صٓۚ وَٱلۡقُرۡءَانِ ذِي ٱلذِّكۡرِ﴿١﴾
1ሷድ የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ (ብዙ አማልክት አሉ እንደሚሉት አይደለም)፡፡
بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي عِزَّةٖ وَشِقَاقٖ﴿٢﴾
2ይልቁንም እነዚያ የካዱት ሰዎች በትዕቢትና በክርክር ውስጥ ናቸው፡፡
كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّن قَرۡنٖ فَنَادَواْ وَّلَاتَ حِينَ مَنَاصٖ﴿٣﴾
3ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙን አጥፍተናል፡፡ (ጊዜው) የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ፡፡
وَعَجِبُوٓاْ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٞ مِّنۡهُمۡۖ وَقَالَ ٱلۡكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٞ كَذَّابٌ﴿٤﴾
4ከእነርሱ የሆነ አስፈራሪም ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም «ይህ ድግምተኛ (ጠንቋይ) ውሸታም ነው» አሉ፡፡
أَجَعَلَ ٱلۡأٓلِهَةَ إِلَٰهٗا وَٰحِدًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٌ عُجَابٞ﴿٥﴾
5«አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው» (አሉ)፡፡
وَٱنطَلَقَ ٱلۡمَلَأُ مِنۡهُمۡ أَنِ ٱمۡشُواْ وَٱصۡبِرُواْ عَلَىٰٓ ءَالِهَتِكُمۡۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٞ يُرَادُ﴿٦﴾
6ከእነርሱም መኳንንቶቹ «ሂዱ፤ በአማልክቶቻችሁም (መግገዛት) ላይ ታገሱ፡፡ ይህ (ከእኛ) የሚፈለግ ነገር ነውና» እያሉ አዘገሙ፡፡
مَا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِي ٱلۡمِلَّةِ ٱلۡأٓخِرَةِ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا ٱخۡتِلَٰقٌ﴿٧﴾
7«ይህንንም በኋለኛይቱ ሃይማኖት አልሰማንም፡፡ ይህ ውሸትን መፍጠር እንጅ ሌላ አይደለም» (እያሉም)፡፡
أَءُنزِلَ عَلَيۡهِ ٱلذِّكۡرُ مِنۢ بَيۡنِنَاۚ بَلۡ هُمۡ فِي شَكّٖ مِّن ذِكۡرِيۚ بَل لَّمَّا يَذُوقُواْ عَذَابِ﴿٨﴾
8«ከመካከላችን በእርሱ ላይ ቁርኣን ተወረደን?» (አሉ)፡፡ በእውነት እነርሱ ከግሳጼዬ (ከቁርኣን) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ በእርግጥም ቅጣቴን ገና አልቀመሱም፡፡
أَمۡ عِندَهُمۡ خَزَآئِنُ رَحۡمَةِ رَبِّكَ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡوَهَّابِ﴿٩﴾
9ይልቁንም የአሸናፊውና የለጋሱ ጌታህ የችሮታው መጋዘኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?
