Al-Ghashiyah

الغاشية

The Overwhelming26 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلۡغَٰشِيَةِ﴿١

1የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን?

وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٍ خَٰشِعَةٌ﴿٢

2ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡

عَامِلَةٞ نَّاصِبَةٞ﴿٣

3ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡

تَصۡلَىٰ نَارًا حَامِيَةٗ﴿٤

4ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡

تُسۡقَىٰ مِنۡ عَيۡنٍ ءَانِيَةٖ﴿٥

5በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡

لَّيۡسَ لَهُمۡ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٖ﴿٦

6ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡

لَّا يُسۡمِنُ وَلَا يُغۡنِي مِن جُوعٖ﴿٧

7የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡

وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ نَّاعِمَةٞ﴿٨

8ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡

لِّسَعۡيِهَا رَاضِيَةٞ﴿٩

9ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡

فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٖ﴿١٠

10በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡

لَّا تَسۡمَعُ فِيهَا لَٰغِيَةٗ﴿١١

11በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡

فِيهَا عَيۡنٞ جَارِيَةٞ﴿١٢

12በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡

فِيهَا سُرُرٞ مَّرۡفُوعَةٞ﴿١٣

13በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡

وَأَكۡوَابٞ مَّوۡضُوعَةٞ﴿١٤

14በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡

وَنَمَارِقُ مَصۡفُوفَةٞ﴿١٥

15የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡

وَزَرَابِيُّ مَبۡثُوثَةٌ﴿١٦

16የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡

أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى ٱلۡإِبِلِ كَيۡفَ خُلِقَتۡ﴿١٧

17(ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!

وَإِلَى ٱلسَّمَآءِ كَيۡفَ رُفِعَتۡ﴿١٨

18ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!

وَإِلَى ٱلۡجِبَالِ كَيۡفَ نُصِبَتۡ﴿١٩

19ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!

وَإِلَى ٱلۡأَرۡضِ كَيۡفَ سُطِحَتۡ﴿٢٠

20ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)

فَذَكِّرۡ إِنَّمَآ أَنتَ مُذَكِّرٞ﴿٢١

21አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡

لَّسۡتَ عَلَيۡهِم بِمُصَيۡطِرٍ﴿٢٢

22በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡

إِلَّا مَن تَوَلَّىٰ وَكَفَرَ﴿٢٣

23ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤

فَيُعَذِّبُهُ ٱللَّهُ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَكۡبَرَ﴿٢٤

24አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡

إِنَّ إِلَيۡنَآ إِيَابَهُمۡ﴿٢٥

25መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡

ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا حِسَابَهُم﴿٢٦

26ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡

RELATED SURAHS