Ad-Duha
الضحى
The Morning Hours • 11 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلضُّحَىٰ﴿١﴾
1በረፋዱ እምላለሁ፡፡
وَٱلَّيۡلِ إِذَا سَجَىٰ﴿٢﴾
2በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤
مَا وَدَّعَكَ رَبُّكَ وَمَا قَلَىٰ﴿٣﴾
3ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡
وَلَلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٞ لَّكَ مِنَ ٱلۡأُولَىٰ﴿٤﴾
4መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡
وَلَسَوۡفَ يُعۡطِيكَ رَبُّكَ فَتَرۡضَىٰٓ﴿٥﴾
5ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡
أَلَمۡ يَجِدۡكَ يَتِيمٗا فَـَٔاوَىٰ﴿٦﴾
6የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡
وَوَجَدَكَ ضَآلّٗا فَهَدَىٰ﴿٧﴾
7የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡
وَوَجَدَكَ عَآئِلٗا فَأَغۡنَىٰ﴿٨﴾
8ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡
فَأَمَّا ٱلۡيَتِيمَ فَلَا تَقۡهَرۡ﴿٩﴾
9የቲምንማ አትጨቁን፡፡
وَأَمَّا ٱلسَّآئِلَ فَلَا تَنۡهَرۡ﴿١٠﴾
10ለማኝንም አትገላምጥ፡፡
وَأَمَّا بِنِعۡمَةِ رَبِّكَ فَحَدِّثۡ﴿١١﴾
11በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