أَمۡ لَهُم مُّلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَاۖ فَلۡيَرۡتَقُواْ فِي ٱلۡأَسۡبَٰبِ﴿١٠﴾
10ወይስ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የእነርሱ ነውን? (ነው ቢሉ) በመሰላሎችም ይውጡ፡፡
جُندٞ مَّا هُنَالِكَ مَهۡزُومٞ مِّنَ ٱلۡأَحۡزَابِ﴿١١﴾
11እዚያ ዘንድ ከአሕዛብ የሆኑ ተሸናፊ ሰራዊት ናቸው፡፡
كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَعَادٞ وَفِرۡعَوۡنُ ذُو ٱلۡأَوۡتَادِ﴿١٢﴾
12ከእነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች፣ ዓድም፣ የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባበሉ፡፡
وَثَمُودُ وَقَوۡمُ لُوطٖ وَأَصۡحَٰبُ لۡـَٔيۡكَةِۚ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلۡأَحۡزَابُ﴿١٣﴾
13ሰሙድም፣ የሉጥ ሰዎችም፣ የአይከት ሰዎችም (አስተባበሉ)፡፡ እነዚህ አሕዛቦቹ ናቸው፡፡
إِن كُلٌّ إِلَّا كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ عِقَابِ﴿١٤﴾
14ሁሉም መልክተኞቹን ያስዋሹ እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ ቅጣቴም ተረጋገጠባቸው፡፡
وَمَا يَنظُرُ هَٰٓؤُلَآءِ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ مَّا لَهَا مِن فَوَاقٖ﴿١٥﴾
15እነዚህም ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲትን ጩኸት እንጅ ሌላን አይጠባበቁም፡፡
وَقَالُواْ رَبَّنَا عَجِّل لَّنَا قِطَّنَا قَبۡلَ يَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ﴿١٦﴾
16«ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት መጽሐፋችንን አስቸኩልልን» አሉም፡፡
ٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱذۡكُرۡ عَبۡدَنَا دَاوُۥدَ ذَا ٱلۡأَيۡدِۖ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ﴿١٧﴾
17በሚሉት ነገር ላይ ታገስ፡፡ የኀይል ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳላቸው፡፡ እርሱ በጣም መላሳ ነውና፡፡
إِنَّا سَخَّرۡنَا ٱلۡجِبَالَ مَعَهُۥ يُسَبِّحۡنَ بِٱلۡعَشِيِّ وَٱلۡإِشۡرَاقِ﴿١٨﴾
18እኛ ተራራዎችን ከቀትር በኋላና በረፋድም ከእርሱ ጋር የሚያወድሱ ሲሆኑ ገራንለት፡፡
وَٱلطَّيۡرَ مَحۡشُورَةٗۖ كُلّٞ لَّهُۥٓ أَوَّابٞ﴿١٩﴾
19በራሪዎችንም (አእዋፍን) የሚሰበሰቡ ሆነው (ገራንለት)፡፡ ሁሉም ለእርሱ (ማወደስ) የሚመላለስ ነው፡፡
وَشَدَدۡنَا مُلۡكَهُۥ وَءَاتَيۡنَٰهُ ٱلۡحِكۡمَةَ وَفَصۡلَ ٱلۡخِطَابِ﴿٢٠﴾
20መንግሥቱንም አበረታንለት፡፡ ጥበብንም ንግግርን መለየትንም ሰጠነው፡፡
۞ وَهَلۡ أَتَىٰكَ نَبَؤُاْ ٱلۡخَصۡمِ إِذۡ تَسَوَّرُواْ ٱلۡمِحۡرَابَ﴿٢١﴾
21የተከራካሪዎቹም ወሬ መጥቶልሃልን? ምኩራቡን በተንጠላጠሉ ጊዜ፡፡
إِذۡ دَخَلُواْ عَلَىٰ دَاوُۥدَ فَفَزِعَ مِنۡهُمۡۖ قَالُواْ لَا تَخَفۡۖ خَصۡمَانِ بَغَىٰ بَعۡضُنَا عَلَىٰ بَعۡضٖ فَٱحۡكُم بَيۡنَنَا بِٱلۡحَقِّ وَلَا تُشۡطِطۡ وَٱهۡدِنَآ إِلَىٰ سَوَآءِ ٱلصِّرَٰطِ﴿٢٢﴾
22በዳውድ ላይም በገቡ ጊዜ ከእነርሱም በደነገጠ ጊዜ «አትፍራ፤ (እኛ) ከፊላችን በከፊሉ ላይ ወሰን ያለፈ ሁለት ተከራካሪዎች ነን፡፡ በመካከላችንም በእውነት ፍረድ፡፡ አታዳላም፡፡ ወደ ትክክለኛው መንገድም ምረን።
