At-Tin
التين
The Fig • 8 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلتِّينِ وَٱلزَّيۡتُونِ﴿١﴾
1በበለስና በዘይት ወይራ እምላለሁ፡፡
وَطُورِ سِينِينَ﴿٢﴾
2በሲኒን ተራራም፤
وَهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ ٱلۡأَمِينِ﴿٣﴾
3በዚህ በጸጥተኛው አገርም (እምላለሁ)፡፡
لَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ فِيٓ أَحۡسَنِ تَقۡوِيمٖ﴿٤﴾
4ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው፡፡
ثُمَّ رَدَدۡنَٰهُ أَسۡفَلَ سَٰفِلِينَ﴿٥﴾
5ከዚያም (ከፊሉን) ከዝቅተኞች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው፡፡
إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَلَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونٖ﴿٦﴾
6ግን እነዚያ ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት ለእነርሱ ተቆራጭ ያልኾነ ምንዳ አልላቸው፡፡
فَمَا يُكَذِّبُكَ بَعۡدُ بِٱلدِّينِ﴿٧﴾
7ታዲያ ከዚህ በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?
أَلَيۡسَ ٱللَّهُ بِأَحۡكَمِ ٱلۡحَٰكِمِينَ﴿٨﴾
8አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? (ነው)፡፡