As-Saffat

الصافات

Those Ranged in Ranks182 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلصَّٰٓفَّٰتِ صَفّٗا﴿١

1መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡

فَٱلزَّٰجِرَٰتِ زَجۡرٗا﴿٢

2መገሠጽንም በሚገሥጹት፤

فَٱلتَّٰلِيَٰتِ ذِكۡرًا﴿٣

3ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡

إِنَّ إِلَٰهَكُمۡ لَوَٰحِدٞ﴿٤

4አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡

رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَرَبُّ ٱلۡمَشَٰرِقِ﴿٥

5የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡

إِنَّا زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِزِينَةٍ ٱلۡكَوَاكِبِ﴿٦

6እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡

وَحِفۡظٗا مِّن كُلِّ شَيۡطَٰنٖ مَّارِدٖ﴿٧

7አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡

لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى ٱلۡمَلَإِ ٱلۡأَعۡلَىٰ وَيُقۡذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٖ﴿٨

8ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡

دُحُورٗاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ وَاصِبٌ﴿٩

9የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡

إِلَّا مَنۡ خَطِفَ ٱلۡخَطۡفَةَ فَأَتۡبَعَهُۥ شِهَابٞ ثَاقِبٞ﴿١٠

10ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡

فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَهُمۡ أَشَدُّ خَلۡقًا أَم مَّنۡ خَلَقۡنَآۚ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّن طِينٖ لَّازِبِۭ﴿١١

11ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡

بَلۡ عَجِبۡتَ وَيَسۡخَرُونَ﴿١٢

12ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡

وَإِذَا ذُكِّرُواْ لَا يَذۡكُرُونَ﴿١٣

13በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡

وَإِذَا رَأَوۡاْ ءَايَةٗ يَسۡتَسۡخِرُونَ﴿١٤

14ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡

وَقَالُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٌ﴿١٥

15ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ﴿١٦

16«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?

أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ﴿١٧

17«የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡

قُلۡ نَعَمۡ وَأَنتُمۡ دَٰخِرُونَ﴿١٨

18«አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡

فَإِنَّمَا هِيَ زَجۡرَةٞ وَٰحِدَةٞ فَإِذَا هُمۡ يَنظُرُونَ﴿١٩

19እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡

وَقَالُواْ يَٰوَيۡلَنَا هَٰذَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ﴿٢٠

20«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡

هَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِ ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ﴿٢١

21«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡

۞ ٱحۡشُرُواْ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ وَأَزۡوَٰجَهُمۡ وَمَا كَانُواْ يَعۡبُدُونَ﴿٢٢

22(ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡

مِن دُونِ ٱللَّهِ فَٱهۡدُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلۡجَحِيمِ﴿٢٣

23«ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡

وَقِفُوهُمۡۖ إِنَّهُم مَّسۡـُٔولُونَ﴿٢٤

24«አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡

مَا لَكُمۡ لَا تَنَاصَرُونَ﴿٢٥

25(ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡

بَلۡ هُمُ ٱلۡيَوۡمَ مُسۡتَسۡلِمُونَ﴿٢٦

26በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡

وَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ﴿٢٧

27የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡

قَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَأۡتُونَنَا عَنِ ٱلۡيَمِينِ﴿٢٨

28(ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡

قَالُواْ بَل لَّمۡ تَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ﴿٢٩

29(አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡

وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيۡكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭۖ بَلۡ كُنتُمۡ قَوۡمٗا طَٰغِينَ﴿٣٠

30«ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡

فَحَقَّ عَلَيۡنَا قَوۡلُ رَبِّنَآۖ إِنَّا لَذَآئِقُونَ﴿٣١

31«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡

فَأَغۡوَيۡنَٰكُمۡ إِنَّا كُنَّا غَٰوِينَ﴿٣٢

32«ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡

فَإِنَّهُمۡ يَوۡمَئِذٖ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ﴿٣٣

33ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ተጋሪዎች ናቸው፡፡

إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ﴿٣٤

34እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡

إِنَّهُمۡ كَانُوٓاْ إِذَا قِيلَ لَهُمۡ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ يَسۡتَكۡبِرُونَ﴿٣٥

35እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡

وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوٓاْ ءَالِهَتِنَا لِشَاعِرٖ مَّجۡنُونِۭ﴿٣٦

36እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡

بَلۡ جَآءَ بِٱلۡحَقِّ وَصَدَّقَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ﴿٣٧

37አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡

إِنَّكُمۡ لَذَآئِقُواْ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَلِيمِ﴿٣٨

38እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡

وَمَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ﴿٣٩

39ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡

إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ﴿٤٠

40ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡

أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ رِزۡقٞ مَّعۡلُومٞ﴿٤١

41እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡

فَوَٰكِهُ وَهُم مُّكۡرَمُونَ﴿٤٢

42ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤

فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ﴿٤٣

43በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡

عَلَىٰ سُرُرٖ مُّتَقَٰبِلِينَ﴿٤٤

44ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡

يُطَافُ عَلَيۡهِم بِكَأۡسٖ مِّن مَّعِينِۭ﴿٤٥

45ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡

بَيۡضَآءَ لَذَّةٖ لِّلشَّٰرِبِينَ﴿٤٦

46ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡

لَا فِيهَا غَوۡلٞ وَلَا هُمۡ عَنۡهَا يُنزَفُونَ﴿٤٧

47በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡

وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ عِينٞ﴿٤٨

48እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡

كَأَنَّهُنَّ بَيۡضٞ مَّكۡنُونٞ﴿٤٩

49እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡

فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ﴿٥٠

50የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡

قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٞ﴿٥١

51ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡

يَقُولُ أَءِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُصَدِّقِينَ﴿٥٢

52«በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡

أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَدِينُونَ﴿٥٣

53«በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡

قَالَ هَلۡ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ﴿٥٤

54እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡

فَٱطَّلَعَ فَرَءَاهُ فِي سَوَآءِ ٱلۡجَحِيمِ﴿٥٥

55ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡

قَالَ تَٱللَّهِ إِن كِدتَّ لَتُرۡدِينِ﴿٥٦

56ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡

وَلَوۡلَا نِعۡمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ ٱلۡمُحۡضَرِينَ﴿٥٧

57«የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡»

أَفَمَا نَحۡنُ بِمَيِّتِينَ﴿٥٨

58(የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን?

إِلَّا مَوۡتَتَنَا ٱلۡأُولَىٰ وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ﴿٥٩

59«የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡

إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ﴿٦٠

60ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡

لِمِثۡلِ هَٰذَا فَلۡيَعۡمَلِ ٱلۡعَٰمِلُونَ﴿٦١

61ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡

أَذَٰلِكَ خَيۡرٞ نُّزُلًا أَمۡ شَجَرَةُ ٱلزَّقُّومِ﴿٦٢

62በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?

إِنَّا جَعَلۡنَٰهَا فِتۡنَةٗ لِّلظَّٰلِمِينَ﴿٦٣

63እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡

إِنَّهَا شَجَرَةٞ تَخۡرُجُ فِيٓ أَصۡلِ ٱلۡجَحِيمِ﴿٦٤

64እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡

طَلۡعُهَا كَأَنَّهُۥ رُءُوسُ ٱلشَّيَٰطِينِ﴿٦٥

65እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡

فَإِنَّهُمۡ لَأٓكِلُونَ مِنۡهَا فَمَالِـُٔونَ مِنۡهَا ٱلۡبُطُونَ﴿٦٦

66እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡

ثُمَّ إِنَّ لَهُمۡ عَلَيۡهَا لَشَوۡبٗا مِّنۡ حَمِيمٖ﴿٦٧

67ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡

ثُمَّ إِنَّ مَرۡجِعَهُمۡ لَإِلَى ٱلۡجَحِيمِ﴿٦٨

68ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡

إِنَّهُمۡ أَلۡفَوۡاْ ءَابَآءَهُمۡ ضَآلِّينَ﴿٦٩

69እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡

فَهُمۡ عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِمۡ يُهۡرَعُونَ﴿٧٠

70እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡

وَلَقَدۡ ضَلَّ قَبۡلَهُمۡ أَكۡثَرُ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿٧١

71ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ﴿٧٢

72በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡

فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُنذَرِينَ﴿٧٣

73የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡

إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ﴿٧٤

74ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡

وَلَقَدۡ نَادَىٰنَا نُوحٞ فَلَنِعۡمَ ٱلۡمُجِيبُونَ﴿٧٥

75ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን!

وَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥ مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ﴿٧٦

76እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡

وَجَعَلۡنَا ذُرِّيَّتَهُۥ هُمُ ٱلۡبَاقِينَ﴿٧٧

77ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤

وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ﴿٧٨

78በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡

سَلَٰمٌ عَلَىٰ نُوحٖ فِي ٱلۡعَٰلَمِينَ﴿٧٩

79«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡»

إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ﴿٨٠

80እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡

إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ﴿٨١

81እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡

ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ﴿٨٢

82ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡

۞ وَإِنَّ مِن شِيعَتِهِۦ لَإِبۡرَٰهِيمَ﴿٨٣

83ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡

إِذۡ جَآءَ رَبَّهُۥ بِقَلۡبٖ سَلِيمٍ﴿٨٤

84ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡

إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَاذَا تَعۡبُدُونَ﴿٨٥

85«ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡

أَئِفۡكًا ءَالِهَةٗ دُونَ ٱللَّهِ تُرِيدُونَ﴿٨٦

86«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?

فَمَا ظَنُّكُم بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ﴿٨٧

87«በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡

فَنَظَرَ نَظۡرَةٗ فِي ٱلنُّجُومِ﴿٨٨

88በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡

فَقَالَ إِنِّي سَقِيمٞ﴿٨٩

89«እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡

فَتَوَلَّوۡاْ عَنۡهُ مُدۡبِرِينَ﴿٩٠

90ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡

فَرَاغَ إِلَىٰٓ ءَالِهَتِهِمۡ فَقَالَ أَلَا تَأۡكُلُونَ﴿٩١

91ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?»

مَا لَكُمۡ لَا تَنطِقُونَ﴿٩٢

92«የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?»

فَرَاغَ عَلَيۡهِمۡ ضَرۡبَۢا بِٱلۡيَمِينِ﴿٩٣

93በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡

فَأَقۡبَلُوٓاْ إِلَيۡهِ يَزِفُّونَ﴿٩٤

94ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡

قَالَ أَتَعۡبُدُونَ مَا تَنۡحِتُونَ﴿٩٥

95አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?»

وَٱللَّهُ خَلَقَكُمۡ وَمَا تَعۡمَلُونَ﴿٩٦

96«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡»

قَالُواْ ٱبۡنُواْ لَهُۥ بُنۡيَٰنٗا فَأَلۡقُوهُ فِي ٱلۡجَحِيمِ﴿٩٧

97«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡

فَأَرَادُواْ بِهِۦ كَيۡدٗا فَجَعَلۡنَٰهُمُ ٱلۡأَسۡفَلِينَ﴿٩٨

98በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡

وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهۡدِينِ﴿٩٩

99አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡»

رَبِّ هَبۡ لِي مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ﴿١٠٠

100ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡

فَبَشَّرۡنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٖ﴿١٠١

101ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡

فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعۡيَ قَالَ يَٰبُنَيَّ إِنِّيٓ أَرَىٰ فِي ٱلۡمَنَامِ أَنِّيٓ أَذۡبَحُكَ فَٱنظُرۡ مَاذَا تَرَىٰۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفۡعَلۡ مَا تُؤۡمَرُۖ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ﴿١٠٢

102ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡

فَلَمَّآ أَسۡلَمَا وَتَلَّهُۥ لِلۡجَبِينِ﴿١٠٣

103ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡

وَنَٰدَيۡنَٰهُ أَن يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ﴿١٠٤

104ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!

