Al-Anfal

الأنفال

The Spoils of War75 ayahsMedinan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلۡأَنفَالِۖ قُلِ ٱلۡأَنفَالُ لِلَّهِ وَٱلرَّسُولِۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَصۡلِحُواْ ذَاتَ بَيۡنِكُمۡۖ وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ﴿١

1ከጦር ዘረፋ ገንዘቦች ይጠይቁሃል፡፡ «የዘረፋ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው፡፡» ስለዚህ አላህን ፍሩ፡፡ በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ፡፡ አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ በላቸው፡፡

إِنَّمَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَجِلَتۡ قُلُوبُهُمۡ وَإِذَا تُلِيَتۡ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُهُۥ زَادَتۡهُمۡ إِيمَٰنٗا وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ﴿٢

2ፍጹም ምእምናን እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በነሱም ላይ አንቀጾቹ በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡

ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ﴿٣

3እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው፡፡

أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ حَقّٗاۚ لَّهُمۡ دَرَجَٰتٌ عِندَ رَبِّهِمۡ وَمَغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ﴿٤

4እነዚያ በእውነት አማኞች እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለእነሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምህረትና የከበረ ሲሳይም አላቸው፡፡

كَمَآ أَخۡرَجَكَ رَبُّكَ مِنۢ بَيۡتِكَ بِٱلۡحَقِّ وَإِنَّ فَرِيقٗا مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ لَكَٰرِهُونَ﴿٥

5(ይህ በዘረፋ ክፍያ የከፊሉ ሰው መጥላት) ከምእምናን ከፊሉ የጠሉ ሲኾኑ ጌታህ ከቤትህ በእውነት ላይ ኾነህ እንዳወጣህ ነው፡፡

يُجَٰدِلُونَكَ فِي ٱلۡحَقِّ بَعۡدَ مَا تَبَيَّنَ كَأَنَّمَا يُسَاقُونَ إِلَى ٱلۡمَوۡتِ وَهُمۡ يَنظُرُونَ﴿٦

6እነርሱ እያዩ ወደሞት እንደሚነዱ ኾነው በእውነቱ ነገር (በመጋደል ግዴታነት) ከተገለጸላቸው በኋላ ይከራከሩሃል፡፡

وَإِذۡ يَعِدُكُمُ ٱللَّهُ إِحۡدَى ٱلطَّآئِفَتَيۡنِ أَنَّهَا لَكُمۡ وَتَوَدُّونَ أَنَّ غَيۡرَ ذَاتِ ٱلشَّوۡكَةِ تَكُونُ لَكُمۡ وَيُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُحِقَّ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦ وَيَقۡطَعَ دَابِرَ ٱلۡكَٰفِرِينَ﴿٧

7አላህም ከሁለቱ ጭፍሮች አንደኛዋን እርሷ ለናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁ ጊዜ፣ የሀይል ባለቤት ያልኾነችውም (ነጋዴይቱ) ለናንተ ልትኾን በወደዳችሁ ጊዜ፣ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነትን ማረጋገጡን ሊገልጽና የከሓዲዎችንም መጨረሻ ሊቆርጥ በሻ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡

لِيُحِقَّ ٱلۡحَقَّ وَيُبۡطِلَ ٱلۡبَٰطِلَ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُجۡرِمُونَ﴿٨

8(ይህንንም ያደረገው) አጋሪዎቹ ቢጠሉም እውነቱን ሊያረጋግጥ ክህደትንም ሊያጠፋ ነው፡፡

إِذۡ تَسۡتَغِيثُونَ رَبَّكُمۡ فَٱسۡتَجَابَ لَكُمۡ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلۡفٖ مِّنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ مُرۡدِفِينَ﴿٩

9ከጌታችሁ ርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲኾኑ እረዳችኋለሁ» ሲል ለናንተ የተቀበላችሁን (አስታውሱ)፡፡

وَمَا جَعَلَهُ ٱللَّهُ إِلَّا بُشۡرَىٰ وَلِتَطۡمَئِنَّ بِهِۦ قُلُوبُكُمۡۚ وَمَا ٱلنَّصۡرُ إِلَّا مِنۡ عِندِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ﴿١٠

10አላህም (ይኽንን ርዳታ) ለብስራትና ልቦቻችሁ በርሱ ሊረኩበት እንጂ ለሌላ አላደረገውም፡፡ ድልም መንሳት ከአላህ ዘንድ እንጂ ከሌላ አይደለም፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡

إِذۡ يُغَشِّيكُمُ ٱلنُّعَاسَ أَمَنَةٗ مِّنۡهُ وَيُنَزِّلُ عَلَيۡكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ لِّيُطَهِّرَكُم بِهِۦ وَيُذۡهِبَ عَنكُمۡ رِجۡزَ ٱلشَّيۡطَٰنِ وَلِيَرۡبِطَ عَلَىٰ قُلُوبِكُمۡ وَيُثَبِّتَ بِهِ ٱلۡأَقۡدَامَ﴿١١

