قَدۡ أَفۡلَحَ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ﴿١﴾
1ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡
ٱلَّذِينَ هُمۡ فِي صَلَاتِهِمۡ خَٰشِعُونَ﴿٢﴾
2እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَنِ ٱللَّغۡوِ مُعۡرِضُونَ﴿٣﴾
3እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِلزَّكَوٰةِ فَٰعِلُونَ﴿٤﴾
4እነዚያም እነርሱ ዘካን ሰጭዎች፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ﴿٥﴾
5እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡
إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ﴿٦﴾
6በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡
فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ﴿٧﴾
7ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ﴿٨﴾
8እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸውና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَوَٰتِهِمۡ يُحَافِظُونَ﴿٩﴾
9እነዚያም እነሱ በስግደቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁ የኸኑት (አገኙ)፡፡
أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡوَٰرِثُونَ﴿١٠﴾
10እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው፡፡
ٱلَّذِينَ يَرِثُونَ ٱلۡفِرۡدَوۡسَ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ﴿١١﴾
11እነዚያ ፊርደውስን (ላዕላይ ገነትን)፤ የሚወርሱ ናቸው፡፡ እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِن سُلَٰلَةٖ مِّن طِينٖ﴿١٢﴾
12በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፡፡
ثُمَّ جَعَلۡنَٰهُ نُطۡفَةٗ فِي قَرَارٖ مَّكِينٖ﴿١٣﴾
13ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው፡፡
ثُمَّ خَلَقۡنَا ٱلنُّطۡفَةَ عَلَقَةٗ فَخَلَقۡنَا ٱلۡعَلَقَةَ مُضۡغَةٗ فَخَلَقۡنَا ٱلۡمُضۡغَةَ عِظَٰمٗا فَكَسَوۡنَا ٱلۡعِظَٰمَ لَحۡمٗا ثُمَّ أَنشَأۡنَٰهُ خَلۡقًا ءَاخَرَۚ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ أَحۡسَنُ ٱلۡخَٰلِقِينَ﴿١٤﴾
14ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡
ثُمَّ إِنَّكُم بَعۡدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ﴿١٥﴾
15ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ፡፡
ثُمَّ إِنَّكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ تُبۡعَثُونَ﴿١٦﴾
16ከዚያም እናንተ በትንሣኤ ቀን ትቀሰቀሳላችሁ፡፡
وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعَ طَرَآئِقَ وَمَا كُنَّا عَنِ ٱلۡخَلۡقِ غَٰفِلِينَ﴿١٧﴾
17በእርግጥም ከበላያችሁ ሰባትን ሰማያት ፈጠርን፡፡ ከፍጥረቶቹም ዘንጊዎች አይደለንም፡፡
وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءَۢ بِقَدَرٖ فَأَسۡكَنَّٰهُ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَإِنَّا عَلَىٰ ذَهَابِۭ بِهِۦ لَقَٰدِرُونَ﴿١٨﴾
18ከሰማይም ውሃን በልክ አወረድን፡፡ በምድርም ውስጥ አስቀመጥነው፡፡ እኛም እርሱን በማስወገድ ላይ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
فَأَنشَأۡنَا لَكُم بِهِۦ جَنَّٰتٖ مِّن نَّخِيلٖ وَأَعۡنَٰبٖ لَّكُمۡ فِيهَا فَوَٰكِهُ كَثِيرَةٞ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ﴿١٩﴾
