Al-Buruj

البروج

The Great Stars22 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلۡبُرُوجِ﴿١

1የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡

وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡمَوۡعُودِ﴿٢

2በተቀጠረው ቀንም፤

وَشَاهِدٖ وَمَشۡهُودٖ﴿٣

3በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡

قُتِلَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡأُخۡدُودِ﴿٤

4የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡

ٱلنَّارِ ذَاتِ ٱلۡوَقُودِ﴿٥

5የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡

إِذۡ هُمۡ عَلَيۡهَا قُعُودٞ﴿٦

6እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡

وَهُمۡ عَلَىٰ مَا يَفۡعَلُونَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ شُهُودٞ﴿٧

7እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡

وَمَا نَقَمُواْ مِنۡهُمۡ إِلَّآ أَن يُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَمِيدِ﴿٨

8ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡

ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ﴿٩

9በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡

إِنَّ ٱلَّذِينَ فَتَنُواْ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ ثُمَّ لَمۡ يَتُوبُواْ فَلَهُمۡ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمۡ عَذَابُ ٱلۡحَرِيقِ﴿١٠

10እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ جَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡكَبِيرُ﴿١١

11እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡

إِنَّ بَطۡشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ﴿١٢

12የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡

إِنَّهُۥ هُوَ يُبۡدِئُ وَيُعِيدُ﴿١٣

13እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡

وَهُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلۡوَدُودُ﴿١٤

14እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡

ذُو ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡمَجِيدُ﴿١٥

15የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡

فَعَّالٞ لِّمَا يُرِيدُ﴿١٦

16የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡

هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلۡجُنُودِ﴿١٧

17የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን?

فِرۡعَوۡنَ وَثَمُودَ﴿١٨

18የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡

بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي تَكۡذِيبٖ﴿١٩

19በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡

وَٱللَّهُ مِن وَرَآئِهِم مُّحِيطُۢ﴿٢٠

20አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡

بَلۡ هُوَ قُرۡءَانٞ مَّجِيدٞ﴿٢١

21ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡

فِي لَوۡحٖ مَّحۡفُوظِۭ﴿٢٢

22የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡

RELATED SURAHS