11ከእርሱ በኾነው ጸጥታ (በጦር ግንባር) በእንቅልፍ በሸፈናችሁና ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ፣ የሰይጣንንም ጉትጎታ ከእናንተ ሊያስወግድላችሁ፣ ልቦቻችሁንም (በትዕግስት) ሊያጠነክርላችሁ፣ በእርሱም ጫማዎችን (በአሸዋው ላይ) ሊያደላድልላችሁ በእናንተ ላይ ከሰማይ ባወረደላችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡

إِذۡ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ أَنِّي مَعَكُمۡ فَثَبِّتُواْ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۚ سَأُلۡقِي فِي قُلُوبِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلرُّعۡبَ فَٱضۡرِبُواْ فَوۡقَ ٱلۡأَعۡنَاقِ وَٱضۡرِبُواْ مِنۡهُمۡ كُلَّ بَنَانٖ﴿١٢

12ጌታህ ወደ መላእክቱ «እኔ (በእርዳታዬ) ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ፡፡ በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፡፡ ከአንገቶችም በላይ (ራሶችን) ምቱ፡፡ ከእነሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ፡፡» ሲል ያወረደውን (አስታውስ)፡፡

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ شَآقُّواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۚ وَمَن يُشَاقِقِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ﴿١٣

13ይህ እነርሱ አላህንና መልክተኛውን ስለተቃወሙ ነው፡፡ አላህንና መልክተኛውንም የሚቃወም ሁሉ አላህ ቅጣቱ ብርቱ ነው፡፡

ذَٰلِكُمۡ فَذُوقُوهُ وَأَنَّ لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابَ ٱلنَّارِ﴿١٤

14ይህ (ቅጣታችሁ ነው) ቅመሱትም፡፡ ለከሓዲዎችም የእሳት ቅጣት በእርግጥ አለባቸው፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا لَقِيتُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ زَحۡفٗا فَلَا تُوَلُّوهُمُ ٱلۡأَدۡبَارَ﴿١٥

15እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን የካዱትን ሰዎች (ለጦር) ሲጓዙ ባገኛችኋቸው ጊዜ ጀርባዎችን አታዙሩላቸው፡፡

وَمَن يُوَلِّهِمۡ يَوۡمَئِذٖ دُبُرَهُۥٓ إِلَّا مُتَحَرِّفٗا لِّقِتَالٍ أَوۡ مُتَحَيِّزًا إِلَىٰ فِئَةٖ فَقَدۡ بَآءَ بِغَضَبٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَمَأۡوَىٰهُ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ﴿١٦

16ያን ጊዜም ለግድያ ለመዘዋወር ወይም ወደ ሠራዊት ለመቀላቀል ሳይኾን ጀርባውን የሚያዞርላቸው ሰው ከአላህ በኾነ ቁጣ በእርግጥ ተመለሰ፡፡ መኖሪያውም ገሀነም ናት፡፡ መመለሻይቱም ከፋች፡፡

فَلَمۡ تَقۡتُلُوهُمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ قَتَلَهُمۡۚ وَمَا رَمَيۡتَ إِذۡ رَمَيۡتَ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ رَمَىٰ وَلِيُبۡلِيَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ مِنۡهُ بَلَآءً حَسَنًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ﴿١٧

17አልገደላችኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፡፡ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፡፡ ግን አላህ ወረወረ (ወደ ዓይኖቻቸው አደረሰው)፡፡ ለአማኞችም ከርሱ የኾነን መልካም ጸጋ ለመስጠት (ይህን አደረገ)፡፡ አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና፡፡

ذَٰلِكُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ مُوهِنُ كَيۡدِ ٱلۡكَٰفِرِينَ﴿١٨

18ይህ (ዕውነት ነው)፡፡ አላህም የከሓዲዎችን ተንኮል አድካሚ ነው፡፡

إِن تَسۡتَفۡتِحُواْ فَقَدۡ جَآءَكُمُ ٱلۡفَتۡحُۖ وَإِن تَنتَهُواْ فَهُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡۖ وَإِن تَعُودُواْ نَعُدۡ وَلَن تُغۡنِيَ عَنكُمۡ فِئَتُكُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَوۡ كَثُرَتۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ﴿١٩

19ፍትሕን (ፍርድን) ብትጠይቁ ፍትሑ በእርግጥ መጥቶላችኋል፡፡ (ክህደትንና መዋጋትን) ብትከለከሉም እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ (ወደ መጋደል) ብትመለሱም እንመለሳለን፡፡ ሰራዊታችሁም ብትበዛም እንኳ ከናንተ ምንም አትጠቅማችሁም፡፡ አላህም ከምእምናን ጋር ነው፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَوَلَّوۡاْ عَنۡهُ وَأَنتُمۡ تَسۡمَعُونَ﴿٢٠

20እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ፡፡ እናንተም የምትሰሙ ስትኾኑ ከርሱ አትሽሹ፡፡

وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ قَالُواْ سَمِعۡنَا وَهُمۡ لَا يَسۡمَعُونَ﴿٢١

21እንደነዚያም እነሱ የማይሰሙ ሲኾኑ ሰማን እንዳሉት አትሁኑ፡፡

۞ إِنَّ شَرَّ ٱلدَّوَآبِّ عِندَ ٱللَّهِ ٱلصُّمُّ ٱلۡبُكۡمُ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡقِلُونَ﴿٢٢

22ከተንቀሳቃሾች ሁሉ አላህ ዘንድ መጥፎ ተንኮለኞች እነዚያ የማያውቁት፣ ደንቆሮዎቹ፣ ዲዳዎቹ ናቸው፡፡

وَلَوۡ عَلِمَ ٱللَّهُ فِيهِمۡ خَيۡرٗا لَّأَسۡمَعَهُمۡۖ وَلَوۡ أَسۡمَعَهُمۡ لَتَوَلَّواْ وَّهُم مُّعۡرِضُونَ﴿٢٣

23በውስጣቸውም ደግ መኖሩን አላህ ባወቀ ኖሮ (የመረዳትን መስማት) ባሰማቸው ነበር፡፡ (ደግ የሌለባቸው መኾኑን ሲያውቅ) ባሰማቸውም ኖሮ እነሱ እውነትን የተው ኾነው በሸሹ ነበር፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱسۡتَجِيبُواْ لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمۡ لِمَا يُحۡيِيكُمۡۖ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَحُولُ بَيۡنَ ٱلۡمَرۡءِ وَقَلۡبِهِۦ وَأَنَّهُۥٓ إِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ﴿٢٤

24እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልክተኛው) ሕያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልክተኛው ታዘዙ፡፡ አላህም በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መኾኑን ወደርሱም የምትሰበሰቡ መኾናችሁን እወቁ፡፡

وَٱتَّقُواْ فِتۡنَةٗ لَّا تُصِيبَنَّ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنكُمۡ خَآصَّةٗۖ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ﴿٢٥

25ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ፡፡

وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ أَنتُمۡ قَلِيلٞ مُّسۡتَضۡعَفُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ تَخَافُونَ أَن يَتَخَطَّفَكُمُ ٱلنَّاسُ فَـَٔاوَىٰكُمۡ وَأَيَّدَكُم بِنَصۡرِهِۦ وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ﴿٢٦

26እናንተም በምድር ላይ የተናቃችሁ ጥቂቶች ኾናችሁ ሳላችሁ ሰዎች ሊነጥቁዋችሁ የምትፈሩ ስትኾኑ ያስጠጋችሁን በእርዳታውም ያበረታችሁን ከመልካሞች ሲሳዮችም ታመሰግኑ ዘንድ የሰጣችሁን አስታውሱ፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَخُونُواْ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ وَتَخُونُوٓاْ أَمَٰنَٰتِكُمۡ وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ﴿٢٧

27እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን አትክዱ፡፡ አደራዎቻችሁንም እናንተ እያወቃችሁ አትክዱ፡፡

وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَآ أَمۡوَٰلُكُمۡ وَأَوۡلَٰدُكُمۡ فِتۡنَةٞ وَأَنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥٓ أَجۡرٌ عَظِيمٞ﴿٢٨

28ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ፈተና ብቻ መኾናቸውንና አላህም እሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለው መኾኑን እወቁ፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن تَتَّقُواْ ٱللَّهَ يَجۡعَل لَّكُمۡ فُرۡقَانٗا وَيُكَفِّرۡ عَنكُمۡ سَيِّـَٔاتِكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡۗ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ﴿٢٩

29እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያን ብርሃን ያደርግላችኋል፡፡ ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከእናንተ ላይ ያብስላችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡

وَإِذۡ يَمۡكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيُثۡبِتُوكَ أَوۡ يَقۡتُلُوكَ أَوۡ يُخۡرِجُوكَۚ وَيَمۡكُرُونَ وَيَمۡكُرُ ٱللَّهُۖ وَٱللَّهُ خَيۡرُ ٱلۡمَٰكِرِينَ﴿٣٠

30እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም (ከመካ) ሊያወጡህ ባንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ይመክራሉም አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል፡፡ አላህም ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው፡፡

وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا قَالُواْ قَدۡ سَمِعۡنَا لَوۡ نَشَآءُ لَقُلۡنَا مِثۡلَ هَٰذَآ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿٣١

31አንቀጾቻችንም በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «በእርግጥ ሰምተናል፤ በሻን ኖሮ የዚህን ብጤ ባልን ነበር፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ጽሑፍ ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» ይላሉ፡፡