قَدۡ صَدَّقۡتَ ٱلرُّءۡيَآۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ﴿١٠٥

105ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡

إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡبَلَٰٓؤُاْ ٱلۡمُبِينُ﴿١٠٦

106ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡

وَفَدَيۡنَٰهُ بِذِبۡحٍ عَظِيمٖ﴿١٠٧

107በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡

وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ﴿١٠٨

108በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡

سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ﴿١٠٩

109ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡

كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ﴿١١٠

110እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡

إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ﴿١١١

111እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡

وَبَشَّرۡنَٰهُ بِإِسۡحَٰقَ نَبِيّٗا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ﴿١١٢

112በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡

وَبَٰرَكۡنَا عَلَيۡهِ وَعَلَىٰٓ إِسۡحَٰقَۚ وَمِن ذُرِّيَّتِهِمَا مُحۡسِنٞ وَظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ مُبِينٞ﴿١١٣

113በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡

وَلَقَدۡ مَنَنَّا عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ﴿١١٤

114በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡

وَنَجَّيۡنَٰهُمَا وَقَوۡمَهُمَا مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ﴿١١٥

115እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡

وَنَصَرۡنَٰهُمۡ فَكَانُواْ هُمُ ٱلۡغَٰلِبِينَ﴿١١٦

116ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡

وَءَاتَيۡنَٰهُمَا ٱلۡكِتَٰبَ ٱلۡمُسۡتَبِينَ﴿١١٧

117በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡

وَهَدَيۡنَٰهُمَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ﴿١١٨

118ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡

وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِمَا فِي ٱلۡأٓخِرِينَ﴿١١٩

119በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡

سَلَٰمٌ عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ﴿١٢٠

120ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡

إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ﴿١٢١

121እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡

إِنَّهُمَا مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ﴿١٢٢

122ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡

وَإِنَّ إِلۡيَاسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ﴿١٢٣

123ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡

إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦٓ أَلَا تَتَّقُونَ﴿١٢٤

124ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን?

أَتَدۡعُونَ بَعۡلٗا وَتَذَرُونَ أَحۡسَنَ ٱلۡخَٰلِقِينَ﴿١٢٥

125በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን?

ٱللَّهَ رَبَّكُمۡ وَرَبَّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿١٢٦

126አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)?

فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ﴿١٢٧

127አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡

إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ﴿١٢٨

128ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡

وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ﴿١٢٩

129በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡

سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِلۡ يَاسِينَ﴿١٣٠

130ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡

إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ﴿١٣١

131እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡

إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ﴿١٣٢

132እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡

وَإِنَّ لُوطٗا لَّمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ﴿١٣٣

133ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡

إِذۡ نَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ﴿١٣٤

134እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡

إِلَّا عَجُوزٗا فِي ٱلۡغَٰبِرِينَ﴿١٣٥

135(በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡

ثُمَّ دَمَّرۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ﴿١٣٦

136ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡

وَإِنَّكُمۡ لَتَمُرُّونَ عَلَيۡهِم مُّصۡبِحِينَ﴿١٣٧

137እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡

وَبِٱلَّيۡلِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ﴿١٣٨

138በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን?

وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ﴿١٣٩

139ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡

إِذۡ أَبَقَ إِلَى ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ﴿١٤٠

140ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡

فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ ٱلۡمُدۡحَضِينَ﴿١٤١

141ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡

فَٱلۡتَقَمَهُ ٱلۡحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٞ﴿١٤٢

142እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡

فَلَوۡلَآ أَنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلۡمُسَبِّحِينَ﴿١٤٣

143እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤

لَلَبِثَ فِي بَطۡنِهِۦٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ﴿١٤٤

144እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡

۞ فَنَبَذۡنَٰهُ بِٱلۡعَرَآءِ وَهُوَ سَقِيمٞ﴿١٤٥

145እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡

وَأَنۢبَتۡنَا عَلَيۡهِ شَجَرَةٗ مِّن يَقۡطِينٖ﴿١٤٦

146በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡

وَأَرۡسَلۡنَٰهُ إِلَىٰ مِاْئَةِ أَلۡفٍ أَوۡ يَزِيدُونَ﴿١٤٧

147ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ።

فَـَٔامَنُواْ فَمَتَّعۡنَٰهُمۡ إِلَىٰ حِينٖ﴿١٤٨

148አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡

فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَلِرَبِّكَ ٱلۡبَنَاتُ وَلَهُمُ ٱلۡبَنُونَ﴿١٤٩

149ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?»

