Al-Ma'arij
المعارج
The Ascending Stairways • 44 ayahs • Meccan
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
سَأَلَ سَآئِلُۢ بِعَذَابٖ وَاقِعٖ﴿١﴾
1ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡
لِّلۡكَٰفِرِينَ لَيۡسَ لَهُۥ دَافِعٞ﴿٢﴾
2በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡
مِّنَ ٱللَّهِ ذِي ٱلۡمَعَارِجِ﴿٣﴾
3የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡
تَعۡرُجُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ إِلَيۡهِ فِي يَوۡمٖ كَانَ مِقۡدَارُهُۥ خَمۡسِينَ أَلۡفَ سَنَةٖ﴿٤﴾
4መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡
فَٱصۡبِرۡ صَبۡرٗا جَمِيلًا﴿٥﴾
5መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡
إِنَّهُمۡ يَرَوۡنَهُۥ بَعِيدٗا﴿٦﴾
6እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡
وَنَرَىٰهُ قَرِيبٗا﴿٧﴾
7እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡
يَوۡمَ تَكُونُ ٱلسَّمَآءُ كَٱلۡمُهۡلِ﴿٨﴾
8ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡
وَتَكُونُ ٱلۡجِبَالُ كَٱلۡعِهۡنِ﴿٩﴾
9ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡
وَلَا يَسۡـَٔلُ حَمِيمٌ حَمِيمٗا﴿١٠﴾
10ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡
يُبَصَّرُونَهُمۡۚ يَوَدُّ ٱلۡمُجۡرِمُ لَوۡ يَفۡتَدِي مِنۡ عَذَابِ يَوۡمِئِذِۭ بِبَنِيهِ﴿١١﴾
11(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡
وَصَٰحِبَتِهِۦ وَأَخِيهِ﴿١٢﴾
12በሚስቱም በወንድሙም፡፡
وَفَصِيلَتِهِ ٱلَّتِي تُـٔۡوِيهِ﴿١٣﴾
13በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡
وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا ثُمَّ يُنجِيهِ﴿١٤﴾
14በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡
كَلَّآۖ إِنَّهَا لَظَىٰ﴿١٥﴾
15ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡
نَزَّاعَةٗ لِّلشَّوَىٰ﴿١٦﴾
16የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡
تَدۡعُواْ مَنۡ أَدۡبَرَ وَتَوَلَّىٰ﴿١٧﴾
17(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡
وَجَمَعَ فَأَوۡعَىٰٓ﴿١٨﴾
18ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡
۞ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ خُلِقَ هَلُوعًا﴿١٩﴾
19ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡
إِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ جَزُوعٗا﴿٢٠﴾
20ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡
وَإِذَا مَسَّهُ ٱلۡخَيۡرُ مَنُوعًا﴿٢١﴾
21መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡
إِلَّا ٱلۡمُصَلِّينَ﴿٢٢﴾
22ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡
ٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ دَآئِمُونَ﴿٢٣﴾
23እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡
وَٱلَّذِينَ فِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقّٞ مَّعۡلُومٞ﴿٢٤﴾
24እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡
لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ﴿٢٥﴾
25ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡
وَٱلَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ﴿٢٦﴾
26እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡
وَٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ﴿٢٧﴾
27እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡
إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمۡ غَيۡرُ مَأۡمُونٖ﴿٢٨﴾
28የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ﴿٢٩﴾
29እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ﴿٣٠﴾
30በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡
فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ﴿٣١﴾
31ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ﴿٣٢﴾
32እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
وَٱلَّذِينَ هُم بِشَهَٰدَٰتِهِمۡ قَآئِمُونَ﴿٣٣﴾
33እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ يُحَافِظُونَ﴿٣٤﴾
34እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡
أُوْلَٰٓئِكَ فِي جَنَّٰتٖ مُّكۡرَمُونَ﴿٣٥﴾
35እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡
فَمَالِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ قِبَلَكَ مُهۡطِعِينَ﴿٣٦﴾
36ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?
عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ عِزِينَ﴿٣٧﴾
37ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡
أَيَطۡمَعُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُدۡخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٖ﴿٣٨﴾
38ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?
كَلَّآۖ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّمَّا يَعۡلَمُونَ﴿٣٩﴾
39ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡
فَلَآ أُقۡسِمُ بِرَبِّ ٱلۡمَشَٰرِقِ وَٱلۡمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ﴿٤٠﴾
40በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ خَيۡرٗا مِّنۡهُمۡ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ﴿٤١﴾
41ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
فَذَرۡهُمۡ يَخُوضُواْ وَيَلۡعَبُواْ حَتَّىٰ يُلَٰقُواْ يَوۡمَهُمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ﴿٤٢﴾
42ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡
يَوۡمَ يَخۡرُجُونَ مِنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ سِرَاعٗا كَأَنَّهُمۡ إِلَىٰ نُصُبٖ يُوفِضُونَ﴿٤٣﴾
43ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡
خَٰشِعَةً أَبۡصَٰرُهُمۡ تَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٞۚ ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلَّذِي كَانُواْ يُوعَدُونَ﴿٤٤﴾
44ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