Al-Qiyamah
القيامة
The Resurrection • 40 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
لَآ أُقۡسِمُ بِيَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ﴿١﴾
1(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡
وَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلنَّفۡسِ ٱللَّوَّامَةِ﴿٢﴾
2(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَلَّن نَّجۡمَعَ عِظَامَهُۥ﴿٣﴾
3ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን?
بَلَىٰ قَٰدِرِينَ عَلَىٰٓ أَن نُّسَوِّيَ بَنَانَهُۥ﴿٤﴾
4አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡
بَلۡ يُرِيدُ ٱلۡإِنسَٰنُ لِيَفۡجُرَ أَمَامَهُۥ﴿٥﴾
5ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡
يَسۡـَٔلُ أَيَّانَ يَوۡمُ ٱلۡقِيَٰمَةِ﴿٦﴾
6«የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡
فَإِذَا بَرِقَ ٱلۡبَصَرُ﴿٧﴾
7ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡
وَخَسَفَ ٱلۡقَمَرُ﴿٨﴾
8ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡
وَجُمِعَ ٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ﴿٩﴾
9ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡
يَقُولُ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذٍ أَيۡنَ ٱلۡمَفَرُّ﴿١٠﴾
10«ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡
كَلَّا لَا وَزَرَ﴿١١﴾
11ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمُسۡتَقَرُّ﴿١٢﴾
12በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
يُنَبَّؤُاْ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذِۭ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ﴿١٣﴾
13ሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡
بَلِ ٱلۡإِنسَٰنُ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦ بَصِيرَةٞ﴿١٤﴾
14በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡
وَلَوۡ أَلۡقَىٰ مَعَاذِيرَهُۥ﴿١٥﴾
15ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡
لَا تُحَرِّكۡ بِهِۦ لِسَانَكَ لِتَعۡجَلَ بِهِۦٓ﴿١٦﴾
16በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡
إِنَّ عَلَيۡنَا جَمۡعَهُۥ وَقُرۡءَانَهُۥ﴿١٧﴾
17(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡
فَإِذَا قَرَأۡنَٰهُ فَٱتَّبِعۡ قُرۡءَانَهُۥ﴿١٨﴾
18ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡
ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا بَيَانَهُۥ﴿١٩﴾
19ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡
كَلَّا بَلۡ تُحِبُّونَ ٱلۡعَاجِلَةَ﴿٢٠﴾
20(ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡
وَتَذَرُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ﴿٢١﴾
21መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡
وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ نَّاضِرَةٌ﴿٢٢﴾
22ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡
إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٞ﴿٢٣﴾
23ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡
وَوُجُوهٞ يَوۡمَئِذِۭ بَاسِرَةٞ﴿٢٤﴾
24ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡
تَظُنُّ أَن يُفۡعَلَ بِهَا فَاقِرَةٞ﴿٢٥﴾
25በርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡
كَلَّآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلتَّرَاقِيَ﴿٢٦﴾
26ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤
وَقِيلَ مَنۡۜ رَاقٖ﴿٢٧﴾
27«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡
وَظَنَّ أَنَّهُ ٱلۡفِرَاقُ﴿٢٨﴾
28(ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡
وَٱلۡتَفَّتِ ٱلسَّاقُ بِٱلسَّاقِ﴿٢٩﴾
29ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمَسَاقُ﴿٣٠﴾
30በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ ነው፡፡
فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ﴿٣١﴾
31አላመነምም አልሰገደምም፡፡
وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ﴿٣٢﴾
32ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡
ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ يَتَمَطَّىٰٓ﴿٣٣﴾
33ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡
أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰ﴿٣٤﴾
34የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡
ثُمَّ أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰٓ﴿٣٥﴾
35ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡
أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَن يُتۡرَكَ سُدًى﴿٣٦﴾
36ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን?
أَلَمۡ يَكُ نُطۡفَةٗ مِّن مَّنِيّٖ يُمۡنَىٰ﴿٣٧﴾
37የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
ثُمَّ كَانَ عَلَقَةٗ فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ﴿٣٨﴾
38ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡
فَجَعَلَ مِنۡهُ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰٓ﴿٣٩﴾
39ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡
أَلَيۡسَ ذَٰلِكَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يُحۡـِۧيَ ٱلۡمَوۡتَىٰ﴿٤٠﴾
40ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?