Muhammad

محمد

Muhammad38 ayahsMedinan

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ أَضَلَّ أَعۡمَٰلَهُمۡ﴿١

1እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድም የከለከሉ (አላህ) ሥራዎቻቸውን አጠፋባቸው፡፡

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَءَامَنُواْ بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٖ وَهُوَ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّهِمۡ كَفَّرَ عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡ وَأَصۡلَحَ بَالَهُمۡ﴿٢

2እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱتَّبَعُواْ ٱلۡبَٰطِلَ وَأَنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّبَعُواْ ٱلۡحَقَّ مِن رَّبِّهِمۡۚ كَذَٰلِكَ يَضۡرِبُ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ أَمۡثَٰلَهُمۡ﴿٣

3ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመኾናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የኾነን እውነት ስለተከተሉ ነው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል፡፡

فَإِذَا لَقِيتُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَضَرۡبَ ٱلرِّقَابِ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَثۡخَنتُمُوهُمۡ فَشُدُّواْ ٱلۡوَثَاقَ فَإِمَّا مَنَّۢا بَعۡدُ وَإِمَّا فِدَآءً حَتَّىٰ تَضَعَ ٱلۡحَرۡبُ أَوۡزَارَهَاۚ ذَٰلِكَۖ وَلَوۡ يَشَآءُ ٱللَّهُ لَٱنتَصَرَ مِنۡهُمۡ وَلَٰكِن لِّيَبۡلُوَاْ بَعۡضَكُم بِبَعۡضٖۗ وَٱلَّذِينَ قُتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَلَن يُضِلَّ أَعۡمَٰلَهُمۡ﴿٤

4እነዚያንም የካዱትን (በጦር ላይ) ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኀይል ምቱ፡፡ ባደካማችኋቸውም ጊዜ (አትግደሏቸው ማርኳቸው)፡፡ ማሰሪያውንም አጥብቁ፡፡ በኋላም ወይም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ፤ ወይም ትበዧቸዋላችሁ፡፡ (ይህም) ጦሪቱ መሳሪያዋን እስከምትጥል ድረስ ነው፡፡ (ነገሩ) ይህ ነው፡፡ አላህም ቢሻ ከእነርሱ (ያለጦር) በተበቀለ ነበር፡፡ ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)፡፡ እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉትን ሥራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸውም፡፡

سَيَهۡدِيهِمۡ وَيُصۡلِحُ بَالَهُمۡ﴿٥

5በእርግጥ ይመራቸዋል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡

وَيُدۡخِلُهُمُ ٱلۡجَنَّةَ عَرَّفَهَا لَهُمۡ﴿٦

6ገነትንም ያገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አስታውቋታል፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن تَنصُرُواْ ٱللَّهَ يَنصُرۡكُمۡ وَيُثَبِّتۡ أَقۡدَامَكُمۡ﴿٧

7እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ሃይማኖቱን) ብትረዱ፤ ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَتَعۡسٗا لَّهُمۡ وَأَضَلَّ أَعۡمَٰلَهُمۡ﴿٨

8እነዚያም የካዱት ለእነርሱ ጥፋት ተገባቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም አጠፋባቸው፡፡

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَرِهُواْ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأَحۡبَطَ أَعۡمَٰلَهُمۡ﴿٩

9ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው፡፡

۞ أَفَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۖ دَمَّرَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡۖ وَلِلۡكَٰفِرِينَ أَمۡثَٰلُهَا﴿١٠

10የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት (ከሓዲዎች) መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ያዩ ዘንድ በምድር ለይ አልኼዱምን? አላህ በእነርሱ ላይ (ያላቸውን ሁሉ) አጠፋባቸው፡፡ ለከሐዲዎችም ሁሉ ብጤዎችዋ አልሏቸው፡፡

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ مَوۡلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَأَنَّ ٱلۡكَٰفِرِينَ لَا مَوۡلَىٰ لَهُمۡ﴿١١

11ይህ አላህ የእነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ስለኾነና ከሓዲዎችም ለእነርሱ ረዳት ስለሌላቸው ነው፡፡

إِنَّ ٱللَّهَ يُدۡخِلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يَتَمَتَّعُونَ وَيَأۡكُلُونَ كَمَا تَأۡكُلُ ٱلۡأَنۡعَٰمُ وَٱلنَّارُ مَثۡوٗى لَّهُمۡ﴿١٢

12አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያገባቸዋል፡፡ እነዚያም የካዱት (በቅርቢቱ ዓለም) ይጣቀማሉ፡፡ እንስሳዎችም እንደሚበሉ ይበላሉ፡፡ እሳትም ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት፡፡

