Al-Mursalat
المرسلات
Those Sent Forth • 50 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلۡمُرۡسَلَٰتِ عُرۡفٗا﴿١﴾
1ተከታታይ ኾነው በተላኩት፣
فَٱلۡعَٰصِفَٰتِ عَصۡفٗا﴿٢﴾
2በኀይል መንፈስን ነፋሾች በኾኑትም፣
وَٱلنَّٰشِرَٰتِ نَشۡرٗا﴿٣﴾
3መበተንን በታኞች በኾኑትም፤ (ነፋሶች)፣
فَٱلۡفَٰرِقَٰتِ فَرۡقٗا﴿٤﴾
4መለየትን ለይዎች በኾኑትም፣
فَٱلۡمُلۡقِيَٰتِ ذِكۡرًا﴿٥﴾
5መገሠጫን (ወደ ነቢያት) ጣይዎች በኾኑትም፣
عُذۡرًا أَوۡ نُذۡرًا﴿٦﴾
6ምክንያትን ለማስወገድ ወይም ለማስፈራራት (ጣይዎች በኾኑት መላእክት) እምላለሁ፡፡
إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَوَٰقِعٞ﴿٧﴾
7ያ የምትስፈራሩበት (ትንሣኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው፡፡
فَإِذَا ٱلنُّجُومُ طُمِسَتۡ﴿٨﴾
8ከዋክብትም (ብርሃንዋ) በታበሰች ጊዜ፡፡
وَإِذَا ٱلسَّمَآءُ فُرِجَتۡ﴿٩﴾
9ሰማይም በተከፈተች ጊዜ፡፡
وَإِذَا ٱلۡجِبَالُ نُسِفَتۡ﴿١٠﴾
10ጋራዎችም በተንኮተኮቱ ጊዜ፡፡
وَإِذَا ٱلرُّسُلُ أُقِّتَتۡ﴿١١﴾
11መልክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፡፡
لِأَيِّ يَوۡمٍ أُجِّلَتۡ﴿١٢﴾
12ለየትኛው ቀን ተቀጠሩ (የሚባል ሲኾን)፤
لِيَوۡمِ ٱلۡفَصۡلِ﴿١٣﴾
13ለመለያው ቀን (በተባለ ጊዜ፤ በፍጡሮች መካከል ይፈረዳል)፡፡
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِ﴿١٤﴾
14የመለያውም ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿١٥﴾
15ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ [1]
أَلَمۡ نُهۡلِكِ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿١٦﴾
16የፊተኞቹን (ሕዝቦች) አላጠፋንምን?
ثُمَّ نُتۡبِعُهُمُ ٱلۡأٓخِرِينَ﴿١٧﴾
17ከዚያም የኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን፡፡
كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ﴿١٨﴾
18በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿١٩﴾
19ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
أَلَمۡ نَخۡلُقكُّم مِّن مَّآءٖ مَّهِينٖ﴿٢٠﴾
20ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን?
فَجَعَلۡنَٰهُ فِي قَرَارٖ مَّكِينٍ﴿٢١﴾
21በተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በማሕፀን) አደረግነው፡፡
إِلَىٰ قَدَرٖ مَّعۡلُومٖ﴿٢٢﴾
22እስከ ታወቀ ልክ ድረስ፡፡
فَقَدَرۡنَا فَنِعۡمَ ٱلۡقَٰدِرُونَ﴿٢٣﴾
23መጠንነውም፤ ምን ያማርንም መጣኞች ነን!
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿٢٤﴾
24ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
أَلَمۡ نَجۡعَلِ ٱلۡأَرۡضَ كِفَاتًا﴿٢٥﴾
25ምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን?
أَحۡيَآءٗ وَأَمۡوَٰتٗا﴿٢٦﴾
26ሕያዋን ኾናችሁ ሙታንም ኾናችሁ፡፡
وَجَعَلۡنَا فِيهَا رَوَٰسِيَ شَٰمِخَٰتٖ وَأَسۡقَيۡنَٰكُم مَّآءٗ فُرَاتٗا﴿٢٧﴾
27በውስጧም ከፍተኛዎችን ተራራዎች አደረግን፡፡ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ፡፡
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿٢٨﴾
28ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
ٱنطَلِقُوٓاْ إِلَىٰ مَا كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ﴿٢٩﴾
29«ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት (ቅጣት) አዝግሙ፡፡
ٱنطَلِقُوٓاْ إِلَىٰ ظِلّٖ ذِي ثَلَٰثِ شُعَبٖ﴿٣٠﴾
30«ባለ ሦስት ቅርንጫፎች ወደ ኾነው ጥላ አዝግሙ፤» (ይባላሉ)፡፡
لَّا ظَلِيلٖ وَلَا يُغۡنِي مِنَ ٱللَّهَبِ﴿٣١﴾
31አጠላይ ያልኾነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ኾነው (አዝግሙ)፡፡
إِنَّهَا تَرۡمِي بِشَرَرٖ كَٱلۡقَصۡرِ﴿٣٢﴾
32እርሷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ የኾኑን ቃንቄዎች ትወረውራለች፡፡
كَأَنَّهُۥ جِمَٰلَتٞ صُفۡرٞ﴿٣٣﴾
33(ቃንቄውም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል፡፡
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿٣٤﴾
34ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
هَٰذَا يَوۡمُ لَا يَنطِقُونَ﴿٣٥﴾
35ይህ የማይናገሩበት ቀን ነው፡፡
وَلَا يُؤۡذَنُ لَهُمۡ فَيَعۡتَذِرُونَ﴿٣٦﴾
36ይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ፤ ለእነርሱ አይፈቀድላቸውም፡፡
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿٣٧﴾
37ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
هَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِۖ جَمَعۡنَٰكُمۡ وَٱلۡأَوَّلِينَ﴿٣٨﴾
38ይህ መለያው ቀን ነው፡፡ እናንተንም የፊተኞቹንም ሰብሰብናችሁ፡፡
فَإِن كَانَ لَكُمۡ كَيۡدٞ فَكِيدُونِ﴿٣٩﴾
39ለናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ፡፡
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿٤٠﴾
40ላስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي ظِلَٰلٖ وَعُيُونٖ﴿٤١﴾
41ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
وَفَوَٰكِهَ مِمَّا يَشۡتَهُونَ﴿٤٢﴾
42ከሚከጅሉትም ሁሉ በፍራፍሬዎች ውስጥ ናቸው፡፡
كُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ هَنِيٓـَٔۢا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ﴿٤٣﴾
43«ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ﴿٤٤﴾
44እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿٤٥﴾
45ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
كُلُواْ وَتَمَتَّعُواْ قَلِيلًا إِنَّكُم مُّجۡرِمُونَ﴿٤٦﴾
46ብሉ፤ ጥቂትንም (ጊዜ) ተጠቀሙ፡፡ እናንተ አመጸኞች ናችሁና፡፡
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿٤٧﴾
47ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱرۡكَعُواْ لَا يَرۡكَعُونَ﴿٤٨﴾
48«ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም፡፡
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ﴿٤٩﴾
49ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
فَبِأَيِّ حَدِيثِۭ بَعۡدَهُۥ يُؤۡمِنُونَ﴿٥٠﴾
50ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?