Al-A'la

الأعلى

The Most High19 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

سَبِّحِ ٱسۡمَ رَبِّكَ ٱلۡأَعۡلَى﴿١

1ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡

ٱلَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ﴿٢

2የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡

وَٱلَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ﴿٣

3የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡

وَٱلَّذِيٓ أَخۡرَجَ ٱلۡمَرۡعَىٰ﴿٤

4የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡

فَجَعَلَهُۥ غُثَآءً أَحۡوَىٰ﴿٥

5(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡

سَنُقۡرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰٓ﴿٦

6(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡

إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ إِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلۡجَهۡرَ وَمَا يَخۡفَىٰ﴿٧

7አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡

وَنُيَسِّرُكَ لِلۡيُسۡرَىٰ﴿٨

8ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡

فَذَكِّرۡ إِن نَّفَعَتِ ٱلذِّكۡرَىٰ﴿٩

9ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡

سَيَذَّكَّرُ مَن يَخۡشَىٰ﴿١٠

10(አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡

وَيَتَجَنَّبُهَا ٱلۡأَشۡقَى﴿١١

11መናጢውም ይርቃታል፡፡

ٱلَّذِي يَصۡلَى ٱلنَّارَ ٱلۡكُبۡرَىٰ﴿١٢

12ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡

ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحۡيَىٰ﴿١٣

13ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡

قَدۡ أَفۡلَحَ مَن تَزَكَّىٰ﴿١٤

14የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡

وَذَكَرَ ٱسۡمَ رَبِّهِۦ فَصَلَّىٰ﴿١٥

15የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡

بَلۡ تُؤۡثِرُونَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا﴿١٦

16ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡

وَٱلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰٓ﴿١٧

17መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡

إِنَّ هَٰذَا لَفِي ٱلصُّحُفِ ٱلۡأُولَىٰ﴿١٨

18ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡

صُحُفِ إِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ﴿١٩

19በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡

RELATED SURAHS