وَكَأَيِّن مِّن قَرۡيَةٍ هِيَ أَشَدُّ قُوَّةٗ مِّن قَرۡيَتِكَ ٱلَّتِيٓ أَخۡرَجَتۡكَ أَهۡلَكۡنَٰهُمۡ فَلَا نَاصِرَ لَهُمۡ﴿١٣

13ከከተማም እርሷ ከዚያች ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በኀይል ጠንካራ የኾነች (ባለቤቶችዋን) ያጠፋናቸው ብዙ ናት፡፡ ለእነርሱም ረዳት አልነበራቸውም፡፡

أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّهِۦ كَمَن زُيِّنَ لَهُۥ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ وَٱتَّبَعُوٓاْ أَهۡوَآءَهُم﴿١٤

14ከጌታው በኾነች አስረጅ ላይ የኾነ ምእመን ክፉ ሥራቸው ለእነርሱ እንደ ተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉት ነውን?

مَّثَلُ ٱلۡجَنَّةِ ٱلَّتِي وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۖ فِيهَآ أَنۡهَٰرٞ مِّن مَّآءٍ غَيۡرِ ءَاسِنٖ وَأَنۡهَٰرٞ مِّن لَّبَنٖ لَّمۡ يَتَغَيَّرۡ طَعۡمُهُۥ وَأَنۡهَٰرٞ مِّنۡ خَمۡرٖ لَّذَّةٖ لِّلشَّٰرِبِينَ وَأَنۡهَٰرٞ مِّنۡ عَسَلٖ مُّصَفّٗىۖ وَلَهُمۡ فِيهَا مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ وَمَغۡفِرَةٞ مِّن رَّبِّهِمۡۖ كَمَنۡ هُوَ خَٰلِدٞ فِي ٱلنَّارِ وَسُقُواْ مَآءً حَمِيمٗا فَقَطَّعَ أَمۡعَآءَهُمۡ﴿١٥

15የዚያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት ገነት ምስል በውስጧ ሺታው ከማይለወጥ ውሃ ወንዞች፣ ጣዕሙ ከማይለወጥ ወተትም ወንዞች፣ ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች ከተነጠረ ማርም ወንዞች አልሉባት፡፡ ለእነርሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ (በያይነቱ) ከጌታቸው ምሕረትም አልላቸው፡፡ (በዚች ገነት ውስጥ ዘውታሪ የኾነ ሰው) እርሱ በእሳት ውስጥ ዘውታሪ እንደኾነ ሰው፣ ሞቃትንም ውሃ እንደተጋቱ፣ አንጀቶቻቸውንም ወዲያውኑ እንደቆራረጠው ነውን? (አይደለም)፡፡

وَمِنۡهُم مَّن يَسۡتَمِعُ إِلَيۡكَ حَتَّىٰٓ إِذَا خَرَجُواْ مِنۡ عِندِكَ قَالُواْ لِلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ مَاذَا قَالَ ءَانِفًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ وَٱتَّبَعُوٓاْ أَهۡوَآءَهُمۡ﴿١٦

16ከእነርሱም ወዳንተ የሚያዳምጡ አልሉ፡፡ ከአንተም ዘንድ በወጡ ጊዜ ለእነዚያ ዕውቀት ለተሰጡት «አሁን ምን አለ?» ይላሉ፡፡ እነዚህ እነዚያ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተመባቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ናቸው፡፡

وَٱلَّذِينَ ٱهۡتَدَوۡاْ زَادَهُمۡ هُدٗى وَءَاتَىٰهُمۡ تَقۡوَىٰهُمۡ﴿١٧

17እነዚያም የተመሩት (አላህ) መመራትን ጨመረላቸው፡፡ (ከእሳት) መጥጠበቂያቸውንም ሰጣቸው፡፡

فَهَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّا ٱلسَّاعَةَ أَن تَأۡتِيَهُم بَغۡتَةٗۖ فَقَدۡ جَآءَ أَشۡرَاطُهَاۚ فَأَنَّىٰ لَهُمۡ إِذَا جَآءَتۡهُمۡ ذِكۡرَىٰهُمۡ﴿١٨

18ሰዓቲቱንም ድንገት የምትመጣባቸው መኾንዋን እንጅ ይጠባበቃሉን? ምልክቶችዋም በእርግጥ መጥተወል፡፡ በመጣቻቸውም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል?

