Al-Haqqah

الحاقة

The Inevitable52 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ٱلۡحَآقَّةُ﴿١

1እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሣኤ)፡፡

مَا ٱلۡحَآقَّةُ﴿٢

2አረጋጋጪቱም (እርሷ) ምንድን ናት!

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡحَآقَّةُ﴿٣

3አረጋጋጪቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?

كَذَّبَتۡ ثَمُودُ وَعَادُۢ بِٱلۡقَارِعَةِ﴿٤

4ሰሙድና ዓድ በቆርቋሪይቱ (ትንሣኤ) አስተባበሉ፡፡

فَأَمَّا ثَمُودُ فَأُهۡلِكُواْ بِٱلطَّاغِيَةِ﴿٥

5ሠሙድማ ወሰን በሌላት ጩኸት ተጠፋ፤ (ተወደሙ)፡፡

وَأَمَّا عَادٞ فَأُهۡلِكُواْ بِرِيحٖ صَرۡصَرٍ عَاتِيَةٖ﴿٦

6ዓድማ በኀይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ፡፡

سَخَّرَهَا عَلَيۡهِمۡ سَبۡعَ لَيَالٖ وَثَمَٰنِيَةَ أَيَّامٍ حُسُومٗاۖ فَتَرَى ٱلۡقَوۡمَ فِيهَا صَرۡعَىٰ كَأَنَّهُمۡ أَعۡجَازُ نَخۡلٍ خَاوِيَةٖ﴿٧

7ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ ሕዝቦቹንም፤ በውስጧ የተጣሉ ኾነው ልክ ክፍት የኾኑ የዘንባባ ግንዶች መስለው ታያቸዋለህ፡፡

فَهَلۡ تَرَىٰ لَهُم مِّنۢ بَاقِيَةٖ﴿٨

8ለእነርሱም ቀሪን ታያለህን?

وَجَآءَ فِرۡعَوۡنُ وَمَن قَبۡلَهُۥ وَٱلۡمُؤۡتَفِكَٰتُ بِٱلۡخَاطِئَةِ﴿٩

9ፈርዖን ከበፊቱ የነበሩትም ሰዎች ተገልባጮቹም (ከተሞች) በኀጢአት (ሥራዎች) መጡ፡፡

فَعَصَوۡاْ رَسُولَ رَبِّهِمۡ فَأَخَذَهُمۡ أَخۡذَةٗ رَّابِيَةً﴿١٠

10የጌታቸውንም መልእክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፡፡ የበረታችንም አያያዝ ያዛቸው፡፡

إِنَّا لَمَّا طَغَا ٱلۡمَآءُ حَمَلۡنَٰكُمۡ فِي ٱلۡجَارِيَةِ﴿١١

11እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሻላይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ፡፡

لِنَجۡعَلَهَا لَكُمۡ تَذۡكِرَةٗ وَتَعِيَهَآ أُذُنٞ وَٰعِيَةٞ﴿١٢

12ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋት አጥኒ የኾነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ፡፡

فَإِذَا نُفِخَ فِي ٱلصُّورِ نَفۡخَةٞ وَٰحِدَةٞ﴿١٣

13በቀንዱም አንዲት መንነፋት በተነፋች ጊዜ፡፡

وَحُمِلَتِ ٱلۡأَرۡضُ وَٱلۡجِبَالُ فَدُكَّتَا دَكَّةٗ وَٰحِدَةٗ﴿١٤

14ምድርና ጋራዎችም (ከስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፡፡

فَيَوۡمَئِذٖ وَقَعَتِ ٱلۡوَاقِعَةُ﴿١٥

15በዚያ ቀን ኋኝቱ (ትንሣኤ) ትኾናለች፡፡

وَٱنشَقَّتِ ٱلسَّمَآءُ فَهِيَ يَوۡمَئِذٖ وَاهِيَةٞ﴿١٦

16ሰማይም ትቀደዳለች፡፡ ስለዚህ እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፡፡

وَٱلۡمَلَكُ عَلَىٰٓ أَرۡجَآئِهَاۚ وَيَحۡمِلُ عَرۡشَ رَبِّكَ فَوۡقَهُمۡ يَوۡمَئِذٖ ثَمَٰنِيَةٞ﴿١٧

17መላእክትም በየጫፎችዋ ላይ ይኾናሉ፡፡ የጌታህንም ዐርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላእክት ከበላያቸው ይሸከማሉ፡፡

يَوۡمَئِذٖ تُعۡرَضُونَ لَا تَخۡفَىٰ مِنكُمۡ خَافِيَةٞ﴿١٨

18በዚያ ቀን ከእናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲኾኑ ትቅቀረባላችሁ፡፡

فَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ فَيَقُولُ هَآؤُمُ ٱقۡرَءُواْ كِتَٰبِيَهۡ﴿١٩

19መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል፡፡

إِنِّي ظَنَنتُ أَنِّي مُلَٰقٍ حِسَابِيَهۡ﴿٢٠

20«እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡

فَهُوَ فِي عِيشَةٖ رَّاضِيَةٖ﴿٢١

21እርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡

فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٖ﴿٢٢

22በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡

قُطُوفُهَا دَانِيَةٞ﴿٢٣

23ፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡

كُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ هَنِيٓـَٔۢا بِمَآ أَسۡلَفۡتُمۡ فِي ٱلۡأَيَّامِ ٱلۡخَالِيَةِ﴿٢٤

24በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ)፡፡

وَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِشِمَالِهِۦ فَيَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي لَمۡ أُوتَ كِتَٰبِيَهۡ﴿٢٥

25መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡

وَلَمۡ أَدۡرِ مَا حِسَابِيَهۡ﴿٢٦

26«ምርመራየንም ምን እንደኾነ ባላወቅኩ፡፡

يَٰلَيۡتَهَا كَانَتِ ٱلۡقَاضِيَةَ﴿٢٧

27«እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በኾነች፡፡

مَآ أَغۡنَىٰ عَنِّي مَالِيَهۡۜ﴿٢٨

28«ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡

هَلَكَ عَنِّي سُلۡطَٰنِيَهۡ﴿٢٩

29«ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ» (ይላል)፡፡

خُذُوهُ فَغُلُّوهُ﴿٣٠

30«ያዙት፤ እሰሩትም፡፡

ثُمَّ ٱلۡجَحِيمَ صَلُّوهُ﴿٣١

31«ከዚያም በእሳት ውሰጥ አግቡት፡፡

ثُمَّ فِي سِلۡسِلَةٖ ذَرۡعُهَا سَبۡعُونَ ذِرَاعٗا فَٱسۡلُكُوهُ﴿٣٢

32«ከዚያም ርዝመቷ ሰባ ክንድ በኾነች ሰንሰለት ውስጥ አግቡት፡፡»

إِنَّهُۥ كَانَ لَا يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ ٱلۡعَظِيمِ﴿٣٣

33እርሱ ታላቅ በኾነው አላህ አያምንም ነበርና፡፡

وَلَا يَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِينِ﴿٣٤

34ድኾችንም በማብላት ላይ አያግባባም ነበርና፡፡

فَلَيۡسَ لَهُ ٱلۡيَوۡمَ هَٰهُنَا حَمِيمٞ﴿٣٥

35ለእርሱም ዛሬ እዚህ ዘመድ የለውም፡፡

وَلَا طَعَامٌ إِلَّا مِنۡ غِسۡلِينٖ﴿٣٦

36ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ (እዥ) በስተቀር የለውም፡፡

لَّا يَأۡكُلُهُۥٓ إِلَّا ٱلۡخَٰطِـُٔونَ﴿٣٧

37ኀጢኣተኞች እንጅ ሌላ አይበላውም፤ (ይባላል)፡፡

فَلَآ أُقۡسِمُ بِمَا تُبۡصِرُونَ﴿٣٨

38በምታዩትም ነገር እምላለሁ፡፡

وَمَا لَا تُبۡصِرُونَ﴿٣٩

39በማታዩትም ነገር፡፡

إِنَّهُۥ لَقَوۡلُ رَسُولٖ كَرِيمٖ﴿٤٠

40እርሱ (ቁርኣን) የተከበረ መልክተኛ ቃል ነው፡፡

وَمَا هُوَ بِقَوۡلِ شَاعِرٖۚ قَلِيلٗا مَّا تُؤۡمِنُونَ﴿٤١

41እርሱም የባለቅኔ ቃል (ግጥም) አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ፡፡

وَلَا بِقَوۡلِ كَاهِنٖۚ قَلِيلٗا مَّا تَذَكَّرُونَ﴿٤٢

42የጠንቋይም ቃል አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ፡፡

تَنزِيلٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ﴿٤٣

43ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡

وَلَوۡ تَقَوَّلَ عَلَيۡنَا بَعۡضَ ٱلۡأَقَاوِيلِ﴿٤٤

44በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤

لَأَخَذۡنَا مِنۡهُ بِٱلۡيَمِينِ﴿٤٥

45በቀኝ በያዝነው ነበር፡፡

ثُمَّ لَقَطَعۡنَا مِنۡهُ ٱلۡوَتِينَ﴿٤٦

46ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር (የተንጠለጠለበትን ጅማት) በቆረጥን ነበር፡፡

فَمَا مِنكُم مِّنۡ أَحَدٍ عَنۡهُ حَٰجِزِينَ﴿٤٧

47ከእናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም፡፡

وَإِنَّهُۥ لَتَذۡكِرَةٞ لِّلۡمُتَّقِينَ﴿٤٨

48እርሱም (ቁርኣን) ለጥንቁቆቹ መገሠጫ ነው፡፡

وَإِنَّا لَنَعۡلَمُ أَنَّ مِنكُم مُّكَذِّبِينَ﴿٤٩

49እኛም ከእናንተ ውስጥ አስተባባዮች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡

وَإِنَّهُۥ لَحَسۡرَةٌ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ﴿٥٠

50እርሱም (ቁርኣን) በከሓዲዎቹ ላይ ጸጸት ነው፡፡

وَإِنَّهُۥ لَحَقُّ ٱلۡيَقِينِ﴿٥١

51እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡

فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ﴿٥٢

52የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡

RELATED SURAHS