتَرۡكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٖ﴿١٩

19ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡

فَمَا لَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ﴿٢٠

20የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?

وَإِذَا قُرِئَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقُرۡءَانُ لَا يَسۡجُدُونَۤ۩﴿٢١

21በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?) [1]

بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُكَذِّبُونَ﴿٢٢

22በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡

وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يُوعُونَ﴿٢٣

23አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡

فَبَشِّرۡهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ﴿٢٤

24በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡

إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونِۭ﴿٢٥

25ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡

RELATED SURAHS