An-Najm

النجم

The Star62 ayahsMeccan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلنَّجۡمِ إِذَا هَوَىٰ﴿١

1በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡

مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمۡ وَمَا غَوَىٰ﴿٢

2ባልደረባችሁ (ነቢያችን ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡

وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلۡهَوَىٰٓ﴿٣

3ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡

إِنۡ هُوَ إِلَّا وَحۡيٞ يُوحَىٰ﴿٤

4እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡

عَلَّمَهُۥ شَدِيدُ ٱلۡقُوَىٰ﴿٥

5ኀይሎቹ ብርቱው አስተማረው፡፡

ذُو مِرَّةٖ فَٱسۡتَوَىٰ﴿٦

6የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡

وَهُوَ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡأَعۡلَىٰ﴿٧

7እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡

ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ﴿٨

8ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡

فَكَانَ قَابَ قَوۡسَيۡنِ أَوۡ أَدۡنَىٰ﴿٩

9(ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡

فَأَوۡحَىٰٓ إِلَىٰ عَبۡدِهِۦ مَآ أَوۡحَىٰ﴿١٠

10ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡

مَا كَذَبَ ٱلۡفُؤَادُ مَا رَأَىٰٓ﴿١١

11(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡

أَفَتُمَٰرُونَهُۥ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ﴿١٢

12ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን?

وَلَقَدۡ رَءَاهُ نَزۡلَةً أُخۡرَىٰ﴿١٣

13በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡

عِندَ سِدۡرَةِ ٱلۡمُنتَهَىٰ﴿١٤

14በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤

عِندَهَا جَنَّةُ ٱلۡمَأۡوَىٰٓ﴿١٥

15እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡

إِذۡ يَغۡشَى ٱلسِّدۡرَةَ مَا يَغۡشَىٰ﴿١٦

16ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡

مَا زَاغَ ٱلۡبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ﴿١٧

17ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡

لَقَدۡ رَأَىٰ مِنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِ ٱلۡكُبۡرَىٰٓ﴿١٨

18ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡

أَفَرَءَيۡتُمُ ٱللَّٰتَ وَٱلۡعُزَّىٰ﴿١٩

19አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን?

وَمَنَوٰةَ ٱلثَّالِثَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ﴿٢٠

20ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?) (የላቸውም)።

أَلَكُمُ ٱلذَّكَرُ وَلَهُ ٱلۡأُنثَىٰ﴿٢١

21ለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን?

تِلۡكَ إِذٗا قِسۡمَةٞ ضِيزَىٰٓ﴿٢٢

22ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍፍል ናት፡፡

إِنۡ هِيَ إِلَّآ أَسۡمَآءٞ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَمَا تَهۡوَى ٱلۡأَنفُسُۖ وَلَقَدۡ جَآءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ ٱلۡهُدَىٰٓ﴿٢٣

23እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡

أَمۡ لِلۡإِنسَٰنِ مَا تَمَنَّىٰ﴿٢٤

24ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን?

فَلِلَّهِ ٱلۡأٓخِرَةُ وَٱلۡأُولَىٰ﴿٢٥

25መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡

۞ وَكَم مِّن مَّلَكٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ لَا تُغۡنِي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ أَن يَأۡذَنَ ٱللَّهُ لِمَن يَشَآءُ وَيَرۡضَىٰٓ﴿٢٦

26በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡

إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ لَيُسَمُّونَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ تَسۡمِيَةَ ٱلۡأُنثَىٰ﴿٢٧

27እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡

وَمَا لَهُم بِهِۦ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّۖ وَإِنَّ ٱلظَّنَّ لَا يُغۡنِي مِنَ ٱلۡحَقِّ شَيۡـٔٗا﴿٢٨

28ለእነርሱም በእርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡

فَأَعۡرِضۡ عَن مَّن تَوَلَّىٰ عَن ذِكۡرِنَا وَلَمۡ يُرِدۡ إِلَّا ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا﴿٢٩

29ከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡

ذَٰلِكَ مَبۡلَغُهُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱهۡتَدَىٰ﴿٣٠

30ይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ድካቸው ነው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡

وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔواْ بِمَا عَمِلُواْ وَيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ بِٱلۡحُسۡنَى﴿٣١

31በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊመነዳ (ሊቀጣ) እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (ነው)፡፡

ٱلَّذِينَ يَجۡتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَۚ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلۡمَغۡفِرَةِۚ هُوَ أَعۡلَمُ بِكُمۡ إِذۡ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ وَإِذۡ أَنتُمۡ أَجِنَّةٞ فِي بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡۖ فَلَا تُزَكُّوٓاْ أَنفُسَكُمۡۖ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱتَّقَىٰٓ﴿٣٢

32(እነርሱ) እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ (የሚማሩ) ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በናንተ (ኹነታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡

أَفَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي تَوَلَّىٰ﴿٣٣

33ያንን (ከእምነት) የዞረውን አየህን?

وَأَعۡطَىٰ قَلِيلٗا وَأَكۡدَىٰٓ﴿٣٤

34ጥቂትን የሰጠውንና ያቋረጠውንም (አየህን?)

أَعِندَهُۥ عِلۡمُ ٱلۡغَيۡبِ فَهُوَ يَرَىٰٓ﴿٣٥

35የሩቁ ምስጢር ዕውቀት እርሱ ዘንድ አልለን? ስለዚህ እርሱ ያያልን?

أَمۡ لَمۡ يُنَبَّأۡ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ﴿٣٦

36ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን?

وَإِبۡرَٰهِيمَ ٱلَّذِي وَفَّىٰٓ﴿٣٧

37በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?)

أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰ﴿٣٨

38(እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡

وَأَن لَّيۡسَ لِلۡإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ﴿٣٩

39ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡

وَأَنَّ سَعۡيَهُۥ سَوۡفَ يُرَىٰ﴿٤٠

40ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡

ثُمَّ يُجۡزَىٰهُ ٱلۡجَزَآءَ ٱلۡأَوۡفَىٰ﴿٤١

41ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡

وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلۡمُنتَهَىٰ﴿٤٢

42መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡

وَأَنَّهُۥ هُوَ أَضۡحَكَ وَأَبۡكَىٰ﴿٤٣

43እነሆ እርሱም አስሳቀ፣ አስለቀሰም፡፡

وَأَنَّهُۥ هُوَ أَمَاتَ وَأَحۡيَا﴿٤٤

44እነሆ እርሱም ገደለ፣ አስነሳም፡፡

وَأَنَّهُۥ خَلَقَ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰ﴿٤٥

45እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ፡፡

مِن نُّطۡفَةٍ إِذَا تُمۡنَىٰ﴿٤٦

46ከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ፡፡

وَأَنَّ عَلَيۡهِ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰ﴿٤٧

47የኋለኛይቱም ማስነሳት በእርሱ ላይ ነው፡፡

وَأَنَّهُۥ هُوَ أَغۡنَىٰ وَأَقۡنَىٰ﴿٤٨

48እነሆ እርሱም አከበረ፣ ጥሪተኛም አደረገ፡፡

وَأَنَّهُۥ هُوَ رَبُّ ٱلشِّعۡرَىٰ﴿٤٩

49እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡

وَأَنَّهُۥٓ أَهۡلَكَ عَادًا ٱلۡأُولَىٰ﴿٥٠

50እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል፡፡

وَثَمُودَاْ فَمَآ أَبۡقَىٰ﴿٥١

51ሰሙድንም (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም፡፡

وَقَوۡمَ نُوحٖ مِّن قَبۡلُۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ هُمۡ أَظۡلَمَ وَأَطۡغَىٰ﴿٥٢

52በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነርሱ ነበሩና፡፡

وَٱلۡمُؤۡتَفِكَةَ أَهۡوَىٰ﴿٥٣

53የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡

فَغَشَّىٰهَا مَا غَشَّىٰ﴿٥٤

54ያለበሳትንም አለበሳት፡፡

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ﴿٥٥

55ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ?

هَٰذَا نَذِيرٞ مِّنَ ٱلنُّذُرِ ٱلۡأُولَىٰٓ﴿٥٦

56ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡

أَزِفَتِ ٱلۡأٓزِفَةُ﴿٥٧

57ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡

لَيۡسَ لَهَا مِن دُونِ ٱللَّهِ كَاشِفَةٌ﴿٥٨

58ለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡

أَفَمِنۡ هَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ تَعۡجَبُونَ﴿٥٩

59ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?

وَتَضۡحَكُونَ وَلَا تَبۡكُونَ﴿٦٠

60ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን?

وَأَنتُمۡ سَٰمِدُونَ﴿٦١

61እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡

فَٱسۡجُدُواْۤ لِلَّهِۤ وَٱعۡبُدُواْ۩﴿٦٢

62ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡ [1]

RELATED SURAHS