19በእርሱም ከዘምባባዎችና ከወይኖች የኾኑን አትክልቶች ለእናንተ አስገኘንላችሁ፡፡ በውስጧ ለእናንተ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁ፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡
وَشَجَرَةٗ تَخۡرُجُ مِن طُورِ سَيۡنَآءَ تَنۢبُتُ بِٱلدُّهۡنِ وَصِبۡغٖ لِّلۡأٓكِلِينَ﴿٢٠﴾
20ከሲና ተራራም የምትወጣን ዛፍ በቅባትና ለበይዎችም መባያ በሚኾን (ዘይት) ተቀላቅላ የምትበቅልን (አስገኘንላችሁ)፡፡
وَإِنَّ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَنۡعَٰمِ لَعِبۡرَةٗۖ نُّسۡقِيكُم مِّمَّا فِي بُطُونِهَا وَلَكُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ كَثِيرَةٞ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ﴿٢١﴾
21ለእናንተም በግመል፣ በከብት፣ በፍየልና በበግ መገምገሚያ አልላችሁ፡፡ በሆዶችዋ ውስጥ ካለው (ወተት) እናጠጣችኋለን፡፡ ለእናንተም በእርሷ ብዙ ጥቅሞች አሏችሁ፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡
وَعَلَيۡهَا وَعَلَى ٱلۡفُلۡكِ تُحۡمَلُونَ﴿٢٢﴾
22በእርሷም ላይ በመርከብም ላይ ትጫናላችሁ፡፡
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ﴿٢٣﴾
23ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ አትጠነቀቁምን?» አላቸው፡፡
فَقَالَ ٱلۡمَلَؤُاْ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يُرِيدُ أَن يَتَفَضَّلَ عَلَيۡكُمۡ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَأَنزَلَ مَلَٰٓئِكَةٗ مَّا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِيٓ ءَابَآئِنَا ٱلۡأَوَّلِينَ﴿٢٤﴾
24ከሕዝቦቹም እነዚያ ታላላቆቹ ሰዎች አሉ «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ በእናንተ ላይ መብለጥን ይፈልጋል፡፡ አላህም በሻ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር፡፡ ይህንንም (የሚለውን) በመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን አልሰማንም፡፡
إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلُۢ بِهِۦ جِنَّةٞ فَتَرَبَّصُواْ بِهِۦ حَتَّىٰ حِينٖ﴿٢٥﴾
25«እርሱ በእርሱ ዕብደት ያለበት ሰው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ በእርሱም እስከ ጊዜ (ሞቱ) ድረስ ተጠባበቁ» (አሉ)፡፡
قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ﴿٢٦﴾
26(ኑሕም) «ጌታዬ ሆይ! ባስተባበሉኝ ምክንያት እርዳኝ» አለ፡፡
فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِ أَنِ ٱصۡنَعِ ٱلۡفُلۡكَ بِأَعۡيُنِنَا وَوَحۡيِنَا فَإِذَا جَآءَ أَمۡرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ فَٱسۡلُكۡ فِيهَا مِن كُلّٖ زَوۡجَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِ وَأَهۡلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيۡهِ ٱلۡقَوۡلُ مِنۡهُمۡۖ وَلَا تُخَٰطِبۡنِي فِي ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ إِنَّهُم مُّغۡرَقُونَ﴿٢٧﴾
27ወደርሱም (እንዲህ ስንል) ላክን «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችንም ታንኳን ሥራ ት እዛዛችን በመጣና እቶኑ በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ሁለት ዓይነቶችን ቤተሰቦችህንም ከነሱ (ጠፊ በመኾን) ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር፤ አስገባ፡፡ በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታነጋግረኝ፡፡ እነሱ ተሰጣሚዎች ነቸውና፡፡