إِنَّ هَٰذَآ أَخِي لَهُۥ تِسۡعٞ وَتِسۡعُونَ نَعۡجَةٗ وَلِيَ نَعۡجَةٞ وَٰحِدَةٞ فَقَالَ أَكۡفِلۡنِيهَا وَعَزَّنِي فِي ٱلۡخِطَابِ﴿٢٣﴾
23«ይህ ወንድሜ ነው፤ ለእርሱ ዘጠና ዘጠኝ ሴቶች በጎች አሉት፡፡ ለኔም አንዲት ሴት በግ አለችኝ፤ እሷን ለእኔ አድርጋት አለኝ። በንግግርም አቸነፈኝ" አለው።
قَالَ لَقَدۡ ظَلَمَكَ بِسُؤَالِ نَعۡجَتِكَ إِلَىٰ نِعَاجِهِۦۖ وَإِنَّ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلۡخُلَطَآءِ لَيَبۡغِي بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٍ إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَقَلِيلٞ مَّا هُمۡۗ وَظَنَّ دَاوُۥدُ أَنَّمَا فَتَنَّٰهُ فَٱسۡتَغۡفَرَ رَبَّهُۥ وَخَرَّۤ رَاكِعٗاۤ وَأَنَابَ۩﴿٢٤﴾
24«ሴት በግህን ወደ በጎቹ (ለመቀላቀል) በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ፡፡ ከተጋሪዎችም ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው» አለ፡፡ ዳውድም የፈተንነው መኾኑን ዐወቀ፡፡ ጌታውንም ምሕረትን ለመነ፡፡ ሰጋጅ ኾኖ ወደቀም፡፡ በመጸጸት ተመለሰም፡፡[1]
فَغَفَرۡنَا لَهُۥ ذَٰلِكَۖ وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلۡفَىٰ وَحُسۡنَ مَـَٔابٖ﴿٢٥﴾
25ያንንም ማርነው፤ ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ (ክብር) መልካም መመለሻም አለው፡፡
يَٰدَاوُۥدُ إِنَّا جَعَلۡنَٰكَ خَلِيفَةٗ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱحۡكُم بَيۡنَ ٱلنَّاسِ بِٱلۡحَقِّ وَلَا تَتَّبِعِ ٱلۡهَوَىٰ فَيُضِلَّكَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَضِلُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدُۢ بِمَا نَسُواْ يَوۡمَ ٱلۡحِسَابِ﴿٢٦﴾
26ዳውድ ሆይ! እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሃልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ፡፡ ዝንባሌሀንም አትከተል፤ ከአላህ መንገድ ያሳሳትሃልና፡፡ እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚሳሳቱ የምርመራውን ቀን በመርሳታቸው ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፡፡
وَمَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَآءَ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَا بَٰطِلٗاۚ ذَٰلِكَ ظَنُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۚ فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنَ ٱلنَّارِ﴿٢٧﴾
27ሰማይንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም፡፡ ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው!
أَمۡ نَجۡعَلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ كَٱلۡمُفۡسِدِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ نَجۡعَلُ ٱلۡمُتَّقِينَ كَٱلۡفُجَّارِ﴿٢٨﴾
28በእውነቱ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለን? ወይስ አላህን ፊረዎቹን እንደ ከሓዲዎቹ እናደርጋለን?
