Al-'Adiyat

العاديات

The Chargers11 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلۡعَٰدِيَٰتِ ضَبۡحٗا﴿١

1እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡

فَٱلۡمُورِيَٰتِ قَدۡحٗا﴿٢

2(በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤

فَٱلۡمُغِيرَٰتِ صُبۡحٗا﴿٣

3በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤

فَأَثَرۡنَ بِهِۦ نَقۡعٗا﴿٤

4በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤

فَوَسَطۡنَ بِهِۦ جَمۡعًا﴿٥

5በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡

إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لِرَبِّهِۦ لَكَنُودٞ﴿٦

6ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡

وَإِنَّهُۥ عَلَىٰ ذَٰلِكَ لَشَهِيدٞ﴿٧

7እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡

وَإِنَّهُۥ لِحُبِّ ٱلۡخَيۡرِ لَشَدِيدٌ﴿٨

8እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡

۞ أَفَلَا يَعۡلَمُ إِذَا بُعۡثِرَ مَا فِي ٱلۡقُبُورِ﴿٩

9(ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤

وَحُصِّلَ مَا فِي ٱلصُّدُورِ﴿١٠

10በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡

إِنَّ رَبَّهُم بِهِمۡ يَوۡمَئِذٖ لَّخَبِيرُۢ﴿١١

11ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡

RELATED SURAHS