فَٱعۡلَمۡ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ وَٱسۡتَغۡفِرۡ لِذَنۢبِكَ وَلِلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِۗ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ مُتَقَلَّبَكُمۡ وَمَثۡوَىٰكُمۡ﴿١٩

19እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ለመእምናትም ምሕረትን ለምን፡፡ አላህ መዘዋወሪያችሁን፣ መርጊያችሁንም ያውቃል፡፡

وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَوۡلَا نُزِّلَتۡ سُورَةٞۖ فَإِذَآ أُنزِلَتۡ سُورَةٞ مُّحۡكَمَةٞ وَذُكِرَ فِيهَا ٱلۡقِتَالُ رَأَيۡتَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ يَنظُرُونَ إِلَيۡكَ نَظَرَ ٱلۡمَغۡشِيِّ عَلَيۡهِ مِنَ ٱلۡمَوۡتِۖ فَأَوۡلَىٰ لَهُمۡ﴿٢٠

20እነዚያም ያመኑት ሰዎች (መታገል ያለባት) «ሱራ አትወርድም ኖሮአልን?» ይላሉ፡፡ የጠነከረችም ሱራ በተወረደችና በውስጧም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሺታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የኾነ መከራ በርሱ ላይ እንደ ወደቀበት ሰው አስተያየት ወዳንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ለእነሱም ወዮላቸው፡፡

طَاعَةٞ وَقَوۡلٞ مَّعۡرُوفٞۚ فَإِذَا عَزَمَ ٱلۡأَمۡرُ فَلَوۡ صَدَقُواْ ٱللَّهَ لَكَانَ خَيۡرٗا لَّهُمۡ﴿٢١

21ታዛዥነትና መልካም ንግግር (ይሻላቸዋል) ትዕዛዙም ቁርጥ በኾነ ጊዜ ለአላህ (ትዕዛዝ) እውነተኞች በኾኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር፡፡

فَهَلۡ عَسَيۡتُمۡ إِن تَوَلَّيۡتُمۡ أَن تُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَتُقَطِّعُوٓاْ أَرۡحَامَكُمۡ﴿٢٢

22ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُ فَأَصَمَّهُمۡ وَأَعۡمَىٰٓ أَبۡصَٰرَهُمۡ﴿٢٣

23እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው፣ ያደነቆራቸውም፣ ዓይኖቻቸውንም ያወራቸው ናቸው፡፡

أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ٱلۡقُرۡءَانَ أَمۡ عَلَىٰ قُلُوبٍ أَقۡفَالُهَآ﴿٢٤

24ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አልሉባትን?

إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱرۡتَدُّواْ عَلَىٰٓ أَدۡبَٰرِهِم مِّنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ ٱلۡهُدَى ٱلشَّيۡطَٰنُ سَوَّلَ لَهُمۡ وَأَمۡلَىٰ لَهُمۡ﴿٢٥

25እነዚያ ለእነርሱ ቅኑ መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን ለእነርሱ መመለሳቸውን ሸለመላቸው፡፡ ለእነርሱም አዝዘናጋቸው፡፡

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَالُواْ لِلَّذِينَ كَرِهُواْ مَا نَزَّلَ ٱللَّهُ سَنُطِيعُكُمۡ فِي بَعۡضِ ٱلۡأَمۡرِۖ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ إِسۡرَارَهُمۡ﴿٢٦

26ይህ እነርሱ ለእነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት «በነገሩ ከፊል እንታዘዛችኋለን» ያሉ በመኾናቸው ነው፡፡ አላህም መደበቃቸውን ያውቃል፡፡

فَكَيۡفَ إِذَا تَوَفَّتۡهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَضۡرِبُونَ وُجُوهَهُمۡ وَأَدۡبَٰرَهُمۡ﴿٢٧

27መላእክትም ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን የሚመቱ ሲኾኑ በገደሉዋቸው ጊዜ (ኹኔታቸው) እንዴት ይኾናል?

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمُ ٱتَّبَعُواْ مَآ أَسۡخَطَ ٱللَّهَ وَكَرِهُواْ رِضۡوَٰنَهُۥ فَأَحۡبَطَ أَعۡمَٰلَهُمۡ﴿٢٨

28ይህ እነርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ስለ ተከተሉ ውዴታውንም ስለ ጠሉ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው፡፡

أَمۡ حَسِبَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ أَن لَّن يُخۡرِجَ ٱللَّهُ أَضۡغَٰنَهُمۡ﴿٢٩

29እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አላህ ቂሞቻቸውን አለማውጣቱን ጠረጠሩን?

