Al-Balad
البلد
The City • 20 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
لَآ أُقۡسِمُ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ﴿١﴾
1በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡
وَأَنتَ حِلُّۢ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ﴿٢﴾
2አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡
وَوَالِدٖ وَمَا وَلَدَ﴿٣﴾
3በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡
لَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ فِي كَبَدٍ﴿٤﴾
4ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡
أَيَحۡسَبُ أَن لَّن يَقۡدِرَ عَلَيۡهِ أَحَدٞ﴿٥﴾
5በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?
يَقُولُ أَهۡلَكۡتُ مَالٗا لُّبَدًا﴿٦﴾
6«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡
أَيَحۡسَبُ أَن لَّمۡ يَرَهُۥٓ أَحَدٌ﴿٧﴾
7አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?
أَلَمۡ نَجۡعَل لَّهُۥ عَيۡنَيۡنِ﴿٨﴾
8ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?
وَلِسَانٗا وَشَفَتَيۡنِ﴿٩﴾
9ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡
وَهَدَيۡنَٰهُ ٱلنَّجۡدَيۡنِ﴿١٠﴾
10ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?
فَلَا ٱقۡتَحَمَ ٱلۡعَقَبَةَ﴿١١﴾
11ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡعَقَبَةُ﴿١٢﴾
12ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
فَكُّ رَقَبَةٍ﴿١٣﴾
13(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡
أَوۡ إِطۡعَٰمٞ فِي يَوۡمٖ ذِي مَسۡغَبَةٖ﴿١٤﴾
14ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡
يَتِيمٗا ذَا مَقۡرَبَةٍ﴿١٥﴾
15የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤
أَوۡ مِسۡكِينٗا ذَا مَتۡرَبَةٖ﴿١٦﴾
16ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡
ثُمَّ كَانَ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلصَّبۡرِ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلۡمَرۡحَمَةِ﴿١٧﴾
17ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች ጋር መሆን ነው፡፡
أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ﴿١٨﴾
18እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا هُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ﴿١٩﴾
19እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
عَلَيۡهِمۡ نَارٞ مُّؤۡصَدَةُۢ﴿٢٠﴾
20በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