Al-Muddaththir

المدثر

The Cloaked One56 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمُدَّثِّرُ﴿١

1አንተ (ልብስህን) ደራቢው ሆይ!

قُمۡ فَأَنذِرۡ﴿٢

2ተነሳ አስጠንቅቅም፡፡

وَرَبَّكَ فَكَبِّرۡ﴿٣

3ጌታህንም አክብር፡፡

وَثِيَابَكَ فَطَهِّرۡ﴿٤

4ልብስህንም አጥራ፡፡

وَٱلرُّجۡزَ فَٱهۡجُرۡ﴿٥

5ጣዖትንም ራቅ፡፡

وَلَا تَمۡنُن تَسۡتَكۡثِرُ﴿٦

6ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ፤ (በረከትን) አትለግስ።

وَلِرَبِّكَ فَٱصۡبِرۡ﴿٧

7ለጌታህም (ትዕዛዝ) ታገሥ፡፡

فَإِذَا نُقِرَ فِي ٱلنَّاقُورِ﴿٨

8በቀንዱም በተነፋ ጊዜ (ነገሩ ይበረታል)፡፡

فَذَٰلِكَ يَوۡمَئِذٖ يَوۡمٌ عَسِيرٌ﴿٩

9ይህም (ጊዜ) ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡

عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ غَيۡرُ يَسِيرٖ﴿١٠

10በከሓዲዎች ላይ ገር ያልኾነ ነው፡፡

ذَرۡنِي وَمَنۡ خَلَقۡتُ وَحِيدٗا﴿١١

11አንድ ኾኖ ከፈጠርኩት ሰው ጋር ተዎኝ (እኔ እበቃሃለሁ)፡፡

وَجَعَلۡتُ لَهُۥ مَالٗا مَّمۡدُودٗا﴿١٢

12ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በያይነቱ) ያደረግሁለት፡፡

وَبَنِينَ شُهُودٗا﴿١٣

13(በያደባባዩ) ተገኝዎች የኾኑ ወንዶች ልጆችንም፡፡

وَمَهَّدتُّ لَهُۥ تَمۡهِيدٗا﴿١٤

14ለእርሱም (ኑሮውን) መዘርጋትን የዘረጋሁለት (ከኾነ ሰው ገር ተዎኝ)፡፡

ثُمَّ يَطۡمَعُ أَنۡ أَزِيدَ﴿١٥

15ከዚያም ልጨምርለት ይከጅላል፡፡

كَلَّآۖ إِنَّهُۥ كَانَ لِأٓيَٰتِنَا عَنِيدٗا﴿١٦

16ይከልከል፤ እርሱ ለአንቀጾቻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበር፡፡

سَأُرۡهِقُهُۥ صَعُودًا﴿١٧

17በእርግጥ ችግርን አስገድደዋለሁ፡፡

إِنَّهُۥ فَكَّرَ وَقَدَّرَ﴿١٨

18እርሱ (በቁርኣን ነገር) ሐሰበ፤ ገመተም፡፡

فَقُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ﴿١٩

19ተረገመም፤ እንዴት ገመተ!

ثُمَّ قُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ﴿٢٠

20ከዚያም (ከሞት በኋላ) ተረገመ፡፡ እንዴት ገመተ!

ثُمَّ نَظَرَ﴿٢١

21ከዚያም እንደ ገና (በቁርኣኑ ነገር) ተመለከተ፡፡

ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ﴿٢٢

22ከዚያም ፊቱን አጨፈገገ፤ አኮማተረም፡፡

ثُمَّ أَدۡبَرَ وَٱسۡتَكۡبَرَ﴿٢٣

23ከዚያም (ከማመን) ዞረ፤ ኮራም፡፡

فَقَالَ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ يُؤۡثَرُ﴿٢٤

24አለም «ይህ (ከሌላ) የሚቀዳ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም፡፡

إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا قَوۡلُ ٱلۡبَشَرِ﴿٢٥

25«ይህ የሰው ቃል እንጅ ሌላ አይደለም፡፡»

سَأُصۡلِيهِ سَقَرَ﴿٢٦

26በሰቀር ውስጥ በእርግጥ አገባዋለሁ፡፡

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سَقَرُ﴿٢٧

27ሰቀር ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?