فَإِذَا ٱسۡتَوَيۡتَ أَنتَ وَمَن مَّعَكَ عَلَى ٱلۡفُلۡكِ فَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي نَجَّىٰنَا مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ﴿٢٨﴾
28አንተም አብረውህ ካሉት ጋር በታንኳይቱ ላይ በተደላደልክ ጊዜ «ምስጋና ለዚያ ከበደለኞች ሕዝቦች ላዳነን አላህ ይገባው» በል፡፡
وَقُل رَّبِّ أَنزِلۡنِي مُنزَلٗا مُّبَارَكٗا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡمُنزِلِينَ﴿٢٩﴾
29በልም «ጌታዬ ሆይ! ብሩክ የኾነን ማውረድ አውርደኝ፡፡ አንተም ከአውራጆች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ وَإِن كُنَّا لَمُبۡتَلِينَ﴿٣٠﴾
30በዚህ ውስጥ (ለከሃሊነታችን) ምልከቶች አልሉበት፡፡ እነሆ! (የኑሕን ሰዎች) በእርግጥም ፈትታኞች ነበርን፡፡
ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قَرۡنًا ءَاخَرِينَ﴿٣١﴾
31ከዚያም ከኋላቸው ሌሎችን የክፍለ ዘመን ሕዝቦች አስገኘን፡፡
فَأَرۡسَلۡنَا فِيهِمۡ رَسُولٗا مِّنۡهُمۡ أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ﴿٣٢﴾
32በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን በማለት ላክን፡፡
وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱلۡأٓخِرَةِ وَأَتۡرَفۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يَأۡكُلُ مِمَّا تَأۡكُلُونَ مِنۡهُ وَيَشۡرَبُ مِمَّا تَشۡرَبُونَ﴿٣٣﴾
33ከሕዝቦቹም እነዚያ የካዱት በመጨረሻይቱም ቀን መገናኘት ያስተባበሉት በቅርቢቱም ሕይወት ያቀማጠልናቸው ታላላቅ ሰዎች «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ከርሱ ከምትበሉት ምግብ ይበላል፡፡ ከምትጠጡትም ውሃ ይጠጣል» አሉ፡፡
وَلَئِنۡ أَطَعۡتُم بَشَرٗا مِّثۡلَكُمۡ إِنَّكُمۡ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ﴿٣٤﴾
34«ብጤያችሁም የኾነን ሰው ብትታዘዙ እናንተ ያን ጊዜ በእርግጥ የተሞኛችሁ ናቸሁ» (አሉ)፡፡
أَيَعِدُكُمۡ أَنَّكُمۡ إِذَا مِتُّمۡ وَكُنتُمۡ تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَنَّكُم مُّخۡرَجُونَ﴿٣٥﴾
35«እናንተ በሞታችሁና ዐፈርና አጥንቶችም በኾናችሁ ጊዜ እናንተ (ከመቃብር) ትወጣላችሁ በማለት ያስፈራራችኋልን?
۞ هَيۡهَاتَ هَيۡهَاتَ لِمَا تُوعَدُونَ﴿٣٦﴾
36«ያ የምትስፈራሩበት ነገር ራቀ፤ በጣም ራቀ፡፡
إِنۡ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا نَمُوتُ وَنَحۡيَا وَمَا نَحۡنُ بِمَبۡعُوثِينَ﴿٣٧﴾
37«እርሷ (ሕይወት) ቅርቢቱ ሕይወታችን እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ እንሞታለን፤ (ልጆቻችን ስለሚተኩ) ሕያውም እንኾናለን፡፡ እኛም ተቀስቃሾች አይደለንም፡፡
إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلٌ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗا وَمَا نَحۡنُ لَهُۥ بِمُؤۡمِنِينَ﴿٣٨﴾
38«እርሱ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እኛም ለእርሱ አማኞች አይደለንም» (አሉ)፡፡
قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ﴿٣٩﴾
39(መልክተኛውም) «ጌታዬ ሆይ! ስላስተባበሉኝ እርዳኝ» አለ፡፡
قَالَ عَمَّا قَلِيلٖ لَّيُصۡبِحُنَّ نَٰدِمِينَ﴿٤٠﴾
40(አላህም) «ከጥቂት ጊዜ በኋላ (በጥፋታቸው) በእርግጥ ተጸጻቾች ይኾናሉ» አለው፡፡
فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّيۡحَةُ بِٱلۡحَقِّ فَجَعَلۡنَٰهُمۡ غُثَآءٗۚ فَبُعۡدٗا لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ﴿٤١﴾