وَإِذۡ قَالُواْ ٱللَّهُمَّ إِن كَانَ هَٰذَا هُوَ ٱلۡحَقَّ مِنۡ عِندِكَ فَأَمۡطِرۡ عَلَيۡنَا حِجَارَةٗ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ أَوِ ٱئۡتِنَا بِعَذَابٍ أَلِيمٖ﴿٣٢

32«ጌታችን ሆይ! ይህ እርሱ ካንተ ዘንድ (የተወረደ) እውነት እንደ ኾነ በኛ ላይ ከሰማይ ድንጋዮችን አዝንብብን ወይም አሳማሚ ቅጣትን አምጣብን» ባሉም ጊዜ (አስታውስ)

وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُعَذِّبَهُمۡ وَأَنتَ فِيهِمۡۚ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ مُعَذِّبَهُمۡ وَهُمۡ يَسۡتَغۡفِرُونَ﴿٣٣

33አላህም አንተ በውስጣቸው እያለህ (ድንጋይ በማዝነብና ባሳማሚ ቅጣት) የሚቀጣቸው አይደለም፡፡ አላህም እነሱ ምህረትን የሚለምኑ ሲኾኑ የሚቀጣቸው አይደለም፡፡

وَمَا لَهُمۡ أَلَّا يُعَذِّبَهُمُ ٱللَّهُ وَهُمۡ يَصُدُّونَ عَنِ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ وَمَا كَانُوٓاْ أَوۡلِيَآءَهُۥٓۚ إِنۡ أَوۡلِيَآؤُهُۥٓ إِلَّا ٱلۡمُتَّقُونَ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ﴿٣٤

34እነሱ ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሲኾኑም አላህ (በሰይፍ) የማይቀጣቸው ለነሱ ምን አልላቸው (የቤቱ) ጠባቂዎችም አልነበሩም፡፡ ጠባቂዎቹ (ክሕደትን) ተጠንቃቂዎቹ እንጂ ሌሎቹ አይደሉም፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡

وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ﴿٣٥

35በቤቱ ዘንድም (በካዕባ) ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ (ይባላሉ)፡፡

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُنفِقُونَ أَمۡوَٰلَهُمۡ لِيَصُدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ فَسَيُنفِقُونَهَا ثُمَّ تَكُونُ عَلَيۡهِمۡ حَسۡرَةٗ ثُمَّ يُغۡلَبُونَۗ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِلَىٰ جَهَنَّمَ يُحۡشَرُونَ﴿٣٦

36እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘቦቻቸውን ያወጣሉ፡፡ በእርግጥም ያወጡዋታል፡፡ ከዚያም በእነሱ ላይ ጸጸት ትኾንባቸዋለች፡፡ ከዚያም ይሸነፋሉ፡፡ እነዚያም የካዱት ወደ ገሀነም ይሰበሰባሉ፡፡

لِيَمِيزَ ٱللَّهُ ٱلۡخَبِيثَ مِنَ ٱلطَّيِّبِ وَيَجۡعَلَ ٱلۡخَبِيثَ بَعۡضَهُۥ عَلَىٰ بَعۡضٖ فَيَرۡكُمَهُۥ جَمِيعٗا فَيَجۡعَلَهُۥ فِي جَهَنَّمَۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ﴿٣٧

37አላህ መጥፎውን ከመልካሙ ሊለይ መጥፎውንም ከፊሉን በከፊሉ ላይ ሊያደርግና ባንድ ላይ ሊያነባብረው በገሀነም ውስጥም ሊያደርገው (ይሰበሰባሉ)፡፡ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎቹ ናቸው፡፡

قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِن يَنتَهُواْ يُغۡفَرۡ لَهُم مَّا قَدۡ سَلَفَ وَإِن يَعُودُواْ فَقَدۡ مَضَتۡ سُنَّتُ ٱلۡأَوَّلِينَ﴿٣٨

38ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ሥራ) ምሕረት ይደረግላቸዋል፡፡ (ወደ መጋደል) ቢመለሱም (እናጠፋቸዋለን)፡፡ የቀድሞዎቹ ሕዝቦች ልማድ በእርግጥ አልፋለችና፡፡

وَقَٰتِلُوهُمۡ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتۡنَةٞ وَيَكُونَ ٱلدِّينُ كُلُّهُۥ لِلَّهِۚ فَإِنِ ٱنتَهَوۡاْ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِمَا يَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ﴿٣٩

39ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው፡፡ ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

وَإِن تَوَلَّوۡاْ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ مَوۡلَىٰكُمۡۚ نِعۡمَ ٱلۡمَوۡلَىٰ وَنِعۡمَ ٱلنَّصِيرُ﴿٤٠

40(ከእምነት) ቢዞሩም አላህ ረዳታችሁ መኾኑን ዕወቁ፡፡ (እርሱ) ምን ያምር ጠባቂ! ምን ያምርም ረዳት!

