Al-Layl

الليل

The Night21 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلَّيۡلِ إِذَا يَغۡشَىٰ﴿١

1በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡

وَٱلنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّىٰ﴿٢

2በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡

وَمَا خَلَقَ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰٓ﴿٣

3ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡

إِنَّ سَعۡيَكُمۡ لَشَتَّىٰ﴿٤

4ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡

فَأَمَّا مَنۡ أَعۡطَىٰ وَٱتَّقَىٰ﴿٥

5የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡

وَصَدَّقَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ﴿٦

6በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤

فَسَنُيَسِّرُهُۥ لِلۡيُسۡرَىٰ﴿٧

7ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡

وَأَمَّا مَنۢ بَخِلَ وَٱسۡتَغۡنَىٰ﴿٨

8የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤

وَكَذَّبَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ﴿٩

9በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤

فَسَنُيَسِّرُهُۥ لِلۡعُسۡرَىٰ﴿١٠

10ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡

وَمَا يُغۡنِي عَنۡهُ مَالُهُۥٓ إِذَا تَرَدَّىٰٓ﴿١١

11በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡

إِنَّ عَلَيۡنَا لَلۡهُدَىٰ﴿١٢

12ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡

وَإِنَّ لَنَا لَلۡأٓخِرَةَ وَٱلۡأُولَىٰ﴿١٣

13መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡

فَأَنذَرۡتُكُمۡ نَارٗا تَلَظَّىٰ﴿١٤

14የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡

لَا يَصۡلَىٰهَآ إِلَّا ٱلۡأَشۡقَى﴿١٥

15ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡

ٱلَّذِي كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ﴿١٦

16ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡

وَسَيُجَنَّبُهَا ٱلۡأَتۡقَى﴿١٧

17አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡

ٱلَّذِي يُؤۡتِي مَالَهُۥ يَتَزَكَّىٰ﴿١٨

18ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡

وَمَا لِأَحَدٍ عِندَهُۥ مِن نِّعۡمَةٖ تُجۡزَىٰٓ﴿١٩

19ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡

إِلَّا ٱبۡتِغَآءَ وَجۡهِ رَبِّهِ ٱلۡأَعۡلَىٰ﴿٢٠

20ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡

وَلَسَوۡفَ يَرۡضَىٰ﴿٢١

21ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡

RELATED SURAHS