أَمۡ خَلَقۡنَا ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ إِنَٰثٗا وَهُمۡ شَٰهِدُونَ﴿١٥٠

150ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?

أَلَآ إِنَّهُم مِّنۡ إِفۡكِهِمۡ لَيَقُولُونَ﴿١٥١

151ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡-

وَلَدَ ٱللَّهُ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ﴿١٥٢

152«አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡

أَصۡطَفَى ٱلۡبَنَاتِ عَلَى ٱلۡبَنِينَ﴿١٥٣

153በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን?

مَا لَكُمۡ كَيۡفَ تَحۡكُمُونَ﴿١٥٤

154ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!

أَفَلَا تَذَكَّرُونَ﴿١٥٥

155አትገነዘቡምን?

أَمۡ لَكُمۡ سُلۡطَٰنٞ مُّبِينٞ﴿١٥٦

156ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን?

فَأۡتُواْ بِكِتَٰبِكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ﴿١٥٧

157«እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡

وَجَعَلُواْ بَيۡنَهُۥ وَبَيۡنَ ٱلۡجِنَّةِ نَسَبٗاۚ وَلَقَدۡ عَلِمَتِ ٱلۡجِنَّةُ إِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ﴿١٥٨

158በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡

سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ﴿١٥٩

159አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡

إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ﴿١٦٠

160ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡

فَإِنَّكُمۡ وَمَا تَعۡبُدُونَ﴿١٦١

161እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤

مَآ أَنتُمۡ عَلَيۡهِ بِفَٰتِنِينَ﴿١٦٢

162በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡

إِلَّا مَنۡ هُوَ صَالِ ٱلۡجَحِيمِ﴿١٦٣

163ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡

وَمَا مِنَّآ إِلَّا لَهُۥ مَقَامٞ مَّعۡلُومٞ﴿١٦٤

164(ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡

وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلصَّآفُّونَ﴿١٦٥

165እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡

وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلۡمُسَبِّحُونَ﴿١٦٦

166እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡

وَإِن كَانُواْ لَيَقُولُونَ﴿١٦٧

167እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡-

لَوۡ أَنَّ عِندَنَا ذِكۡرٗا مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿١٦٨

168«ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤

لَكُنَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ﴿١٦٩

169«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡»

فَكَفَرُواْ بِهِۦۖ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ﴿١٧٠

170ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡

وَلَقَدۡ سَبَقَتۡ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا ٱلۡمُرۡسَلِينَ﴿١٧١

171(የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡

إِنَّهُمۡ لَهُمُ ٱلۡمَنصُورُونَ﴿١٧٢

172እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ﴿١٧٣

173ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٖ﴿١٧٤

174ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡

وَأَبۡصِرۡهُمۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ﴿١٧٥

175እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡

أَفَبِعَذَابِنَا يَسۡتَعۡجِلُونَ﴿١٧٦

176በቅጣታችንም ያቻኩላሉን?

فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمۡ فَسَآءَ صَبَاحُ ٱلۡمُنذَرِينَ﴿١٧٧

177በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!

وَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٖ﴿١٧٨

178እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡

وَأَبۡصِرۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ﴿١٧٩

179ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡

سُبۡحَٰنَ رَبِّكَ رَبِّ ٱلۡعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ﴿١٨٠

180የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡

وَسَلَٰمٌ عَلَى ٱلۡمُرۡسَلِينَ﴿١٨١

181በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤

وَٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ﴿١٨٢

182ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡

RELATED SURAHS