An-Naba

النبأ

The Tidings40 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

عَمَّ يَتَسَآءَلُونَ﴿١

1ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?

عَنِ ٱلنَّبَإِ ٱلۡعَظِيمِ﴿٢

2ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡

ٱلَّذِي هُمۡ فِيهِ مُخۡتَلِفُونَ﴿٣

3ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡

كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ﴿٤

4ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡

ثُمَّ كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ﴿٥

5ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡

أَلَمۡ نَجۡعَلِ ٱلۡأَرۡضَ مِهَٰدٗا﴿٦

6ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን?

وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادٗا﴿٧

7ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን?

وَخَلَقۡنَٰكُمۡ أَزۡوَٰجٗا﴿٨

8ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡

وَجَعَلۡنَا نَوۡمَكُمۡ سُبَاتٗا﴿٩

9እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡

وَجَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ لِبَاسٗا﴿١٠

10ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡

وَجَعَلۡنَا ٱلنَّهَارَ مَعَاشٗا﴿١١

11ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡

وَبَنَيۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعٗا شِدَادٗا﴿١٢

12ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡

وَجَعَلۡنَا سِرَاجٗا وَهَّاجٗا﴿١٣

13አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡

وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡمُعۡصِرَٰتِ مَآءٗ ثَجَّاجٗا﴿١٤

14ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡

لِّنُخۡرِجَ بِهِۦ حَبّٗا وَنَبَاتٗا﴿١٥

15በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡

وَجَنَّٰتٍ أَلۡفَافًا﴿١٦

16የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡

إِنَّ يَوۡمَ ٱلۡفَصۡلِ كَانَ مِيقَٰتٗا﴿١٧

17የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡

يَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِ فَتَأۡتُونَ أَفۡوَاجٗا﴿١٨

18በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡

وَفُتِحَتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ أَبۡوَٰبٗا﴿١٩

19ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡

وَسُيِّرَتِ ٱلۡجِبَالُ فَكَانَتۡ سَرَابًا﴿٢٠

20ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡

إِنَّ جَهَنَّمَ كَانَتۡ مِرۡصَادٗا﴿٢١

21ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡

لِّلطَّٰغِينَ مَـَٔابٗا﴿٢٢

22ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡

لَّٰبِثِينَ فِيهَآ أَحۡقَابٗا﴿٢٣

23በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤

لَّا يَذُوقُونَ فِيهَا بَرۡدٗا وَلَا شَرَابًا﴿٢٤

24በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡

إِلَّا حَمِيمٗا وَغَسَّاقٗا﴿٢٥

25ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡

جَزَآءٗ وِفَاقًا﴿٢٦

26ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡

إِنَّهُمۡ كَانُواْ لَا يَرۡجُونَ حِسَابٗا﴿٢٧

27እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡

وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا كِذَّابٗا﴿٢٨

28በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡

وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ كِتَٰبٗا﴿٢٩

29ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡

فَذُوقُواْ فَلَن نَّزِيدَكُمۡ إِلَّا عَذَابًا﴿٣٠

30ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡

إِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ مَفَازًا﴿٣١

31ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡

حَدَآئِقَ وَأَعۡنَٰبٗا﴿٣٢

32አትክልቶችና ወይኖችም፡፡

وَكَوَاعِبَ أَتۡرَابٗا﴿٣٣

33እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡

وَكَأۡسٗا دِهَاقٗا﴿٣٤

34የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡

لَّا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوٗا وَلَا كِذَّٰبٗا﴿٣٥

35በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡

جَزَآءٗ مِّن رَّبِّكَ عَطَآءً حِسَابٗا﴿٣٦

36ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡

رَّبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا ٱلرَّحۡمَٰنِۖ لَا يَمۡلِكُونَ مِنۡهُ خِطَابٗا﴿٣٧

37የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡

يَوۡمَ يَقُومُ ٱلرُّوحُ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ صَفّٗاۖ لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنۡ أَذِنَ لَهُ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَقَالَ صَوَابٗا﴿٣٨

38መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡

ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ مَـَٔابًا﴿٣٩

39ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡

إِنَّآ أَنذَرۡنَٰكُمۡ عَذَابٗا قَرِيبٗا يَوۡمَ يَنظُرُ ٱلۡمَرۡءُ مَا قَدَّمَتۡ يَدَاهُ وَيَقُولُ ٱلۡكَافِرُ يَٰلَيۡتَنِي كُنتُ تُرَٰبَۢا﴿٤٠

40እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡

RELATED SURAHS