41ወዲያውም (የጥፋት) ጩኸቲቱ በእውነት ያዘቻቸው፡፡ እንደ ጎርፍ ግብስባሽም አደረግናቸው፡፡ ለበደለኞች ሕዝቦችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡
ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قُرُونًا ءَاخَرِينَ﴿٤٢﴾
42ከዚያም ከእነሱ በኋላ ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ሕዝቦች አስገኘን፡፡
مَا تَسۡبِقُ مِنۡ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ﴿٤٣﴾
43ማንኛይቱም ሕዝብ ጊዜያዋን አትቀድምም፤ አይቅቆዩምም፡፡
ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا رُسُلَنَا تَتۡرَاۖ كُلَّ مَا جَآءَ أُمَّةٗ رَّسُولُهَا كَذَّبُوهُۖ فَأَتۡبَعۡنَا بَعۡضَهُم بَعۡضٗا وَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَحَادِيثَۚ فَبُعۡدٗا لِّقَوۡمٖ لَّا يُؤۡمِنُونَ﴿٤٤﴾
44ከዚያም መልክተኞቻችንን የሚከታተሉ ኾነው ላክን፡፡ ማንኛይቱንም ሕዝብ መልክተኛዋ በመጣላት ቁጥር አስተባበሉት፡፡ ከፊላቸውንም በከፊሉ (በጥፋት) አስከታተለን፡፡ ወሬዎችም አደረግናቸው፡፡ ለማያምኑም ሕዝቦች (ከእዝነታችን) መራቅ ተገባቸው፡፡
ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَٰرُونَ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ﴿٤٥﴾
45ከዚያም ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላክን፡፡
إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمًا عَالِينَ﴿٤٦﴾
46ወደ ፈርዖንና ወደ ጭፍሮቹ (ላክናቸው)፡፡ ኮሩም፡፡ የተንበጣረሩ ሕዝቦችም ነበሩ፡፡
فَقَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ لِبَشَرَيۡنِ مِثۡلِنَا وَقَوۡمُهُمَا لَنَا عَٰبِدُونَ﴿٤٧﴾
47«ብጤያችንም ለኾኑ ሁለት ሰዎች ሕዝቦቻቸው ለእኛ ተገዢዎች ኾነው ሳሉ እናምናለን?» አሉ፡፡
فَكَذَّبُوهُمَا فَكَانُواْ مِنَ ٱلۡمُهۡلَكِينَ﴿٤٨﴾
48አስተባበሉዋቸውም፡፡ ከጠፊዎቹም ኾኑ፡፡
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ لَعَلَّهُمۡ يَهۡتَدُونَ﴿٤٩﴾
49ሙሳንም (ነገዶቹ) ይምመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡
وَجَعَلۡنَا ٱبۡنَ مَرۡيَمَ وَأُمَّهُۥٓ ءَايَةٗ وَءَاوَيۡنَٰهُمَآ إِلَىٰ رَبۡوَةٖ ذَاتِ قَرَارٖ وَمَعِينٖ﴿٥٠﴾
50የመርየምን ልጅና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው፡፡ የመደላደልና የምንጭ ባለቤት ወደ ኾነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلرُّسُلُ كُلُواْ مِنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَٱعۡمَلُواْ صَٰلِحًاۖ إِنِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ عَلِيمٞ﴿٥١﴾
51እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ፡፡
وَإِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَأَنَا۠ رَبُّكُمۡ فَٱتَّقُونِ﴿٥٢﴾
52ይህችም (በአንድ አምላክ የማመን ሕግጋት) አንድ መንገድ ስትኾን ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ፡፡
فَتَقَطَّعُوٓاْ أَمۡرَهُم بَيۡنَهُمۡ زُبُرٗاۖ كُلُّ حِزۡبِۭ بِمَا لَدَيۡهِمۡ فَرِحُونَ﴿٥٣﴾
53(ከዚያ ተከታዮቻቸው) የሃይማኖት ነገራቸውንም በመካከላቸው ክፍልፍሎች አድርገው ቆራረጡ፡፡ ሕዝብ ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳቾች ናቸው፡፡
فَذَرۡهُمۡ فِي غَمۡرَتِهِمۡ حَتَّىٰ حِينٍ﴿٥٤﴾
54እስከ ጊዜያቸውም ድረስ በጥምመታቸው ውስጥ ተዋቸው፡፡
أَيَحۡسَبُونَ أَنَّمَا نُمِدُّهُم بِهِۦ مِن مَّالٖ وَبَنِينَ﴿٥٥﴾
55ከገንዘብና ከልጆች በእርሱ የምንጨምርላቸውን ያስባሉን?
