Al-'Alaq
العلق
The Clot • 19 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
ٱقۡرَأۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلَّذِي خَلَقَ﴿١﴾
1አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡[1]
خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِنۡ عَلَقٍ﴿٢﴾
2ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
ٱقۡرَأۡ وَرَبُّكَ ٱلۡأَكۡرَمُ﴿٣﴾
3አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
ٱلَّذِي عَلَّمَ بِٱلۡقَلَمِ﴿٤﴾
4ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
عَلَّمَ ٱلۡإِنسَٰنَ مَا لَمۡ يَعۡلَمۡ﴿٥﴾
5ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
كَلَّآ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَيَطۡغَىٰٓ﴿٦﴾
6በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
أَن رَّءَاهُ ٱسۡتَغۡنَىٰٓ﴿٧﴾
7ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡
إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلرُّجۡعَىٰٓ﴿٨﴾
8መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
أَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي يَنۡهَىٰ﴿٩﴾
9አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡
عَبۡدًا إِذَا صَلَّىٰٓ﴿١٠﴾
10ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤
أَرَءَيۡتَ إِن كَانَ عَلَى ٱلۡهُدَىٰٓ﴿١١﴾
11አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤
أَوۡ أَمَرَ بِٱلتَّقۡوَىٰٓ﴿١٢﴾
12ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤
أَرَءَيۡتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰٓ﴿١٣﴾
13አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤
أَلَمۡ يَعۡلَم بِأَنَّ ٱللَّهَ يَرَىٰ﴿١٤﴾
14አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?
كَلَّا لَئِن لَّمۡ يَنتَهِ لَنَسۡفَعَۢا بِٱلنَّاصِيَةِ﴿١٥﴾
15ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡
نَاصِيَةٖ كَٰذِبَةٍ خَاطِئَةٖ﴿١٦﴾
16ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡
فَلۡيَدۡعُ نَادِيَهُۥ﴿١٧﴾
17ሸንጎውንም ይጥራ፡፡
سَنَدۡعُ ٱلزَّبَانِيَةَ﴿١٨﴾
18(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡
كَلَّا لَا تُطِعۡهُ وَٱسۡجُدۡۤ وَٱقۡتَرِب۩﴿١٩﴾
19ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡ [1]