At-Tahrim

التحريم

The Prohibition12 ayahsMedinan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَۖ تَبۡتَغِي مَرۡضَاتَ أَزۡوَٰجِكَۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ﴿١

1አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትኾን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

قَدۡ فَرَضَ ٱللَّهُ لَكُمۡ تَحِلَّةَ أَيۡمَٰنِكُمۡۚ وَٱللَّهُ مَوۡلَىٰكُمۡۖ وَهُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ﴿٢

2አላህ ለእናንተ የመሓሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፡፡ አላህም ረዳታችሁ ነው፡፡ እርሱም ዐዋቂው ጥበበኛው ነው፡፡

وَإِذۡ أَسَرَّ ٱلنَّبِيُّ إِلَىٰ بَعۡضِ أَزۡوَٰجِهِۦ حَدِيثٗا فَلَمَّا نَبَّأَتۡ بِهِۦ وَأَظۡهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيۡهِ عَرَّفَ بَعۡضَهُۥ وَأَعۡرَضَ عَنۢ بَعۡضٖۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتۡ مَنۡ أَنۢبَأَكَ هَٰذَاۖ قَالَ نَبَّأَنِيَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡخَبِيرُ﴿٣

3ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን (ማውራትዋን) ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፡፡ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት፤

إِن تَتُوبَآ إِلَى ٱللَّهِ فَقَدۡ صَغَتۡ قُلُوبُكُمَاۖ وَإِن تَظَٰهَرَا عَلَيۡهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ هُوَ مَوۡلَىٰهُ وَجِبۡرِيلُ وَصَٰلِحُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۖ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ بَعۡدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ﴿٤

4ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና (ትስማማላችሁ)፡፡ በእርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፡፡ ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው፡፡

عَسَىٰ رَبُّهُۥٓ إِن طَلَّقَكُنَّ أَن يُبۡدِلَهُۥٓ أَزۡوَٰجًا خَيۡرٗا مِّنكُنَّ مُسۡلِمَٰتٖ مُّؤۡمِنَٰتٖ قَٰنِتَٰتٖ تَٰٓئِبَٰتٍ عَٰبِدَٰتٖ سَٰٓئِحَٰتٖ ثَيِّبَٰتٖ وَأَبۡكَارٗا﴿٥

5(መላችሁንም) ቢፈታችሁ ከእናንተ የበለጡ ሚስቶችን ሙስሊሞች፣ አማኞች፣ ታዛዦች፣ ተጸጻቾች፣ (ለአላህ) ተገዢዎች፣ ጾመኛዎች ፈቶች፣ ደናግልም የኾኑትን ጌታው ሊለውጠው ይከጀላል፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ قُوٓاْ أَنفُسَكُمۡ وَأَهۡلِيكُمۡ نَارٗا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلۡحِجَارَةُ عَلَيۡهَا مَلَٰٓئِكَةٌ غِلَاظٞ شِدَادٞ لَّا يَعۡصُونَ ٱللَّهَ مَآ أَمَرَهُمۡ وَيَفۡعَلُونَ مَا يُؤۡمَرُونَ﴿٦

6እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَا تَعۡتَذِرُواْ ٱلۡيَوۡمَۖ إِنَّمَا تُجۡزَوۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ﴿٧

7እላንተ የካዳችሁ ሆይ! ዛሬ አታመካኙ፡፡ የምትመነዱት ያንን ትሠሩት የነበራችሁትን ብቻ ነው (ይባላሉ)፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ تُوبُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ تَوۡبَةٗ نَّصُوحًا عَسَىٰ رَبُّكُمۡ أَن يُكَفِّرَ عَنكُمۡ سَيِّـَٔاتِكُمۡ وَيُدۡخِلَكُمۡ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ يَوۡمَ لَا يُخۡزِي ٱللَّهُ ٱلنَّبِيَّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥۖ نُورُهُمۡ يَسۡعَىٰ بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَبِأَيۡمَٰنِهِمۡ يَقُولُونَ رَبَّنَآ أَتۡمِمۡ لَنَا نُورَنَا وَٱغۡفِرۡ لَنَآۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ﴿٨

8እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ንጹሕ የኾነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፡፡ ጌታችሁ ከእናንተ ኀጢኣቶቻችሁን ሊሰርይላችሁ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ሊያስገባችሁ ይከጀላልና፡፡ አላህ ነቢዩን፣ እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያመኑትን በማያሳፍርበት ቀን ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲኾን «ጌታችን ሆይ! ብርሃናችንን ሙላልን፣ ለእኛ ምሕረትም አድርግልን፣ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና» ይላሉ፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ جَٰهِدِ ٱلۡكُفَّارَ وَٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱغۡلُظۡ عَلَيۡهِمۡۚ وَمَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ﴿٩

9አንተ ነቢዩ ሆይ! ከሓዲዎችንና መናፍቃንን ታገል፡፡ በእነርሱም ላይ በርታ፡፡ መኖሪያቸውም ገሀነም ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!

ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱمۡرَأَتَ نُوحٖ وَٱمۡرَأَتَ لُوطٖۖ كَانَتَا تَحۡتَ عَبۡدَيۡنِ مِنۡ عِبَادِنَا صَٰلِحَيۡنِ فَخَانَتَاهُمَا فَلَمۡ يُغۡنِيَا عَنۡهُمَا مِنَ ٱللَّهِ شَيۡـٔٗا وَقِيلَ ٱدۡخُلَا ٱلنَّارَ مَعَ ٱلدَّٰخِلِينَ﴿١٠

10አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች የኑሕን ሴትና የሉጥን ሴት ምሳሌ አደረገ፡፡ ከባሮቻችን ከኾኑ ሁለት መልካም ባሪያዎች ሥር ነበሩ፡፡ ከዱዋቸውም፡፡ ከአላህም (ቅጣት ኑሕና ሉጥ) ከሚስቶቻቸው ምንም አልገፈተሩላቸውም፡፡ ከገቢዎቹም ጋር «እሳትን ግቡ» ተባሉ፡፡

وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱمۡرَأَتَ فِرۡعَوۡنَ إِذۡ قَالَتۡ رَبِّ ٱبۡنِ لِي عِندَكَ بَيۡتٗا فِي ٱلۡجَنَّةِ وَنَجِّنِي مِن فِرۡعَوۡنَ وَعَمَلِهِۦ وَنَجِّنِي مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ﴿١١

11ለእነዚያ ለአመኑትም የፈርኦንን ሴት አላህ ምሳሌ አደረገ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለእኔ ቤትን ገንባልኝ፡፡ ከፈርዖንና ከሥራውም አድነኝ፡፡ ከበደለኞቹ ሕዝቦችም አድነኝ» ባለች ጊዜ፡፡

وَمَرۡيَمَ ٱبۡنَتَ عِمۡرَٰنَ ٱلَّتِيٓ أَحۡصَنَتۡ فَرۡجَهَا فَنَفَخۡنَا فِيهِ مِن رُّوحِنَا وَصَدَّقَتۡ بِكَلِمَٰتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِۦ وَكَانَتۡ مِنَ ٱلۡقَٰنِتِينَ﴿١٢

12የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን (ምሳሌ አደረገ)፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡

RELATED SURAHS