Az-Zalzalah

الزلزلة

The Earthquake8 ayahsMedinan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

إِذَا زُلۡزِلَتِ ٱلۡأَرۡضُ زِلۡزَالَهَا﴿١

1ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤

وَأَخۡرَجَتِ ٱلۡأَرۡضُ أَثۡقَالَهَا﴿٢

2ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤

وَقَالَ ٱلۡإِنسَٰنُ مَا لَهَا﴿٣

3ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤

يَوۡمَئِذٖ تُحَدِّثُ أَخۡبَارَهَا﴿٤

4በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡

بِأَنَّ رَبَّكَ أَوۡحَىٰ لَهَا﴿٥

5ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡

يَوۡمَئِذٖ يَصۡدُرُ ٱلنَّاسُ أَشۡتَاتٗا لِّيُرَوۡاْ أَعۡمَٰلَهُمۡ﴿٦

6በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡

فَمَن يَعۡمَلۡ مِثۡقَالَ ذَرَّةٍ خَيۡرٗا يَرَهُۥ﴿٧

7የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

وَمَن يَعۡمَلۡ مِثۡقَالَ ذَرَّةٖ شَرّٗا يَرَهُۥ﴿٨

8የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

RELATED SURAHS