نُسَارِعُ لَهُمۡ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِۚ بَل لَّا يَشۡعُرُونَ﴿٥٦﴾
56በበጎ ነገሮች የምንቻኮልላቸው መኾንን (ያስባሉን) አይደለም፤ (ለማዘንጋት መኾኑን) አያውቁም፡፡
إِنَّ ٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ خَشۡيَةِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ﴿٥٧﴾
57እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ከመፍራት የተነሳ ተጨናቂዎች የኾኑት፡፡
وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ يُؤۡمِنُونَ﴿٥٨﴾
58እነዚያም እነርሱ በጌታቸው ተዓምራቶች ከሚያምኑት፡፡
وَٱلَّذِينَ هُم بِرَبِّهِمۡ لَا يُشۡرِكُونَ﴿٥٩﴾
59እነዚያም እነርሱ በጌታቸው (ጣዖትን) የማያጋሩት፡፡
وَٱلَّذِينَ يُؤۡتُونَ مَآ ءَاتَواْ وَّقُلُوبُهُمۡ وَجِلَةٌ أَنَّهُمۡ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ رَٰجِعُونَ﴿٦٠﴾
60እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መኾናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ኾነው የሚሰጡት፡፡
أُوْلَٰٓئِكَ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَهُمۡ لَهَا سَٰبِقُونَ﴿٦١﴾
61እነዚያ በመልካም ሥራዎች ይጣደፋሉ፡፡ እነሱም ለርሷ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡
وَلَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ وَلَدَيۡنَا كِتَٰبٞ يَنطِقُ بِٱلۡحَقِّ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ﴿٦٢﴾
62ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም፡፡ እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር መጽሐፍ አልለ፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
بَلۡ قُلُوبُهُمۡ فِي غَمۡرَةٖ مِّنۡ هَٰذَا وَلَهُمۡ أَعۡمَٰلٞ مِّن دُونِ ذَٰلِكَ هُمۡ لَهَا عَٰمِلُونَ﴿٦٣﴾
63በእውነቱ (ከሓዲዎች) ልቦቻቸው ከዚያ (መጽሐፍ) በዝንጋቴ ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነሱም ከዚህ ሌላ እነሱ ለርሷ ሠሪዎችዋ የኾኑ (መጥፎ) ሥራዎች አሏቸው፡፡
حَتَّىٰٓ إِذَآ أَخَذۡنَا مُتۡرَفِيهِم بِٱلۡعَذَابِ إِذَا هُمۡ يَجۡـَٔرُونَ﴿٦٤﴾
64ቅምጥሎቻቸውንም በቅጣት በያዝናቸው ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይወተውታሉ፡፡
لَا تَجۡـَٔرُواْ ٱلۡيَوۡمَۖ إِنَّكُم مِّنَّا لَا تُنصَرُونَ﴿٦٥﴾
65ዛሬ አትወትውቱ፤ እናንተ ከእኛ ዘንድ አትረዱም፡፡
قَدۡ كَانَتۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَكُنتُمۡ عَلَىٰٓ أَعۡقَٰبِكُمۡ تَنكِصُونَ﴿٦٦﴾
66አንቀጾቼ በእናንተ ላይ በእርግጥ ይነበቡላችሁ ነበር፡፡ በተረከዞቻችሁም ላይ ወደ ኋላችሁ ትመለሱ ነበራችሁ፡፡
مُسۡتَكۡبِرِينَ بِهِۦ سَٰمِرٗا تَهۡجُرُونَ﴿٦٧﴾
67በእርሱ (በክልሉ ቤት) ኩሩዎች ሌሊት ተጫዋቾች (ቁርኣንንም) የምትተው ኾናችሁ (ትመለሱ ነበራችሁ ይባላሉ)፡፡
أَفَلَمۡ يَدَّبَّرُواْ ٱلۡقَوۡلَ أَمۡ جَآءَهُم مَّا لَمۡ يَأۡتِ ءَابَآءَهُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿٦٨﴾
68(የቁርኣንን) ንግግሩንም አያስተነትኑምን ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን?
أَمۡ لَمۡ يَعۡرِفُواْ رَسُولَهُمۡ فَهُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ﴿٦٩﴾
69ወይስ መልክተኛቸውን አላወቁምን? ስለዚህ እነርሱ ለእርሱ ከሓዲዎች ናቸውን?