وَلَوۡ نَشَآءُ لَأَرَيۡنَٰكَهُمۡ فَلَعَرَفۡتَهُم بِسِيمَٰهُمۡۚ وَلَتَعۡرِفَنَّهُمۡ فِي لَحۡنِ ٱلۡقَوۡلِۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ أَعۡمَٰلَكُمۡ﴿٣٠

30በሻንም ኖሮ እነርሱን ባሳየንህና በምልክታቸውም በእርግጥ ባወቅሃቸው ነበር፡፡ ንግግርንም በማሸሞራቸው በእርግጥ ታውቃቸዋለህ፡፡ አላህም ሥራዎቻችሁን ያውቃል፡፡

وَلَنَبۡلُوَنَّكُمۡ حَتَّىٰ نَعۡلَمَ ٱلۡمُجَٰهِدِينَ مِنكُمۡ وَٱلصَّٰبِرِينَ وَنَبۡلُوَاْ أَخۡبَارَكُمۡ﴿٣١

31ከእናንተም ታጋዮቹንና ታጋሾቹን እስከምናውቅ፣ ወሬዎቻችሁንም እስከምንገልጽ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَشَآقُّواْ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ ٱلۡهُدَىٰ لَن يَضُرُّواْ ٱللَّهَ شَيۡـٔٗا وَسَيُحۡبِطُ أَعۡمَٰلَهُمۡ﴿٣٢

32እነዚያ የካዱና ከአላህም መንገድ ያገዱ ለእነርሱም ቅኑ መንገድ ከተገለጸላቸው በኋላ መልክተኛውን የተከራከሩ አላህን በምንም አይጎዱትም፡፡ ሥራዎቻቸውንም በእርግጥ ያበላሻል፡፡

۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَ وَلَا تُبۡطِلُوٓاْ أَعۡمَٰلَكُمۡ﴿٣٣

33እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ፡፡

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ ثُمَّ مَاتُواْ وَهُمۡ كُفَّارٞ فَلَن يَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَهُمۡ﴿٣٤

34እነዚያ የካዱ፣ ከአላህም መንገድ ያገዱ፣ ከዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ኾነው የሞቱ አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም፡፡

فَلَا تَهِنُواْ وَتَدۡعُوٓاْ إِلَى ٱلسَّلۡمِ وَأَنتُمُ ٱلۡأَعۡلَوۡنَ وَٱللَّهُ مَعَكُمۡ وَلَن يَتِرَكُمۡ أَعۡمَٰلَكُمۡ﴿٣٥

35እናንተም አሸናፊዎቹ ስትኾኑ አላህ ከእናንተ ጋር ሲሆን አትድከሙ፡፡ ወደ ዕርቅም አትጥሩ፡፡ ሥራዎቻችሁንም ፈጽሞ አያጎድልባችሁም፡፡

إِنَّمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا لَعِبٞ وَلَهۡوٞۚ وَإِن تُؤۡمِنُواْ وَتَتَّقُواْ يُؤۡتِكُمۡ أُجُورَكُمۡ وَلَا يَسۡـَٔلۡكُمۡ أَمۡوَٰلَكُمۡ﴿٣٦

36ቅርቢቱ ሕይወት ጫወታና ዛዛታ ብቻ ናት፡፡ ብታምኑም ብትጠነቀቁም ምንዳዎቻችሁን ይሰጣችኋል፡፡ ገንዘቦቻችሁንም (ሁሉ) አይጠይቃችሁም፡፡

إِن يَسۡـَٔلۡكُمُوهَا فَيُحۡفِكُمۡ تَبۡخَلُواْ وَيُخۡرِجۡ أَضۡغَٰنَكُمۡ﴿٣٧

37እርሷን ቢጠይቃችሁና ችክ ቢልባችሁ ትሰስታላችሁ፡፡ ቂሞቻችሁንም ያወጣል፡፡

هَٰٓأَنتُمۡ هَٰٓؤُلَآءِ تُدۡعَوۡنَ لِتُنفِقُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَمِنكُم مَّن يَبۡخَلُۖ وَمَن يَبۡخَلۡ فَإِنَّمَا يَبۡخَلُ عَن نَّفۡسِهِۦۚ وَٱللَّهُ ٱلۡغَنِيُّ وَأَنتُمُ ٱلۡفُقَرَآءُۚ وَإِن تَتَوَلَّوۡاْ يَسۡتَبۡدِلۡ قَوۡمًا غَيۡرَكُمۡ ثُمَّ لَا يَكُونُوٓاْ أَمۡثَٰلَكُم﴿٣٨

38ንቁ! እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጥጠሩ ናችሁ፡፡ ከእናንተም ውስጥ የሚሰስት ሰው አልለ፡፡ የሚሰስትም ሰው የሚሰስተው በራሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ አላህም ከበርቴ ነው፡፡ እናንተም ድኾች ናችሁ፡፡ ብትሸሹም ሌሎችን ሕዝቦች ይለውጣል፡፡ ከዚያም (ባለመታዘዝ) ብጤዎቻችሁ አይኾኑም፡፡

RELATED SURAHS