لَا تُبۡقِي وَلَا تَذَرُ﴿٢٨

28(ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም አትተውምም፡፡

لَوَّاحَةٞ لِّلۡبَشَرِ﴿٢٩

29ቆዳን በጣም አክሳይ ናት፡፡

عَلَيۡهَا تِسۡعَةَ عَشَرَ﴿٣٠

30በእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት፡፡

وَمَا جَعَلۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلنَّارِ إِلَّا مَلَٰٓئِكَةٗۖ وَمَا جَعَلۡنَا عِدَّتَهُمۡ إِلَّا فِتۡنَةٗ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيَسۡتَيۡقِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَيَزۡدَادَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِيمَٰنٗا وَلَا يَرۡتَابَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَلِيَقُولَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ وَٱلۡكَٰفِرُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَمَا يَعۡلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكۡرَىٰ لِلۡبَشَرِ﴿٣١

31የእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም፡፡ ቁጥራቸውንም ለእነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም፡፡ እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት እንዲያረጋግጡ፣ እነዚያም ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፣ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምእምናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፣ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው (መናፍቃን)፣ ከሓዲዎችም አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል? እንዲሉ (እንጅ አላደረግንም)፡፡ እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም፡፡ እርሷም (የሰቀር እሳት) ለሰዎች መገሰጫ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡

كَلَّا وَٱلۡقَمَرِ﴿٣٢

32(ከክህደት) ይከልከሉ፡፡ በጨረቃ እምላለሁ፡፡

وَٱلَّيۡلِ إِذۡ أَدۡبَرَ﴿٣٣

33በሌሊቱም በኼደ ጊዜ፡፡

وَٱلصُّبۡحِ إِذَآ أَسۡفَرَ﴿٣٤

34በንጋቱም ባበራ ጊዜ፡፡

إِنَّهَا لَإِحۡدَى ٱلۡكُبَرِ﴿٣٥

35እርሷ (ሰቀር) ከታላላቆቹ (አደጋዎች) አንዷ ናት፡፡

نَذِيرٗا لِّلۡبَشَرِ﴿٣٦

36ለሰዎች አስፈራሪ ስትኾን፡፡

لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَتَقَدَّمَ أَوۡ يَتَأَخَّرَ﴿٣٧

37ከእናንተ (ወደ በጎ ነገር) መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለሻ ሰው (አስፈራሪ ስትኾኑ)፡፡

كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا كَسَبَتۡ رَهِينَةٌ﴿٣٨

38ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡

إِلَّآ أَصۡحَٰبَ ٱلۡيَمِينِ﴿٣٩

39የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡

فِي جَنَّٰتٖ يَتَسَآءَلُونَ﴿٤٠

40(እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡

عَنِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ﴿٤١

41ከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡

مَا سَلَكَكُمۡ فِي سَقَرَ﴿٤٢

42(ይሏቸዋልም) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?»

قَالُواْ لَمۡ نَكُ مِنَ ٱلۡمُصَلِّينَ﴿٤٣

43(እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡

وَلَمۡ نَكُ نُطۡعِمُ ٱلۡمِسۡكِينَ﴿٤٤

44«ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡

وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ ٱلۡخَآئِضِينَ﴿٤٥

45«ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡

وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ﴿٤٦

46«በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡

حَتَّىٰٓ أَتَىٰنَا ٱلۡيَقِينُ﴿٤٧

47«እርግጠኛው (ሞት) እስከ መጣን ድረስ፡፡»

فَمَا تَنفَعُهُمۡ شَفَٰعَةُ ٱلشَّٰفِعِينَ﴿٤٨

48የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡

فَمَا لَهُمۡ عَنِ ٱلتَّذۡكِرَةِ مُعۡرِضِينَ﴿٤٩

49ከግሣጼዬም (ከቁርኣን) የሚያፈገፍጉት ለእነርሱ ምን አልላቸው?

كَأَنَّهُمۡ حُمُرٞ مُّسۡتَنفِرَةٞ﴿٥٠

50እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዮች ይመስላሉ፡፡

فَرَّتۡ مِن قَسۡوَرَةِۭ﴿٥١

51ከዐንበሳ የሸሹ፡፡

بَلۡ يُرِيدُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُؤۡتَىٰ صُحُفٗا مُّنَشَّرَةٗ﴿٥٢

52ይልቁንም ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ የተዘረጉ ጽሑፎችን እንዲስሰጥ ይፈልጋል፡፡

كَلَّاۖ بَل لَّا يَخَافُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ﴿٥٣

53ይከልከሉ፡፡ ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) አይፈሩም፡፡

كَلَّآ إِنَّهُۥ تَذۡكِرَةٞ﴿٥٤

54ይከልከሉ፡፡ እርሱ (ቁርኣን) መገሠጫ ነው፡፡

فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ﴿٥٥

55ስለዚህ የሻ ሰው ይገሰጽበታል፡፡

وَمَا يَذۡكُرُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ هُوَ أَهۡلُ ٱلتَّقۡوَىٰ وَأَهۡلُ ٱلۡمَغۡفِرَةِ﴿٥٦

56አላህም ካልሻ በስተቀር አይገሠጹም፡፡ እርሱ (አላህ) የመፈራት ባለቤት የምሕረትም ባለቤት ነው፡፡

RELATED SURAHS