أَمۡ يَقُولُونَ بِهِۦ جِنَّةُۢۚ بَلۡ جَآءَهُم بِٱلۡحَقِّ وَأَكۡثَرُهُمۡ لِلۡحَقِّ كَٰرِهُونَ﴿٧٠﴾
70ወይስ በእርሱ ዕብደት አለበት ይላሉን? አይደለም፡፡ እውነትን ይዞ መጣላቸው፡፡ አብዛኞቻቸውም እውነትን ጠይዎች ናቸው፡፡
وَلَوِ ٱتَّبَعَ ٱلۡحَقُّ أَهۡوَآءَهُمۡ لَفَسَدَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهِنَّۚ بَلۡ أَتَيۡنَٰهُم بِذِكۡرِهِمۡ فَهُمۡ عَن ذِكۡرِهِم مُّعۡرِضُونَ﴿٧١﴾
71ሀቅ (አላህ) ዝንባሌዎቻቸውን በተከተለ ኖሮ ሰማያትና ምድር በውስጣቸውም ያለው ሁሉ በእርግጥ በተበላሸ ነበር፡፡ ይልቁንም ክብራቸው ያለበትን (ቁርኣን) አመጣንላቸው፡፡ እነርሱም ከክብራቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡
أَمۡ تَسۡـَٔلُهُمۡ خَرۡجٗا فَخَرَاجُ رَبِّكَ خَيۡرٞۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلرَّٰزِقِينَ﴿٧٢﴾
72ወይስ ግብርን ትጠይቃቸዋለህን? የጌታህም ችሮታ በላጭ ነው፡፡ እርሱም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
وَإِنَّكَ لَتَدۡعُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ﴿٧٣﴾
73አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትጠራቸዋለህ፡፡
وَإِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ عَنِ ٱلصِّرَٰطِ لَنَٰكِبُونَ﴿٧٤﴾
74እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ከትክክለኛው መንገድ ተዘንባዮች ናቸው፡፡
۞ وَلَوۡ رَحِمۡنَٰهُمۡ وَكَشَفۡنَا مَا بِهِم مِّن ضُرّٖ لَّلَجُّواْ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ﴿٧٥﴾
75ባዘንንላቸውና ከጉዳትም በእነርሱ ያለውን ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ የሚዋልሉ ኾነው ይዘወትሩ ነበር፡፡
وَلَقَدۡ أَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡعَذَابِ فَمَا ٱسۡتَكَانُواْ لِرَبِّهِمۡ وَمَا يَتَضَرَّعُونَ﴿٧٦﴾
76በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው፡፡ ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም፡፡ አይዋደቁምም፡፡
حَتَّىٰٓ إِذَا فَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَابٗا ذَا عَذَابٖ شَدِيدٍ إِذَا هُمۡ فِيهِ مُبۡلِسُونَ﴿٧٧﴾
77በእነሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የኾነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው፡፡
وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَۚ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ﴿٧٨﴾
78እርሱም ያ መስሚያዎችንና ማያዎችን ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፡፡ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡
وَهُوَ ٱلَّذِي ذَرَأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ﴿٧٩﴾
79እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው፡፡ ወደርሱም ትሰበሰባላችሁ፡፡
وَهُوَ ٱلَّذِي يُحۡيِۦ وَيُمِيتُ وَلَهُ ٱخۡتِلَٰفُ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ﴿٨٠﴾
80እርሱም ያ ሕያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው፡፡ የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው፡፡ አታውቁምን?
