الشرح
The Relief • 8 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1ልብህን ለአንተ አላሰፋንልህምን? (አስፍተንልሃል)፡፡
2ሸክምህንም ካንተ አውርደንልሃል፡፡
3ያንን ጀርባህን ያከበደውን (ሸክም)፡፡
4መወሳትህንም ላንተ ከፍ አድርገንልሃል፡፡
5ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡
6ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
7በጨረስክም ጊዜ ልፋ፡፡ (ቀጥል)፡፡
8ወደ ጌታህም ብቻ ከጅል፡፡