كِتَٰبٌ أَنزَلۡنَٰهُ إِلَيۡكَ مُبَٰرَكٞ لِّيَدَّبَّرُوٓاْ ءَايَٰتِهِۦ وَلِيَتَذَكَّرَ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ﴿٢٩﴾
29(ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡
وَوَهَبۡنَا لِدَاوُۥدَ سُلَيۡمَٰنَۚ نِعۡمَ ٱلۡعَبۡدُ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ﴿٣٠﴾
30ለዳውድም ሱለይማንን ሰጠነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ! (ሱለይማን)፣ እርሱ መላሳ ነው፡፡
إِذۡ عُرِضَ عَلَيۡهِ بِٱلۡعَشِيِّ ٱلصَّٰفِنَٰتُ ٱلۡجِيَادُ﴿٣١﴾
31በእርሱ ላይ ከቀትር በኋላ በሦስት እግሮችና በአራተኛዋ ኮቴ ጫፍ የሚቆሙ ጮሌዎች ፈረሶች በተቀረቡለት ጊዜ (አስታውስ)፡፡
فَقَالَ إِنِّيٓ أَحۡبَبۡتُ حُبَّ ٱلۡخَيۡرِ عَن ذِكۡرِ رَبِّي حَتَّىٰ تَوَارَتۡ بِٱلۡحِجَابِ﴿٣٢﴾
32አለም «እኔ (ፀሐይ) በግርዶ እስከ ተደበቀች ድረስ ከጌታዬ ማስታወስ ፋንታ ፈረስን መውደድን መረጥኩ፡፡»
رُدُّوهَا عَلَيَّۖ فَطَفِقَ مَسۡحَۢا بِٱلسُّوقِ وَٱلۡأَعۡنَاقِ﴿٣٣﴾
33«በእኔ ላይ መልሷት» (አለ) አጋዶችዋንና አንገቶችዋንም ማበስ ያዘ፡፡
وَلَقَدۡ فَتَنَّا سُلَيۡمَٰنَ وَأَلۡقَيۡنَا عَلَىٰ كُرۡسِيِّهِۦ جَسَدٗا ثُمَّ أَنَابَ﴿٣٤﴾
34ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው፡፡ በመንበሩም ላይ አካልን ጣልን፡፡ ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ፡፡
قَالَ رَبِّ ٱغۡفِرۡ لِي وَهَبۡ لِي مُلۡكٗا لَّا يَنۢبَغِي لِأَحَدٖ مِّنۢ بَعۡدِيٓۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡوَهَّابُ﴿٣٥﴾
35«ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ማር፡፡ ከእኔ በኋላ ለአንድም የማይገባንም ንግሥና ስጠኝ፡፡ አንተ ለጋሱ አንተ ብቻ ነህና» አለ፡፡
فَسَخَّرۡنَا لَهُ ٱلرِّيحَ تَجۡرِي بِأَمۡرِهِۦ رُخَآءً حَيۡثُ أَصَابَ﴿٣٦﴾
36ነፋስንም በትእዛዙ ወደፈለገበት ስፍራ ልዝብ ኾና የምትነፍስ ስትኾን ገራንለት፡፡
وَٱلشَّيَٰطِينَ كُلَّ بَنَّآءٖ وَغَوَّاصٖ﴿٣٧﴾
37ሰይጣናትንም ገንቢዎችንና ሰጣሚዎችን ሁሉ (ገራንለት)፡፡
وَءَاخَرِينَ مُقَرَّنِينَ فِي ٱلۡأَصۡفَادِ﴿٣٨﴾
38ሌሎችንም በፍንጆች ተቆራኞችን (ገራንለት)፡፡
هَٰذَا عَطَآؤُنَا فَٱمۡنُنۡ أَوۡ أَمۡسِكۡ بِغَيۡرِ حِسَابٖ﴿٣٩﴾
39«ይህ ስጦታችን ነው፡፡ ያለግምት ለግስ፤ ወይም ጨብጥ» (አልነው)፡፡
وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلۡفَىٰ وَحُسۡنَ مَـَٔابٖ﴿٤٠﴾
40ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ፤ መልካም መመለሻም በእርግጥ አልለው፡፡
وَٱذۡكُرۡ عَبۡدَنَآ أَيُّوبَ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّي مَسَّنِيَ ٱلشَّيۡطَٰنُ بِنُصۡبٖ وَعَذَابٍ﴿٤١﴾
41ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡
ٱرۡكُضۡ بِرِجۡلِكَۖ هَٰذَا مُغۡتَسَلُۢ بَارِدٞ وَشَرَابٞ﴿٤٢﴾
42«በእግርህ (ምድርን) ምታ፡፡ ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው» (ተባለ)፡፡
وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ أَهۡلَهُۥ وَمِثۡلَهُم مَّعَهُمۡ رَحۡمَةٗ مِّنَّا وَذِكۡرَىٰ لِأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ﴿٤٣﴾
43ለእርሱም ከእኛ ዘንድ ለችሮታ ባለአእምሮዎችንም ለመገሠጽ ቤተሰቦቹን ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ሰጠነው፡፡
وَخُذۡ بِيَدِكَ ضِغۡثٗا فَٱضۡرِب بِّهِۦ وَلَا تَحۡنَثۡۗ إِنَّا وَجَدۡنَٰهُ صَابِرٗاۚ نِّعۡمَ ٱلۡعَبۡدُ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٞ﴿٤٤﴾
44«በእጅህም ጭብጥ አርጩሜን ያዝ፡፡ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ፡፡ ማላህንም አታፍርስ» (አልነው)፡፡ እኛ ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ እርሱ በጣም መላሳ ነው፡፡
وَٱذۡكُرۡ عِبَٰدَنَآ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ أُوْلِي ٱلۡأَيۡدِي وَٱلۡأَبۡصَٰرِ﴿٤٥﴾
45ባሮቻችንንም ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆበንም፣ የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የኾኑን አውሳላቸው፡፡
إِنَّآ أَخۡلَصۡنَٰهُم بِخَالِصَةٖ ذِكۡرَى ٱلدَّارِ﴿٤٦﴾
46እኛ ጥሩ በኾነች ጠባይ መረጥናቸው፡፡ (እርሷም) የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት፡፡
وَإِنَّهُمۡ عِندَنَا لَمِنَ ٱلۡمُصۡطَفَيۡنَ ٱلۡأَخۡيَارِ﴿٤٧﴾
47እነርሱም እኛ ዘንድ ከመልካሞቹ ምርጦች ናቸው፡፡
وَٱذۡكُرۡ إِسۡمَٰعِيلَ وَٱلۡيَسَعَ وَذَا ٱلۡكِفۡلِۖ وَكُلّٞ مِّنَ ٱلۡأَخۡيَارِ﴿٤٨﴾
48ኢስማዒልንም፣ አልየሰዕንም፣ ዙልኪፍልንም አውሳ፡፡ ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው፡፡
هَٰذَا ذِكۡرٞۚ وَإِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ لَحُسۡنَ مَـَٔابٖ﴿٤٩﴾
49ይህ መልካም ዝና ነው፡፡ ለአላህ ፈሪዎችም በእርግጥ ውብ የኾነ መመለሻ አላቸው፡፡
جَنَّٰتِ عَدۡنٖ مُّفَتَّحَةٗ لَّهُمُ ٱلۡأَبۡوَٰبُ﴿٥٠﴾
50በሮቻቸው ለእነርሱ የተከፈቱ ሲኾኑ የመኖሪያ ገነቶች አሏቸው፡፡
مُتَّكِـِٔينَ فِيهَا يَدۡعُونَ فِيهَا بِفَٰكِهَةٖ كَثِيرَةٖ وَشَرَابٖ﴿٥١﴾
51በእርሷ ውስጥ የተደገፉ ኾነው በውስጧ በብዙ እሸቶችና በመጠጥም ያዝዛሉ፡፡
۞ وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ أَتۡرَابٌ﴿٥٢﴾
52እነርሱ ዘንድም ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች እኩያዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡
هَٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِيَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ﴿٥٣﴾
53ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተሰፋ ነው፡፡
إِنَّ هَٰذَا لَرِزۡقُنَا مَا لَهُۥ مِن نَّفَادٍ﴿٥٤﴾
54ይህ ሲሳያችን ነው፡፡ ለእርሱ ምንም ማለቅ የለውም፡፡
هَٰذَاۚ وَإِنَّ لِلطَّٰغِينَ لَشَرَّ مَـَٔابٖ﴿٥٥﴾
55ይህ (ለአማኞች ነው)፡፡ ለጠማሞችም በጣም የከፋ መመለሻ አላቸው፡፡
جَهَنَّمَ يَصۡلَوۡنَهَا فَبِئۡسَ ٱلۡمِهَادُ﴿٥٦﴾
56የሚገቧት ስትኾን ገሀነም (አለቻቸው)፡፡ ምንጣፊቱም ምንኛ ከፋች፡፡
هَٰذَا فَلۡيَذُوقُوهُ حَمِيمٞ وَغَسَّاقٞ﴿٥٧﴾