۞ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَا غَنِمۡتُم مِّن شَيۡءٖ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُۥ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ إِن كُنتُمۡ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَىٰ عَبۡدِنَا يَوۡمَ ٱلۡفُرۡقَانِ يَوۡمَ ٱلۡتَقَى ٱلۡجَمۡعَانِۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ﴿٤١

41ከማንኛውም ነገር በጦር (ከከሓዲዎች) የማረካችሁትን አንድ አምስተኛው ለአላህና ለመልክተኛው፣ (ለነቢዩ) የዝምድና ባለቤቶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም የተገባ መኾኑን ዕውቁ፣ በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙበት (በበድር) ቀን በባሪያችን ላይ ባወረድነው የምታምኑ እንደኾናችሁ (ይህንን ዕወቁ)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

إِذۡ أَنتُم بِٱلۡعُدۡوَةِ ٱلدُّنۡيَا وَهُم بِٱلۡعُدۡوَةِ ٱلۡقُصۡوَىٰ وَٱلرَّكۡبُ أَسۡفَلَ مِنكُمۡۚ وَلَوۡ تَوَاعَدتُّمۡ لَٱخۡتَلَفۡتُمۡ فِي ٱلۡمِيعَٰدِ وَلَٰكِن لِّيَقۡضِيَ ٱللَّهُ أَمۡرٗا كَانَ مَفۡعُولٗا لِّيَهۡلِكَ مَنۡ هَلَكَ عَنۢ بَيِّنَةٖ وَيَحۡيَىٰ مَنۡ حَيَّ عَنۢ بَيِّنَةٖۗ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَسَمِيعٌ عَلِيمٌ﴿٤٢

42እናንተ በቅርቢቱ ዳርቻ ኾናችሁ እነርሱም በሩቂቱ ዳርቻ ኾነው የነጋዴዎቹም ጭፍራ ከናንተ በታች ሲኾኑ በሰፈራችሁ ጊዜ (ያደረግንላችሁን አስታውሱ)፡፡ በተቃጠራችሁም ኖሮ በቀጠሮው በተለያያችሁ ነበር፡፡ ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽም የሚጠፋ ሰው ከአስረጅ በኋላ እንዲጠፋ ሕያው የሚኾንም ሰው ከአስረጅ በኋላ ሕያው እንዲኾን (ያለቀጠሮ አጋጠማችሁ)፡፡ አላህም በእርግጥ ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

إِذۡ يُرِيكَهُمُ ٱللَّهُ فِي مَنَامِكَ قَلِيلٗاۖ وَلَوۡ أَرَىٰكَهُمۡ كَثِيرٗا لَّفَشِلۡتُمۡ وَلَتَنَٰزَعۡتُمۡ فِي ٱلۡأَمۡرِ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ سَلَّمَۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ﴿٤٣

43አላህ በሕልምህ እነሱን ጥቂት አድርጎ ባሳየህ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ እነሱን ብዙ አድርጎ ባሳየህም ኖሮ በፈራችሁና በነገሩ በተጨቃጨቃችሁ ነበር፡፡ ግን አላህ አዳናችሁ፡፡ እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡

وَإِذۡ يُرِيكُمُوهُمۡ إِذِ ٱلۡتَقَيۡتُمۡ فِيٓ أَعۡيُنِكُمۡ قَلِيلٗا وَيُقَلِّلُكُمۡ فِيٓ أَعۡيُنِهِمۡ لِيَقۡضِيَ ٱللَّهُ أَمۡرٗا كَانَ مَفۡعُولٗاۗ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ﴿٤٤

44አላህም ሊሠራው የሚገባን ነገር ይፈጽም ዘንድ በተጋጠማችሁ ጊዜ እነርሱን በዓይኖቻችሁ ጥቂት አድርጎ ያሳያችሁንና በዓይኖቻቸውም ላይ ያሳነሳችሁን (አስታውሱ)፡፡ ነገሮቹም ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا لَقِيتُمۡ فِئَةٗ فَٱثۡبُتُواْ وَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا لَّعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ﴿٤٥

45እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሰራዊትን በገጠማችሁ ጊዜ እርጉ፤ (መክቱ)፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፤ በእርግጥ ትድናላችሁና፡፡

وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَنَٰزَعُواْ فَتَفۡشَلُواْ وَتَذۡهَبَ رِيحُكُمۡۖ وَٱصۡبِرُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ﴿٤٦

46አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ አትጨቃጨቁም፡፡ ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትኼዳለችና፡፡ ታገሱም፤ አላህ ከትዕግስተኞች ጋር ነውና፡፡

وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ خَرَجُواْ مِن دِيَٰرِهِم بَطَرٗا وَرِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ بِمَا يَعۡمَلُونَ مُحِيطٞ﴿٤٧

47እንደነዚያ ለትዕቢትና ለሰዎች ይዩልኝ ሲሉ ከአላህም መንገድ ለማገድ ከአገራቸው እንደወጡት አትኹኑ፡፡ አላህም በሚሠሩት ሁሉ (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡

وَإِذۡ زَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ وَقَالَ لَا غَالِبَ لَكُمُ ٱلۡيَوۡمَ مِنَ ٱلنَّاسِ وَإِنِّي جَارٞ لَّكُمۡۖ فَلَمَّا تَرَآءَتِ ٱلۡفِئَتَانِ نَكَصَ عَلَىٰ عَقِبَيۡهِ وَقَالَ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّنكُمۡ إِنِّيٓ أَرَىٰ مَا لَا تَرَوۡنَ إِنِّيٓ أَخَافُ ٱللَّهَۚ وَٱللَّهُ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ﴿٤٨

48ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና «ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ» ባለ ጊዜም (አስታውስ)፡፡ ሁለቱ ጭፍሮችም በተያዩ ጊዜ፤ ወደኋላው አፈገፈገ፡፡ «እኔ ከናንተ ንጹህ ነኝ፡፡ እኔ እናንተ የማታዩትን አያለሁ፡፡ እኔ አላህን እፈራለሁ፡፡ አላህም ቅጣተ ብርቱ ነው» አላቸውም፡፡

إِذۡ يَقُولُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ غَرَّ هَٰٓؤُلَآءِ دِينُهُمۡۗ وَمَن يَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ﴿٤٩

49መናፍቃንና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው «እነዚህን (ሙስሊሞች) ሃይማኖታቸው አታለላቸው» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ (ያሸንፋል)፤ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡

وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ يَتَوَفَّى ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَضۡرِبُونَ وُجُوهَهُمۡ وَأَدۡبَٰرَهُمۡ وَذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡحَرِيقِ﴿٥٠

50እነዚያንም የካዱትን መላእክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» (እያሉ) በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)፡፡

ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيكُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيۡسَ بِظَلَّٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ﴿٥١

51ይህ እጆቻችሁ ባስቀደሙት ምክንያት አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመኾኑ ነው (ይባላሉ)፡፡

كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ قَوِيّٞ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ﴿٥٢

52(የነዚያ ልማድ) እንደ ፈርዖን ቤተሰብና እንደነዚያም ከእነሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ ነው፡፡ በአላህ አንቀጾች ካዱ፤ አላህም በኃጢኣቶቻቸው ያዛቸው፤ አላህ ኀይለኛ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ لَمۡ يَكُ مُغَيِّرٗا نِّعۡمَةً أَنۡعَمَهَا عَلَىٰ قَوۡمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُواْ مَا بِأَنفُسِهِمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ﴿٥٣

53ይህ (ቅጣት) አላህ በሕዝቦች ላይ የለገሰውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ነገር እስከሚለውጡ ድረስ የማይለውጥ በመኾኑ ምክንያት ነው፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ فَأَهۡلَكۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡ وَأَغۡرَقۡنَآ ءَالَ فِرۡعَوۡنَۚ وَكُلّٞ كَانُواْ ظَٰلِمِينَ﴿٥٤

54እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደእነዚያም ከእነሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ (እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥባቸውም)፡፡ በጌታቸው ተአምራት አስተባበሉና በኃጢኣቶቻቸው አጠፋናቸው፡፡ የፈርዖንንም ቤተሰቦች አሰጠምናቸው፡፡ ሁሉም በዳዮች ነበሩም፡፡

إِنَّ شَرَّ ٱلدَّوَآبِّ عِندَ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ﴿٥٥

55ከሚንቀሳቀሱ እንስሳዎች ሁሉ አላህ ዘንድ ይበልጥ ክፉዎቹ እነዚያ ዘወትር የካዱት ናቸው፡፡ ስለዚህ እነሱ አያምኑም፡፡

ٱلَّذِينَ عَٰهَدتَّ مِنۡهُمۡ ثُمَّ يَنقُضُونَ عَهۡدَهُمۡ فِي كُلِّ مَرَّةٖ وَهُمۡ لَا يَتَّقُونَ﴿٥٦

56እነዚያ ከነሱ ቃል ኪዳን የያዝክባቸው ከዚያም በየጊዜው ቃል ኪዳናቸውን የሚያፈርሱ ናቸው፡፡ እነሱም አይጠነቀቁም፡፡

فَإِمَّا تَثۡقَفَنَّهُمۡ فِي ٱلۡحَرۡبِ فَشَرِّدۡ بِهِم مَّنۡ خَلۡفَهُمۡ لَعَلَّهُمۡ يَذَّكَّرُونَ﴿٥٧

57በጦርም ላይ ብታገኛቸው በእነርሱ ቅጣት ምክንያት (ሌሎቹ ከሓዲዎች) ይገሰጹ ዘንድ ከኋላቸው ያሉትን በትንባቸው፡፡

وَإِمَّا تَخَافَنَّ مِن قَوۡمٍ خِيَانَةٗ فَٱنۢبِذۡ إِلَيۡهِمۡ عَلَىٰ سَوَآءٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡخَآئِنِينَ﴿٥٨

58ከሕዝቦችም ክዳትን ብትፈራ (የኪዳኑን መፍረስ በማወቅ) በመተካከል ላይ ኾናችሁ ኪዳናቸውን ወደነሱ ጣልላቸው፡፡ አላህ ከዳተኞችን አይወድምና፡፡

وَلَا يَحۡسَبَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ سَبَقُوٓاْۚ إِنَّهُمۡ لَا يُعۡجِزُونَ﴿٥٩

59እነዚያም የካዱት ከአላህ ቅጣት ያመለጡ መኾናቸውን አያስቡ፡፡ እነሱ አያቅቱምና፡፡

وَأَعِدُّواْ لَهُم مَّا ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن قُوَّةٖ وَمِن رِّبَاطِ ٱلۡخَيۡلِ تُرۡهِبُونَ بِهِۦ عَدُوَّ ٱللَّهِ وَعَدُوَّكُمۡ وَءَاخَرِينَ مِن دُونِهِمۡ لَا تَعۡلَمُونَهُمُ ٱللَّهُ يَعۡلَمُهُمۡۚ وَمَا تُنفِقُواْ مِن شَيۡءٖ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ يُوَفَّ إِلَيۡكُمۡ وَأَنتُمۡ لَا تُظۡلَمُونَ﴿٦٠

60ለእነሱም ከማንኛውም ኃይልና ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ በቀር ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ የሚያውቃቸውን (መናፍቃን) የምታሸብሩበት ስትኾኑ አዘጋጁላቸው፡፡ ከማንኛውም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱትም ምንዳው ወደናንተ በሙሉ ይሰጣል፡፡ እናንተም አትበደሉም፡፡

۞ وَإِن جَنَحُواْ لِلسَّلۡمِ فَٱجۡنَحۡ لَهَا وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ﴿٦١

61ወደ ዕርቅም ቢያዘነብሉ ወደ እርሷ አዘንብል፡፡ በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚ ዐዋቂ ነውና፡፡

وَإِن يُرِيدُوٓاْ أَن يَخۡدَعُوكَ فَإِنَّ حَسۡبَكَ ٱللَّهُۚ هُوَ ٱلَّذِيٓ أَيَّدَكَ بِنَصۡرِهِۦ وَبِٱلۡمُؤۡمِنِينَ﴿٦٢

62ሊያታልሉህም ቢፈልጉ አላህ በቂህ ነው፡፡ እርሱ ያ በእርዳታውና በምእምናን ያበረታህ ነው፡፡

وَأَلَّفَ بَيۡنَ قُلُوبِهِمۡۚ لَوۡ أَنفَقۡتَ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا مَّآ أَلَّفۡتَ بَيۡنَ قُلُوبِهِمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ أَلَّفَ بَيۡنَهُمۡۚ إِنَّهُۥ عَزِيزٌ حَكِيمٞ﴿٦٣

63በልቦቻቸውም መካከል ያስማማ ነው፡፡ በምድር ያለውን ሁሉ (ሀብት) በለገስክ ኖሮ በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር፡፡ ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ፡፡ እርሱ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَسۡبُكَ ٱللَّهُ وَمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ﴿٦٤

64አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ በቂህ ነው፡፡ ለተከተሉህም ምእምናን (አላህ በቂያቸው ነው)፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَرِّضِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ عَلَى ٱلۡقِتَالِۚ إِن يَكُن مِّنكُمۡ عِشۡرُونَ صَٰبِرُونَ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ﴿٦٥

65አንተ ነቢዩ ሆይ! ምእምናንን በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው፡፡ ከእናንተ ውስጥ ሃያ ታጋሾች biኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ፡፡ ከእናንተም መቶ ቢኖሩ ከእነዚያ ከካዱት እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች ስለኾኑ ሺህን ያሸንፋሉ፤

ٱلۡـَٰٔنَ خَفَّفَ ٱللَّهُ عَنكُمۡ وَعَلِمَ أَنَّ فِيكُمۡ ضَعۡفٗاۚ فَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ صَابِرَةٞ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُمۡ أَلۡفٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفَيۡنِ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ﴿٦٦

66አሁን አላህ ከእናንተ ላይ አቀለለላችሁ፡፡ በእናንተ ውስጥም ድክመት መኖሩን ዐወቀ፡፡ ስለዚህ ከእናንተ መቶ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ፡፡ ከእናንተም ሺህ ቢኖሩ በአላህ ፈቃድ ሁለት ሺህን ያሸንፋሉ፡፡ አላህም ከታጋሾቹ ጋር ነው፡፡

مَا كَانَ لِنَبِيٍّ أَن يَكُونَ لَهُۥٓ أَسۡرَىٰ حَتَّىٰ يُثۡخِنَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ تُرِيدُونَ عَرَضَ ٱلدُّنۡيَا وَٱللَّهُ يُرِيدُ ٱلۡأٓخِرَةَۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٞ﴿٦٧

67ለነቢይ በምድር ላይ እስቲያደክም ድረስ ለእርሱ ምርኮኞች ሊኖሩት አይገባም፡፡ የቅርቢቱን ዓለም ጠፊ ጥቅም ትፈልጋላችሁ፡፡ አላህም መጨረሻይቱን ይሻል፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡

لَّوۡلَا كِتَٰبٞ مِّنَ ٱللَّهِ سَبَقَ لَمَسَّكُمۡ فِيمَآ أَخَذۡتُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ﴿٦٨

68ከአላህ ያለፈ ፍርድ ባልነበረ ኖሮ በወሰዳችሁት (ቤዛ) ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር፡፡

فَكُلُواْ مِمَّا غَنِمۡتُمۡ حَلَٰلٗا طَيِّبٗاۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ﴿٦٩

69(ከጠላት) ከዘረፋችሁትም (ሀብት) የተፈቀደ መልካም ሲኾን ብሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ قُل لِّمَن فِيٓ أَيۡدِيكُم مِّنَ ٱلۡأَسۡرَىٰٓ إِن يَعۡلَمِ ٱللَّهُ فِي قُلُوبِكُمۡ خَيۡرٗا يُؤۡتِكُمۡ خَيۡرٗا مِّمَّآ أُخِذَ مِنكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ﴿٧٠

70አንተ ነቢዩ ሆይ! ከምርኮኞች በእጆቻችሁ ላሉት በላቸው፡- «አላህ በልቦቻችሁ ውስጥ በጎን ነገር (እምነትን) ቢያውቅ ከእናንተ ከተወሰደባችሁ የተሻለን ይሰጣችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»

وَإِن يُرِيدُواْ خِيَانَتَكَ فَقَدۡ خَانُواْ ٱللَّهَ مِن قَبۡلُ فَأَمۡكَنَ مِنۡهُمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ﴿٧١

71ሊከዱህም ቢፈልጉ ከዚህ በፊት አላህን በእርግጥ ከድተዋል፡፡ ከነሱም አስመችቶሃል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَهَاجَرُواْ وَجَٰهَدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ ءَاوَواْ وَّنَصَرُوٓاْ أُوْلَٰٓئِكَ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٖۚ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَلَمۡ يُهَاجِرُواْ مَا لَكُم مِّن وَلَٰيَتِهِم مِّن شَيۡءٍ حَتَّىٰ يُهَاجِرُواْۚ وَإِنِ ٱسۡتَنصَرُوكُمۡ فِي ٱلدِّينِ فَعَلَيۡكُمُ ٱلنَّصۡرُ إِلَّا عَلَىٰ قَوۡمِۭ بَيۡنَكُمۡ وَبَيۡنَهُم مِّيثَٰقٞۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ﴿٧٢

72እነዚያ ያመኑና የተሰደዱ፡፡ በአላህም መንገድ ላይ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የታገሉ፡፡ እነዚያም (ስደተኞቹን) ያስጠጉና የረዱ፡፡ እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ እነዚያም ያመኑና ያልተሰደዱ እስከሚሰደዱ ድረስ ከነሱ ምንም ዝምድና የላችሁም፡፡ በሃይማኖትም እርዳታን ቢፈልጉባችሁ በእናንተና በነሱ መካከል ቃል ኪዳን ባላችሁ ሕዝቦች ላይ ካልኾነ በስተቀር በናንተ ላይ መርዳት አለባችሁ፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٍۚ إِلَّا تَفۡعَلُوهُ تَكُن فِتۡنَةٞ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَفَسَادٞ كَبِيرٞ﴿٧٣

73እነዚያም የካዱት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ (ከምእምናን መረዳዳትን ከከሓዲያን መቆራረጥን) ባትሠሩት በምድር ላይ ሁከትና ታላቅ ጥፋት ይኾናል፡፡

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَهَاجَرُواْ وَجَٰهَدُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ ءَاوَواْ وَّنَصَرُوٓاْ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ حَقّٗاۚ لَّهُم مَّغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ﴿٧٤

74እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉና የረዱ እነዚያ እነሱ በእውነት አማኞች ናቸው፡፡ ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው፡፡

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنۢ بَعۡدُ وَهَاجَرُواْ وَجَٰهَدُواْ مَعَكُمۡ فَأُوْلَٰٓئِكَ مِنكُمۡۚ وَأُوْلُواْ ٱلۡأَرۡحَامِ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلَىٰ بِبَعۡضٖ فِي كِتَٰبِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمُۢ﴿٧٥

75እነዚያም በኋላ ያመኑና የተሰደዱ፣ ከእናንተም ጋር ኾነው የታገሉ እነዚያ ከናንተው ናቸው፡፡ የዝምድናዎች ባለቤቶችም በአላህ መጽሐፍ ከፊሎቻቸው በከፊሉ (መውረስ) የተገቡ ናቸው፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

RELATED SURAHS