بَلۡ قَالُواْ مِثۡلَ مَا قَالَ ٱلۡأَوَّلُونَ﴿٨١﴾
81ይልቁንም (የመካ ከሓዲዎች) የፊተኞቹ ሕዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ፡፡
قَالُوٓاْ أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ﴿٨٢﴾
82«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶች በኾን ጊዜ እኛ ተቀስቃሾች ነን?» አሉ፡፡
لَقَدۡ وُعِدۡنَا نَحۡنُ وَءَابَآؤُنَا هَٰذَا مِن قَبۡلُ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿٨٣﴾
83«ይህንን እኛም ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፡፡ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» (አሉ)፡፡
قُل لِّمَنِ ٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهَآ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ﴿٨٤﴾
84«ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)» በላቸው፡፡
سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ﴿٨٥﴾
85«በእርግጥ የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ አትገሰጹምን?» በላቸው፡፡
قُلۡ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلسَّبۡعِ وَرَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ﴿٨٦﴾
86«የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው?» በላቸው፡፡
سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ﴿٨٧﴾
87«በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «እንግዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው፡፡
قُلۡ مَنۢ بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٖ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيۡهِ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ﴿٨٨﴾
88«የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡
سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ فَأَنَّىٰ تُسۡحَرُونَ﴿٨٩﴾
89«በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው፡፡
بَلۡ أَتَيۡنَٰهُم بِٱلۡحَقِّ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ﴿٩٠﴾
90ይልቁንም እውነትን አመጣንላቸው፡፡ እነርሱም (በመካዳቸው) ውሸታሞች ናቸው፡፡
مَا ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ مِن وَلَدٖ وَمَا كَانَ مَعَهُۥ مِنۡ إِلَٰهٍۚ إِذٗا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهِۭ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ﴿٩١﴾
91አላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላ አምላክ በነበረ) አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡
عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ﴿٩٢﴾
92ሩቁንና ቅርቡንም ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ (በእርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ፡፡
قُل رَّبِّ إِمَّا تُرِيَنِّي مَا يُوعَدُونَ﴿٩٣﴾
93(ሙሐመድ ሆይ!) በል «ጌታዬ ሆይ! የሚያስፈራሩበትን (ቅጣት) ብታሳየኝ፡፡
رَبِّ فَلَا تَجۡعَلۡنِي فِي ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ﴿٩٤﴾
94«ጌታዬ ሆይ! በበደለኞች ሕዝቦች ውስጥ አታድርገኝ፡፡»
وَإِنَّا عَلَىٰٓ أَن نُّرِيَكَ مَا نَعِدُهُمۡ لَقَٰدِرُونَ﴿٩٥﴾
95እኛ የምናስፈራራቸውን ነገር ልናሳይህ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
ٱدۡفَعۡ بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ ٱلسَّيِّئَةَۚ نَحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَا يَصِفُونَ﴿٩٦﴾
96በዚያች እርስዋ መልካም በኾነችው (ጠባይ) መጥፎይቱን ነገር ገፍትር፡፡ እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂዎች ነን፡፡
وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنۡ هَمَزَٰتِ ٱلشَّيَٰطِينِ﴿٩٧﴾
97በልም «ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ፡፡
وَأَعُوذُ بِكَ رَبِّ أَن يَحۡضُرُونِ﴿٩٨﴾
98«ባንተም ጌታዬ ሆይ! (በነገሮቼ) ወደእኔ ከመጣዳቸው እጠበቃለሁ፡፡»
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَحَدَهُمُ ٱلۡمَوۡتُ قَالَ رَبِّ ٱرۡجِعُونِ﴿٩٩﴾
99አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡
لَعَلِّيٓ أَعۡمَلُ صَٰلِحٗا فِيمَا تَرَكۡتُۚ كَلَّآۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَآئِلُهَاۖ وَمِن وَرَآئِهِم بَرۡزَخٌ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ﴿١٠٠﴾