57ይህ (ለከሓዲዎች ነው)፡፡ ይቅመሱትም፡፡ የፈላ ውሃና እዥ ነው፡፡
وَءَاخَرُ مِن شَكۡلِهِۦٓ أَزۡوَٰجٌ﴿٥٨﴾
58ሌላም ከመሰሉ ዓይነቶች አልሉ፡፡
هَٰذَا فَوۡجٞ مُّقۡتَحِمٞ مَّعَكُمۡ لَا مَرۡحَبَۢا بِهِمۡۚ إِنَّهُمۡ صَالُواْ ٱلنَّارِ﴿٥٩﴾
59ይህ ከእናንተ ጋር በመጋፈጥ ገቢ ጭፍራ ነው፤ (ይባላሉ)፡፡ ለእነርሱ አይስፋቸው፡፡ እነርሱ እሳትን ገቢዎች ናቸውና (ይላሉ)፡፡
قَالُواْ بَلۡ أَنتُمۡ لَا مَرۡحَبَۢا بِكُمۡۖ أَنتُمۡ قَدَّمۡتُمُوهُ لَنَاۖ فَبِئۡسَ ٱلۡقَرَارُ﴿٦٠﴾
60(ተከታዮቹ) ይላሉ «ይልቁን እናንተ አይስፋችሁ፡፡ እናንተ (ክህደቱን) ለእኛ አቀረባችሁት፡፡ መርጊያይቱም (ገሀነም) ከፋች፡፡»
قَالُواْ رَبَّنَا مَن قَدَّمَ لَنَا هَٰذَا فَزِدۡهُ عَذَابٗا ضِعۡفٗا فِي ٱلنَّارِ﴿٦١﴾
61«ጌታችን ሆይ! ይህንን ያቀረበልንን ሰው በእሳት ውስጥ እጥፍን ቅጣት ጨምርለት» ይላሉ፡፡
وَقَالُواْ مَا لَنَا لَا نَرَىٰ رِجَالٗا كُنَّا نَعُدُّهُم مِّنَ ٱلۡأَشۡرَارِ﴿٦٢﴾
62ይላሉም «ለእኛ ምን አለን? ከመጥፎዎች እንቆጥራቸው የነበሩትን ሰዎች (እዚህ) አናይምሳ፡፡»
أَتَّخَذۡنَٰهُمۡ سِخۡرِيًّا أَمۡ زَاغَتۡ عَنۡهُمُ ٱلۡأَبۡصَٰرُ﴿٦٣﴾
63«መቀለጃ አድርገን ያዝናቸውን? ወይስ ዓይኖቻችን ከእነሱ ዋለሉ?»
إِنَّ ذَٰلِكَ لَحَقّٞ تَخَاصُمُ أَهۡلِ ٱلنَّارِ﴿٦٤﴾
64ይህ በእርግጥ እምነት ነው፡፡ (እርሱም) የእሳት ሰዎች (የእርስ በእርስ) መካሰስ ነው፡፡
قُلۡ إِنَّمَآ أَنَا۠ مُنذِرٞۖ وَمَا مِنۡ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ٱلۡوَٰحِدُ ٱلۡقَهَّارُ﴿٦٥﴾
65«እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ፡፡ ኀያል አንድ ከኾነው አላህ በቀር ምንም አምላክ የለም» በላቸው፡፡
رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡغَفَّٰرُ﴿٦٦﴾
66«የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡»
قُلۡ هُوَ نَبَؤٌاْ عَظِيمٌ﴿٦٧﴾
67በላቸው «እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው፡፡
أَنتُمۡ عَنۡهُ مُعۡرِضُونَ﴿٦٨﴾
68«እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ፡፡
مَا كَانَ لِيَ مِنۡ عِلۡمِۭ بِٱلۡمَلَإِ ٱلۡأَعۡلَىٰٓ إِذۡ يَخۡتَصِمُونَ﴿٦٩﴾
69(በአደም ነገር) «በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛው ሰራዊት ለእኔ ምንም ዕውቀት አልነበረኝም፡፡
إِن يُوحَىٰٓ إِلَيَّ إِلَّآ أَنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٞ مُّبِينٌ﴿٧٠﴾
70«ወደ እኔም አስፈራሪ ገላጭ መኾኔ እንጂ ሌላ አይወረድልኝም» (በል)፡፡
إِذۡ قَالَ رَبُّكَ لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّي خَٰلِقُۢ بَشَرٗا مِّن طِينٖ﴿٧١﴾
71ጌታህ «ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» (አስታውስ)፡፡
فَإِذَا سَوَّيۡتُهُۥ وَنَفَخۡتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُواْ لَهُۥ سَٰجِدِينَ﴿٧٢﴾
72«ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» (አልኩ)፡፡
فَسَجَدَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ كُلُّهُمۡ أَجۡمَعُونَ﴿٧٣﴾
