At-Tariq
الطارق
The Night Comer • 17 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلسَّمَآءِ وَٱلطَّارِقِ﴿١﴾
1በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلطَّارِقُ﴿٢﴾
2የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
ٱلنَّجۡمُ ٱلثَّاقِبُ﴿٣﴾
3ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡
إِن كُلُّ نَفۡسٖ لَّمَّا عَلَيۡهَا حَافِظٞ﴿٤﴾
4ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
فَلۡيَنظُرِ ٱلۡإِنسَٰنُ مِمَّ خُلِقَ﴿٥﴾
5ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡
خُلِقَ مِن مَّآءٖ دَافِقٖ﴿٦﴾
6ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡
يَخۡرُجُ مِنۢ بَيۡنِ ٱلصُّلۡبِ وَٱلتَّرَآئِبِ﴿٧﴾
7ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡
إِنَّهُۥ عَلَىٰ رَجۡعِهِۦ لَقَادِرٞ﴿٨﴾
8እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡
يَوۡمَ تُبۡلَى ٱلسَّرَآئِرُ﴿٩﴾
9ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡
فَمَا لَهُۥ مِن قُوَّةٖ وَلَا نَاصِرٖ﴿١٠﴾
10ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡
وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلرَّجۡعِ﴿١١﴾
11የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡
وَٱلۡأَرۡضِ ذَاتِ ٱلصَّدۡعِ﴿١٢﴾
12(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤
إِنَّهُۥ لَقَوۡلٞ فَصۡلٞ﴿١٣﴾
13እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡
وَمَا هُوَ بِٱلۡهَزۡلِ﴿١٤﴾
14እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡
إِنَّهُمۡ يَكِيدُونَ كَيۡدٗا﴿١٥﴾
15እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡
وَأَكِيدُ كَيۡدٗا﴿١٦﴾
16(እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡
فَمَهِّلِ ٱلۡكَٰفِرِينَ أَمۡهِلۡهُمۡ رُوَيۡدَۢا﴿١٧﴾
17ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