100«በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» (ይህን ከማለት) ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አልለ፡፡
فَإِذَا نُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَلَآ أَنسَابَ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَئِذٖ وَلَا يَتَسَآءَلُونَ﴿١٠١﴾
101በቀንዱም በተነፋ ጊዜ በዚያ ቀን በመካከላቸው ዝምድና የለም፡፡ አይጠያየቁምም፡፡
فَمَن ثَقُلَتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ﴿١٠٢﴾
102ሚዛኖቹም የከበዱለት ሰው እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡
وَمَنۡ خَفَّتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فِي جَهَنَّمَ خَٰلِدُونَ﴿١٠٣﴾
103ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰው እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፡፡ በገሀነም ውስጥ ዘመውታሪዎች ናቸው፡፡
تَلۡفَحُ وُجُوهَهُمُ ٱلنَّارُ وَهُمۡ فِيهَا كَٰلِحُونَ﴿١٠٤﴾
104ፊቶቻቸውን እሳት ትገርፉቸዋለች፡፡ እነርሱም በእርሷ ውስጥ ከንፈሮቻቸው የተኮማተሩ ናቸው፡፡
أَلَمۡ تَكُنۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَكُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ﴿١٠٥﴾
105«አንቀጾቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን?» (ይባላሉ)፡፡
قَالُواْ رَبَّنَا غَلَبَتۡ عَلَيۡنَا شِقۡوَتُنَا وَكُنَّا قَوۡمٗا ضَآلِّينَ﴿١٠٦﴾
106ይላሉ «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችን፡፡ ጠማማዎችም ሕዝቦች ነበርን፡፡
رَبَّنَآ أَخۡرِجۡنَا مِنۡهَا فَإِنۡ عُدۡنَا فَإِنَّا ظَٰلِمُونَ﴿١٠٧﴾
107«ጌታችን ሆይ! ከእርሷ አውጣን፡፡ (ወደ ክህደት) ብንመለስ እኛ በደዮች ነን፡፡»
قَالَ ٱخۡسَـُٔواْ فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ﴿١٠٨﴾
108(አላህም) «ወራዶች ኾናችሁ በውስጥዋ እርጉ፡፡ አታናግሩኝም» ይላቸዋል፡፡
إِنَّهُۥ كَانَ فَرِيقٞ مِّنۡ عِبَادِي يَقُولُونَ رَبَّنَآ ءَامَنَّا فَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلرَّٰحِمِينَ﴿١٠٩﴾
109እነሆ ከባሮቼ «ጌታችን ሆይ! አምነናልና ማረን እዘንልንም አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» የሚሉ ክፍሎች ነበሩ፡፡
فَٱتَّخَذۡتُمُوهُمۡ سِخۡرِيًّا حَتَّىٰٓ أَنسَوۡكُمۡ ذِكۡرِي وَكُنتُم مِّنۡهُمۡ تَضۡحَكُونَ﴿١١٠﴾
110እኔንም ማውሳትን እስካስረሷችሁ ድረስም ማላገጫ አድርጋችሁ ያዛችኋቸው፡፡ በእነርሱም የምትስቁ ነበራችሁ፡፡
إِنِّي جَزَيۡتُهُمُ ٱلۡيَوۡمَ بِمَا صَبَرُوٓاْ أَنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ﴿١١١﴾
111እኔ ዛሬ በትዕግስታቸው ምክንያት እነሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙት እነርሱ ብቻ በመኾን መነዳኋቸው፤ (ይላቸዋል)፡፡
قَٰلَ كَمۡ لَبِثۡتُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ عَدَدَ سِنِينَ﴿١١٢﴾
112«በምድር ውስጥ ከዓመታት ቁጥር ስንትን ቆያችሁ؟» ይላቸዋል፡፡
قَالُواْ لَبِثۡنَا يَوۡمًا أَوۡ بَعۡضَ يَوۡمٖ فَسۡـَٔلِ ٱلۡعَآدِّينَ﴿١١٣﴾
113«አንድ ቀንን ወይም ከፊል ቀንን ቆየን፡፡ ቆጣሪዎቹንም ጠይቅ» ይላሉ፡፡
قَٰلَ إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا قَلِيلٗاۖ لَّوۡ أَنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ﴿١١٤﴾
114«እናንተ (የቆያችሁትን መጠን) የምታውቁ ብትኾኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥ በምትቆዩት አንፃር) ጥቂትን ጊዜ እንጂ አልቆያችሁም» ይላቸዋል፡፡
أَفَحَسِبۡتُمۡ أَنَّمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ عَبَثٗا وَأَنَّكُمۡ إِلَيۡنَا لَا تُرۡجَعُونَ﴿١١٥﴾
115«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን አሰባችሁን؟» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን?) [1]
فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلۡمَلِكُ ٱلۡحَقُّۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡكَرِيمِ﴿١١٦﴾
116የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡
وَمَن يَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ لَا بُرۡهَٰنَ لَهُۥ بِهِۦ فَإِنَّمَا حِسَابُهُۥ عِندَ رَبِّهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلۡكَٰفِرُونَ﴿١١٧﴾
117ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለው (መሆኑ እየታወቀ) የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡
وَقُل رَّبِّ ٱغۡفِرۡ وَٱرۡحَمۡ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلرَّٰحِمِينَ﴿١١٨﴾
118በልም «ጌታዬ ሆይ ማር፤ እዘንም፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»