Al-Fajr

الفجر

The Dawn30 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلۡفَجۡرِ﴿١

1በጎህ እምላለሁ፡፡

وَلَيَالٍ عَشۡرٖ﴿٢

2በዐሥር ሌሊቶችም፡፡

وَٱلشَّفۡعِ وَٱلۡوَتۡرِ﴿٣

3በጥንዱም በነጠላውም፡፡

وَٱلَّيۡلِ إِذَا يَسۡرِ﴿٤

4በሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ፡፡

هَلۡ فِي ذَٰلِكَ قَسَمٞ لِّذِي حِجۡرٍ﴿٥

5በዚህ (መሓላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሓላ አለበትን?

أَلَمۡ تَرَ كَيۡفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِعَادٍ﴿٦

6ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታውቅምን?

إِرَمَ ذَاتِ ٱلۡعِمَادِ﴿٧

7በኢረም በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፡፡

ٱلَّتِي لَمۡ يُخۡلَقۡ مِثۡلُهَا فِي ٱلۡبِلَٰدِ﴿٨

8በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በኾነችው፡፡

وَثَمُودَ ٱلَّذِينَ جَابُواْ ٱلصَّخۡرَ بِٱلۡوَادِ﴿٩

9በሰሙድም በእነዚያ በሸለቆው ቋጥኝን የቆረጡ በኾኑት፡፡

وَفِرۡعَوۡنَ ذِي ٱلۡأَوۡتَادِ﴿١٠

10በፈርዖንም ባለ ችካሎች በኾነው፡፡

ٱلَّذِينَ طَغَوۡاْ فِي ٱلۡبِلَٰدِ﴿١١

11በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፡፡

فَأَكۡثَرُواْ فِيهَا ٱلۡفَسَادَ﴿١٢

12በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በኾኑት (እንዴት እንደሠራ አታውቅምን?)

فَصَبَّ عَلَيۡهِمۡ رَبُّكَ سَوۡطَ عَذَابٍ﴿١٣

13በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው፡፡

إِنَّ رَبَّكَ لَبِٱلۡمِرۡصَادِ﴿١٤

14ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና፡፡

فَأَمَّا ٱلۡإِنسَٰنُ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ رَبُّهُۥ فَأَكۡرَمَهُۥ وَنَعَّمَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَكۡرَمَنِ﴿١٥

15ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡

وَأَمَّآ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ فَقَدَرَ عَلَيۡهِ رِزۡقَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَهَٰنَنِ﴿١٦

16በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡

كَلَّاۖ بَل لَّا تُكۡرِمُونَ ٱلۡيَتِيمَ﴿١٧

17ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፡፡

وَلَا تَحَٰٓضُّونَ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِينِ﴿١٨

18ድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፡፡

وَتَأۡكُلُونَ ٱلتُّرَاثَ أَكۡلٗا لَّمّٗا﴿١٩

19የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፡፡

وَتُحِبُّونَ ٱلۡمَالَ حُبّٗا جَمّٗا﴿٢٠

20ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡

كَلَّآۖ إِذَا دُكَّتِ ٱلۡأَرۡضُ دَكّٗا دَكّٗا﴿٢١

21ተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤

وَجَآءَ رَبُّكَ وَٱلۡمَلَكُ صَفّٗا صَفّٗا﴿٢٢

22መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) በመጣ ጊዜ፤

وَجِاْيٓءَ يَوۡمَئِذِۭ بِجَهَنَّمَۚ يَوۡمَئِذٖ يَتَذَكَّرُ ٱلۡإِنسَٰنُ وَأَنَّىٰ لَهُ ٱلذِّكۡرَىٰ﴿٢٣

23ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ?

يَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي قَدَّمۡتُ لِحَيَاتِي﴿٢٤

24«ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡

فَيَوۡمَئِذٖ لَّا يُعَذِّبُ عَذَابَهُۥٓ أَحَدٞ﴿٢٥

25በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡

وَلَا يُوثِقُ وَثَاقَهُۥٓ أَحَدٞ﴿٢٦

26የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፡፡

يَٰٓأَيَّتُهَا ٱلنَّفۡسُ ٱلۡمُطۡمَئِنَّةُ﴿٢٧

27(ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ!

ٱرۡجِعِيٓ إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةٗ مَّرۡضِيَّةٗ﴿٢٨

28«ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡

فَٱدۡخُلِي فِي عِبَٰدِي﴿٢٩

29«በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡

وَٱدۡخُلِي جَنَّتِي﴿٣٠

30ገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)፡፡

RELATED SURAHS