73መላእክትም መላውም ባንድነት ሰገዱ፡፡
إِلَّآ إِبۡلِيسَ ٱسۡتَكۡبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ﴿٧٤﴾
74ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ ኮራ፤ ከከሓዲዎቹም ነበር፡፡
قَالَ يَٰٓإِبۡلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسۡجُدَ لِمَا خَلَقۡتُ بِيَدَيَّۖ أَسۡتَكۡبَرۡتَ أَمۡ كُنتَ مِنَ ٱلۡعَالِينَ﴿٧٥﴾
75(አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ) ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡
قَالَ أَنَا۠ خَيۡرٞ مِّنۡهُ خَلَقۡتَنِي مِن نَّارٖ وَخَلَقۡتَهُۥ مِن طِينٖ﴿٧٦﴾
76«እኔ ከእርሱ በላጭ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ ከጭቃም ፈጠርከው» አለ፡፡
قَالَ فَٱخۡرُجۡ مِنۡهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٞ﴿٧٧﴾
77(አላህ) አለው «ከእርሷ ውጣ፤ አንተ የተባረርክ ነህና፡፡»
وَإِنَّ عَلَيۡكَ لَعۡنَتِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلدِّينِ﴿٧٨﴾
78«እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይኹን፡፡»
قَالَ رَبِّ فَأَنظِرۡنِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ﴿٧٩﴾
79«ጌታዬ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝም» አለ፡፡
قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ ٱلۡمُنظَرِينَ﴿٨٠﴾
80(አላህም) አለው «አንተ ከሚቆዩት ነህ፡፡»
إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡوَقۡتِ ٱلۡمَعۡلُومِ﴿٨١﴾
81«እስከ ታወቀው ወቅት ቀን ድረስ፡፡»
قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغۡوِيَنَّهُمۡ أَجۡمَعِينَ﴿٨٢﴾
82(እርሱም) አለ «በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ፡፡»
إِلَّا عِبَادَكَ مِنۡهُمُ ٱلۡمُخۡلَصِينَ﴿٨٣﴾
83«ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡»
قَالَ فَٱلۡحَقُّ وَٱلۡحَقَّ أَقُولُ﴿٨٤﴾
84(አላህ) አለው «እውነቱም (ከኔ ነው)፡፡ እውነትንም እላለሁ፡፡
لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكَ وَمِمَّن تَبِعَكَ مِنۡهُمۡ أَجۡمَعِينَ﴿٨٥﴾
85ከአንተና ከእነርሱ ውስጥ ከተከተሉህ ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ፡፡»
قُلۡ مَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٖ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُتَكَلِّفِينَ﴿٨٦﴾
86በላቸው «በእርሱ ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፤ እኔም ከተግደርዳሪዎቹ አይደለሁም፡፡
إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ لِّلۡعَٰلَمِينَ﴿٨٧﴾
87«እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሠጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
وَلَتَعۡلَمُنَّ نَبَأَهُۥ بَعۡدَ حِينِۭ﴿٨٨﴾
88«ትንቢቱንም (እውነት መኾኑን) ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡»