Al-Hashr

الحشر

The Gathering24 ayahsMedinan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ﴿١

1በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡

هُوَ ٱلَّذِيٓ أَخۡرَجَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ مِن دِيَٰرِهِمۡ لِأَوَّلِ ٱلۡحَشۡرِۚ مَا ظَنَنتُمۡ أَن يَخۡرُجُواْۖ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُم مَّانِعَتُهُمۡ حُصُونُهُم مِّنَ ٱللَّهِ فَأَتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِنۡ حَيۡثُ لَمۡ يَحۡتَسِبُواْۖ وَقَذَفَ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلرُّعۡبَۚ يُخۡرِبُونَ بُيُوتَهُم بِأَيۡدِيهِمۡ وَأَيۡدِي ٱلۡمُؤۡمِنِينَ فَٱعۡتَبِرُواْ يَٰٓأُوْلِي ٱلۡأَبۡصَٰرِ﴿٢

2እርሱ ያ ከመጽሐፉ ሰዎች እነዚያን የካዱትን ከቤቶቻቸው ለመጀመሪያው ማውጣት ያወጣቸው ነው፡፡ መውጣታቸውን አላሰባችሁም፡፡ እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ (ኀይል) የሚከላከሉላቸው መኾናቸውን አሰቡ፡፡ አላህም ካላሰቡት ስፍራ መጣባቸው፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ መርበድበድን ጣለባቸው፡፡ ቤቶቻቸውን በእጆቻቸውና በምእምናኖቹ እጆች ያፈርሳሉ፡፡ አስተውሉም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ!

وَلَوۡلَآ أَن كَتَبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمُ ٱلۡجَلَآءَ لَعَذَّبَهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ عَذَابُ ٱلنَّارِ﴿٣

3በእነርሱም ላይ አላህ ከአገር መውጣትን ባልጻፈ ኖሮ በቅርቢቱ ዓለም በቀጣቸው ነበር፡፡ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ (ዓለም) የእሳት ቅጣት አልላቸው፡፡

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ شَآقُّواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۖ وَمَن يُشَآقِّ ٱللَّهَ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ﴿٤

4ይህ እነርሱ አላህንና መልክተኛውን በመከራከራቸው ነው፡፡ አላህንም የሚከራከር ሰው (ይቀጣዋል)፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

مَا قَطَعۡتُم مِّن لِّينَةٍ أَوۡ تَرَكۡتُمُوهَا قَآئِمَةً عَلَىٰٓ أُصُولِهَا فَبِإِذۡنِ ٱللَّهِ وَلِيُخۡزِيَ ٱلۡفَٰسِقِينَ﴿٥

5ከዘንባባ (ከተምር ዛፍ) ማንኛዋም የቆረጣችኋት ወይም በግንዶቿ ላይ የቆመች ኾና የተዋችኋት በአላህ ፈቃድ ነው፡፡ አመጸኞቸንም ያዋርድ ዘንድ (በመቁረጥ ፈቀደ)፡፡

وَمَآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ مِنۡهُمۡ فَمَآ أَوۡجَفۡتُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ خَيۡلٖ وَلَا رِكَابٖ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يُسَلِّطُ رُسُلَهُۥ عَلَىٰ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ﴿٦

6ከእነርሱም (ገንዘብ) በመልእክተኛው ላይ አላህ የመለሰው በእርሱ ላይ ፈረሶችንና ግመሎችን አላስጋለባችሁበትም፡፡ ግን አላህ መልክተኞቹን በሚሻው ሰው ላይ ይሾማል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

مَّآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡقُرَىٰ فَلِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ كَيۡ لَا يَكُونَ دُولَةَۢ بَيۡنَ ٱلۡأَغۡنِيَآءِ مِنكُمۡۚ وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمۡ عَنۡهُ فَٱنتَهُواْۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ﴿٧

7አላህ ከከተሞቹ ሰዎች (ሀብት) በመልክተኛው ላይ የመለሰው (ሀብት) ከእናንተ ውስጥ በሀብታሞቹ መካከል ተዘዋዋሪ እንዳይኾን፡፡ ለአላህና ለመልክተኛው፣ ለዝምድና ባለቤትም፣ አባት ለሌላቸው ልጆችም፣ ለድኾችም፣ ለመንገደኛም (የሚስሰጥ) ነው፡፡ መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

لِلۡفُقَرَآءِ ٱلۡمُهَٰجِرِينَ ٱلَّذِينَ أُخۡرِجُواْ مِن دِيَٰرِهِمۡ وَأَمۡوَٰلِهِمۡ يَبۡتَغُونَ فَضۡلٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضۡوَٰنٗا وَيَنصُرُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصَّٰدِقُونَ﴿٨

8ለእነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉ፣ አላህንና መልክተኛውንም የሚረዱ ኾነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡት ስደተኞች ድኾች (ይስሰጣል)፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፡፡

وَٱلَّذِينَ تَبَوَّءُو ٱلدَّارَ وَٱلۡإِيمَٰنَ مِن قَبۡلِهِمۡ يُحِبُّونَ مَنۡ هَاجَرَ إِلَيۡهِمۡ وَلَا يَجِدُونَ فِي صُدُورِهِمۡ حَاجَةٗ مِّمَّآ أُوتُواْ وَيُؤۡثِرُونَ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ وَلَوۡ كَانَ بِهِمۡ خَصَاصَةٞۚ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفۡسِهِۦ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ﴿٩

9እነዚያም ከበፊታቸው አገሪቱን መኖሪያ ያደረጉት እምነትንም የለመዱት ወደእነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ፡፡ (ስደተኞቹ) ከተሰጡትም ነገር በልቦቻቸው ውስጥ ቅሬታን አያገኙም፡፡ በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ፡፡ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡

وَٱلَّذِينَ جَآءُو مِنۢ بَعۡدِهِمۡ يَقُولُونَ رَبَّنَا ٱغۡفِرۡ لَنَا وَلِإِخۡوَٰنِنَا ٱلَّذِينَ سَبَقُونَا بِٱلۡإِيمَٰنِ وَلَا تَجۡعَلۡ فِي قُلُوبِنَا غِلّٗا لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ رَبَّنَآ إِنَّكَ رَءُوفٞ رَّحِيمٌ﴿١٠

10እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት «ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምሕረት አድርግ፡፡ በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ፡፡ ጌታችን ሆይ! አንተ ርኅሩህ አዛኝ ነህና» ይላሉ፡፡

۞ أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ نَافَقُواْ يَقُولُونَ لِإِخۡوَٰنِهِمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ لَئِنۡ أُخۡرِجۡتُمۡ لَنَخۡرُجَنَّ مَعَكُمۡ وَلَا نُطِيعُ فِيكُمۡ أَحَدًا أَبَدٗا وَإِن قُوتِلۡتُمۡ لَنَنصُرَنَّكُمۡ وَٱللَّهُ يَشۡهَدُ إِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ﴿١١

11ወደእነዚያ ወደ ነፈቁት አላየህምን? ከመጽሐፉ ሰዎች ውስጥ ለእነዚያ ለካዱት ወንድሞቻቸው (ከአገር) «ብትባረሩ አብረናችሁ እንወጣለን፡፡ በእናንተም (ጉዳይ) አንድንም በፍጹም አንታዘዝም፡፡ ብትገድሉም በእርግጥ እንረዳችኋለን» ይሏቸዋል፡፡ አላህም እነርሱ ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል፡፡

لَئِنۡ أُخۡرِجُواْ لَا يَخۡرُجُونَ مَعَهُمۡ وَلَئِن قُوتِلُواْ لَا يَنصُرُونَهُمۡ وَلَئِن نَّصَرُوهُمۡ لَيُوَلُّنَّ ٱلۡأَدۡبَٰرَ ثُمَّ لَا يُنصَرُونَ﴿١٢

12ቢወጥጡ አብረዋቸው አይወጡም፤ ቢገደሉም አይረዱዋቸውም፡፡ ቢረዷቸውም (ለሽሽት) ጀርባቸውን ያዞራሉ፡፡ ከዚያም እርዳታን አያገኙም፡፡

لَأَنتُمۡ أَشَدُّ رَهۡبَةٗ فِي صُدُورِهِم مِّنَ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ﴿١٣

13እናንተ በልቦቻቸው ውስጥ በማስፈራት ከአላህ ይልቅ የበረታችሁ ናችሁ፡፡ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡

لَا يُقَٰتِلُونَكُمۡ جَمِيعًا إِلَّا فِي قُرٗى مُّحَصَّنَةٍ أَوۡ مِن وَرَآءِ جُدُرِۭۚ بَأۡسُهُم بَيۡنَهُمۡ شَدِيدٞۚ تَحۡسَبُهُمۡ جَمِيعٗا وَقُلُوبُهُمۡ شَتَّىٰۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَعۡقِلُونَ﴿١٤

14በተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ወይም ከአጥሮች ጀርባ ኾነው እንጅ፤ የተሰበሰቡ ኾነው አይዋጉዋችሁም፡፡ ኀይላቸው በመካከላቸው ብርቱ ነው፡፡ ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲኾኑ የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠረጥራቸዋለህ፡፡ ይህ እነሱ አእምሮ የሌላቸው ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡

كَمَثَلِ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ قَرِيبٗاۖ ذَاقُواْ وَبَالَ أَمۡرِهِمۡ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ﴿١٥

15(ብጤያቸው) እንደእነዚያ ከእነሱ በፊት በቅርብ ጊዜ የነገራቸውን ቅጣት እንደቀመሱት ብጤ ነው፡፡ ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡

كَمَثَلِ ٱلشَّيۡطَٰنِ إِذۡ قَالَ لِلۡإِنسَٰنِ ٱكۡفُرۡ فَلَمَّا كَفَرَ قَالَ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّنكَ إِنِّيٓ أَخَافُ ٱللَّهَ رَبَّ ٱلۡعَٰلَمِينَ﴿١٦

16እንደ ሰይጣን ብጤ ለሰውየው «ካድ» ባለው ጊዜና በካደም ጊዜ «እኔ ከአንተ ንጹሕ ነኝ እኔ አላህን የዓለማትን ጌታ እፈራለሁ» እንዳለው ነው፡፡

فَكَانَ عَٰقِبَتَهُمَآ أَنَّهُمَا فِي ٱلنَّارِ خَٰلِدَيۡنِ فِيهَاۚ وَذَٰلِكَ جَزَٰٓؤُاْ ٱلظَّٰلِمِينَ﴿١٧

17መጨረሻቸውም እነርሱ በውስጡ ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእሳት ውስጥ መኾን ነው፡፡ ይህም የበዳዮች ዋጋ ነው፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلۡتَنظُرۡ نَفۡسٞ مَّا قَدَّمَتۡ لِغَدٖۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ﴿١٨

18እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡

وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ نَسُواْ ٱللَّهَ فَأَنسَىٰهُمۡ أَنفُسَهُمۡۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ﴿١٩

19እንደነዚያም አላህን እንደረሱትና ነፍሶቻቸውን እንዳስረሳቸው (ሰዎች) አትኹኑ፡፡ እነዚያ እነርሱ አመጸኞቹ ናቸው፡፡

لَا يَسۡتَوِيٓ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۚ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ﴿٢٠

20የእሳት ጓዶችና የገነት ጓዶች አይተካከሉም፡፡ የገነት ጓዶች እነርሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡

لَوۡ أَنزَلۡنَا هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ عَلَىٰ جَبَلٖ لَّرَأَيۡتَهُۥ خَٰشِعٗا مُّتَصَدِّعٗا مِّنۡ خَشۡيَةِ ٱللَّهِۚ وَتِلۡكَ ٱلۡأَمۡثَٰلُ نَضۡرِبُهَا لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ﴿٢١

21ይህንን ቁርኣን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ (የተነሳ) ተዋራጅ ተሰንጣቂ ኾኖ ባየሀው ነበር። ይህችንም ምሳሌ ይገመግሙ ዘንድ ለሰዎች እንገልጻለን

هُوَ ٱللَّهُ ٱلَّذِي لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِۖ هُوَ ٱلرَّحۡمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ﴿٢٢

22እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ ነው፡፡

هُوَ ٱللَّهُ ٱلَّذِي لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡمَلِكُ ٱلۡقُدُّوسُ ٱلسَّلَٰمُ ٱلۡمُؤۡمِنُ ٱلۡمُهَيۡمِنُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡجَبَّارُ ٱلۡمُتَكَبِّرُۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يُشۡرِكُونَ﴿٢٣

23እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኀያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡

هُوَ ٱللَّهُ ٱلۡخَٰلِقُ ٱلۡبَارِئُ ٱلۡمُصَوِّرُۖ لَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ يُسَبِّحُ لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ﴿٢٤

24እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አልሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።

RELATED SURAHS