Al-Humazah

الهمزة

The Gossipmonger9 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَيۡلٞ لِّكُلِّ هُمَزَةٖ لُّمَزَةٍ﴿١

1ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡

ٱلَّذِي جَمَعَ مَالٗا وَعَدَّدَهُۥ﴿٢

2ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበውም) ለኾነ ፤(ወዮለት)፡፡

يَحۡسَبُ أَنَّ مَالَهُۥٓ أَخۡلَدَهُۥ﴿٣

3ገንዘቡ የሚያዘወትረው መኾኑን ያስባል፡፡

كَلَّاۖ لَيُنۢبَذَنَّ فِي ٱلۡحُطَمَةِ﴿٤

4ይከልከል፤ በሰባሪይቱ (እሳት) ውስጥ በእርግጥ ይጣላል፡፡

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡحُطَمَةُ﴿٥

5ሰባሪይቱም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?

نَارُ ٱللَّهِ ٱلۡمُوقَدَةُ﴿٦

6የተነደደችው የአላህ እሳት ናት፡፡

ٱلَّتِي تَطَّلِعُ عَلَى ٱلۡأَفۡـِٔدَةِ﴿٧

7ያቺ በልቦች ላይ የምትዘልቅ የኾነችው፡፡

إِنَّهَا عَلَيۡهِم مُّؤۡصَدَةٞ﴿٨

8እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋጀች ናት፡፡

فِي عَمَدٖ مُّمَدَّدَةِۭ﴿٩

9በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ (የተዘጋች ናት)፡፡

RELATED SURAHS